"በኢትዮጵያ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጠየቁ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ግጭት የሚያበቃ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አቀረቡ።
ኒው ዮርክ ውስጥ ለጋዜጠኞች የተናገሩት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እየተካሄደ ያለውና ወደ አጎራባች ክልሎች ለተስፋፋው ጦርነት ወታደራዊ መፍትሄ ሊገኝለት አይችልም ብለዋል።
ዋና ጸሐፊው "በአገሪቱ ውስጥ ለተከሰተው ቀውስ መፍትሄ ለመፈለግ በኢትዮጵያውያን የሚመራ ፖለቲካዊ ንግግር ለመጀመር የሚያስችል መላ መፈጠር አለበት" ብለዋል።
ጨምረውም "እንዲህ አይነቱ ንግግር ላጋጠመው ግጭት ምክንያት ለሆኑት ነገሮች መፍትሄ ለመፈለግ ከማስቻሉ በተጨማሪ ወደ ሰላም ለመሄድ የኢትዮጵያውያን ድምጽ እንዲሰማ ያስችላል" ሲሉ ተናገረዋል።
በትግራይ ክልል ውስጥ ከአስር ወራት በፊት ተቀስቅሶ አሁን ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ጦርነት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመፈናቀል የዳረገ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ችግር ላይ ጥሏል።
የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አስከፊ የሆነ ደረጃ ላይ በመድረሱ የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያቀርቡ ያልተገደበ እንቅስቃሴ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።
ጉቴሬዝ ጨምረውም ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ወሲባዊ ጥቃት እንደ ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋሉን አውግዘዋል።
በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ ባይታወቅም በርካቶች ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ ይታመናል።
የእርዳታ ድርጅቶች እንደሚሉት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።
ከሰኔ ወር ማብቂያ ወዲህ ጦርነቱ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ከተስፋፋ በኋላ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ክልሎቹ አሳውቀዋል።"
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube