"በትግራይ ያለው የእርዳታ አቅርቦት ሊያልቅ መሆኑን ሳማንታ ፓወር ገለጹ
የአሜሪካ መንግሥት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በነበሩት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የእርዳታ ድርጅቶች ለተረጂዎች የሚያቀርቡት ምግብ ሊያልቅባቸው እንደሆነ አሳወቁ።
በድርጅቱ ዋና ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ስም በወጣው መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ አደጋ በተጋለጡበት በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ የየኤስኤይድ እና ሌሎች ድርጅቶች የእርዳታ ምግብ ማከማቻ መጋዘኖች ባዶ ናቸው በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ይህ የእርዳታ ምግብ እጥረት የተከሰተው ምግብ ባለመኖሩ ምክንያት ሳይሆን "የአየርና የመንገድ እርዳታ አቅርቦት መስመሮችን ጨምሮ የእርዳታ አቅርቦትና የእርዳታ ሠራተኞችን ሥራ የኢትዮጵያ መንግሥት በማደናቀፉ ነው" ሲል መግለጫው ከሷል።
ስለዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ለመታደግ የእርዳታ አቅርቦት በፍጥነት ወደ ትግራይ ክልል እንዲቀርብ የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲፈቅድ ጠይቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ አርብ በሰጠው መግለጫ መንግሥት ሆን ብሎ እርዳታ እንዳይደርስ እያገደ ነው የሚለውን ውንጀላ ውድቅ አድርጎታል።
የጠቅላይ ሚኒስተሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ በሰጡት ምላሽ በክልሉ ካለው የደኅንነት ስጋት አንጻር በተለያዩ ስፍራዎች የፍተሻ ጣቢያዎች መኖራቸውንና ማንኛውም ወደ ትግራይ ክልል ለመግባት የሚፈልግ አካል በፌደራል መንግሥቱ የተቀመጠውን አሰራር መከተል እንደሚኖበት ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግሥታት በአፋር ሰመራ ወደ ተግራይ የሚገቡ እና የሚወጡ የእርዳታ እህል የሚያጓጉዙ መኪኖችን በሚመለከት እየሰራ መሆኑን በመግለጽ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች ካሉ በቀጣይ በሚኖር ውይይት እንደሚታዩ አመልክተዋል።
ባለፈው አንድ ወር ተኩል ውስጥ የተወሰነ መጠን ያለው እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባ መፈቀዱን ያስታወሰው መግለጫው አሁንም የምግብ እርዳታ ጭነው ሰመራ አፋር ውስጥና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተጠባበቁ ያሉ ተሽከርካሪዎች እንዳሉም አመልክቷል።
በተጨማሪም በትግራይ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት ለማሟላት በየቀኑ 100 ምግብና የነፍስ አድን አቅርቦቶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ማቅረብ ቢቻል ኖሮ በሐምሌ ወር በአጠቃላይ እስከ አምስት ሺህ መኪኖች መግባት ይኖርባቸው እንደነበር ገልጾ እስከአሁን የቀረበው ግን በ320 መኪኖች የተጫነ እርዳታ ነው ብሏል።
መግለጫው ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት የተወሰነ መጠን ያለውን የምግብ አቅርቦት እንዲጓጓዝ በፍጥነት እንዲንቀሳቀስ ማድረጉን በአዎንታዊ መልኩ የጠቀሰው ቢሆንም አቅርቦቱ በጣም ትንሽና የዘገየ ነው ብሎታል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦት ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ መፍቀዱን በተደጋጋሚ የገለጸ ሲሆን ቁጥጥር የሚያደርገው የጦር መሳሪያ ለአማጺያኑ እንዳይደርስ ለመከላከል ነው ብሏል።
በትግራይ ክልል በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ ጦርነት ተቀስቅሶ ለወራት ሲካሄድ ከቆየ በኋላ የፌደራል መንግሥቱ የተናጠል ተኩስ አውጆ ባለፈው ሰኔ ወር ሠራዊቱን ማስወጣቱ ይታወሳል።
ነገር ግን የህወሓት አማጺያን በአጎራባቾቹ የአፋርና የአማራ ክልሎች ውስጥ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ጦርነቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተስፋፍቷል።
በዚህም ሳቢያ በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ በማድረግ ተጨማሪ ሰብአዊ ቀውስ ቀስቅሷል።
ሳምንታ ፓወር በመግለጫው ላይ የህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸማቸውን አቁመው ከገቡባቸው ክልሎች እንዲወጡ እንዲሁም የአማራ እና የኤርትራ ኃይሎችም ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የአሜሪካ መንግሥት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ ዋና ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ከሁለት ሳምንት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ጦርነትና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወሳል።"
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube