"ሳማንታ ፓወር ህወሓት ከአፋር እና አማራ እንዲወጣ ዳግም ጠየቁ
የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓዎር ህወሓት ከያዛቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎች እንዲወጣ ዳግም ጥሪ አቀረቡ።
ህወሓት ግጭቱን አቁሞ ከያዛቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎች ወጥቶ ወደ ድርድር እንዲመጠ የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን ሳማንታ ፓወር በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
"የህወሓት የሚፈጽመው ጥቃት ግጭቱን እንዲሁም የኢትዮጵያን ሕዝብ ስቃይ ያራዝማል" ብለዋል የተራድኦ ድርጅቱ ኃላፊ።
ከሁለት ወራት በፊት የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም አውጆ ከትግራይ መዲና መውጣቱን ተከትሎ የህወሓት አማጺያን በርካታ የትግራይ ክልል ቦታዎችን ከተቆጣሩ በኋላ በመልሶ ማጥቃት ወደ አማራ እና አፋር ክልል ዘልቀው መግባታቸው ይታወሳል።
የህወሓት አማጺያን የፌደራሉ መንግሥት የተኩስ አቁም ጥያቄያቸውን እንዲቀበል ለማስገደድ እያደረጉ ያሉትን ጥቃት እንደማያቆሙ ገልጸው ነበር።
የአገር መከላከያ ሠራዊት ከክልል ኃይሎች ጋር በመሆኑ የህወሓት ኃይሎች በአማራ እና አፋር ክልል የያዟቸውን አካባቢዎችን ለማስለቀቅ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በተደጋጋሚ ተዘግቧል።
ሳማንታ ፓዎር በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ በህወሓት ጥቃት ከአፋር እና ከአማራ ክልሎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸውን ገልጸዋል።
በዚህ ሳምንት መጀመሪያም ዩኤስኤይድ በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው 136ሺህ በላይ የክልሎቹ ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን ሳማንታ ፓዎር ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሳማንታ ባለፈው አርብ በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከዘጠኝ ወራት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የእርዳታ ድርጅቶች ለተረጂዎች የሚያቀርቡት ምግብ ሊያልቅባቸው እንደሆነ አስታውቀው ነበር።
ሳማንታ የየኤስኤይድ እና ሌሎች ድርጅቶች የእርዳታ ምግብ ማከማቻ መጋዘኖች ባዶ ናቸው በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛሉ ብለው ነበር ባወጡት መግለጫ።
ይህ የእርዳታ ምግብ እጥረት የተከሰተው ምግብ ባለመኖሩ ምክንያት ሳይሆን "የአየርና የመንገድ እርዳታ አቅርቦት መስመሮችን ጨምሮ የእርዳታ አቅርቦትና የእርዳታ ሠራተኞችን ሥራ የኢትዮጵያ መንግሥት በማደናቀፉ ነው" ሲል ከሷል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ውንጀላ ውድቅ አድረጎ ወደ ክልሉ አስፈላጊው እርዳታ እንዲደርስ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ነገር ግን በክልሉ ካለው የደኅንነት ስጋት አንጻር በተለያዩ ስፍራዎች የፍተሻ ጣቢያዎች በመኖራቸው ማንኛውም አካል በፌደራል መንግሥቱ የተቀመጠውን አሰራር መከተል እንዳለበት ገልጿል።"
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube