❤️ ከሊባኖስ ❤️
ሐና እና ኢያቄም ወለዱ ሰማይተጨነቀ አዳም በመከራ
አዲሷም ሰማይ አስገኘች ፀሐይ
ምስራቀ ምስራቃት የአምላክ መገኛ
ከሊባኖስ ድንግል ነይ ወደኛ(፪)
በእርግማን ቀን ለቅሶ እየዘራ
በልጅሽ ሞት ዓለም ተቀደሰ
የፍጥረቱ ዕንባ በመስቀል ታበሰ(፪)
የሕያዋን እናታቸው ሆነሽ
ለቀደመች ሔዋን ጠበቃ ሆንሽ
ደስተኛዋ ደስ ይበልሽ ማርያም
ከአንቺ ወጣ የዓለሙ ሰላም(፪)
ጽኑ ገመድ በአንቺ ተቆረጠ
የፍዳ ዓመት ይኸው ተለወጠ
በሐና ልጅ በኢያቄም ፍሬ
ደስታ ሆነ ቅኔ እና ዝማሬ(፪)
በወለዱሽ በሐና በኢያቄም
ተማጽነናል ድንግል ማርያም
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ልጆችሽን ጠብቂን ከጥፋት
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ኢትዮጵያን ጠብቂያት ከጥፋት
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈