"አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የኤርትራ ጦር ዳግም ወደ ትግራይ እየተሰማራ ነው አሉ
አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የኤርትራ ጦር በቅርብ ቀናት ውስጥ ዳግም ወደ ትግራይ እየገባ መሆኑ አሳስቦናል አሉ።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ከትናንት በስቲያ፤ "[የኤርትራ ጦር] ሰኔ ወር ላይ ከወጣ በኋላ በበርካታ ቁጥር ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ተመለሶ ገብቷል" ማለታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የአውሮፓ ሕብረት ዲፕሎማቶች ደግሞ ነሐሴ 14 የጻፉት የውስጥ ማስታወሻ (ኢንተርናል ሜሞረንደም) ኤርትራ የትግራይ ድንበርን ተሻግረው የገቡ ተጨማሪ ኃይሎች አሰማርታለች ይላል።
ይህ የአንቶኒ ብሊንከን እና የአውሮፓ ሕብረት ማሳሰቢያ የተሰማው አሜሪካ በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የኤርትራ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ላይ በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምክንያት ማዕቀብ መጣሏን ካስታወቀች በኋላ ነው።
ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ፤ በጦርነቱ ውስጥ በከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሚከሰሰው የኤርትራ ሠራዊት መሪ ወይም ከፍተኛ ባለሥልጣን በመሆናቸው ማዕቀቡ ተጥሎባቸዋል።
ሮይተር ተመልክቸዋለሁ ያለው የአውሮፓ ሕብረት የውስጥ ማስታወሻ፤ ኤርትራ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሱባቸው ምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ጦሯን አስፍራለች ይላል።
እንደ ሮይተርስ የዜና ወኪል ከሆነ የአውሮፓ ሕብረት የውስጥ ማስታወሻ፤ የኤርትራ ጦር አዲ ጎሹ እና ሑመራ ከተሞች አካባቢ "ታንክ እና ከባድ መሣሪያዎችን በመታጠቅ መከላከያ ቦታ ይዟል" ይላል።
ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕመድ ወደ ቱርክ ከማቅናታቸው ከአንድ ቀን በፊት ማለትም ነሐሴ 11 ወደ አስመራ ተጉዘው ነበር ይላል። ማስታወሻው ጠቅላይ ሚንሰትሩ ወደ አስመራ ስለማቅናታቸው ይፋ አለመደረጉን አስታውሷል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተውበታል በሚባለው ጦርነት የኤርትራ ጦር ከፌደራሉ መንግሥት ጎን ተሰልፎ የህወሓት አማጺያንን ወግቷል።
የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም አውጆ በርካታ የትግራይ ስፍራዎችን ለቅቆ ከወጣ በኋላ የህወሓት አማጺያን መቀለን ጨምሮ በርካታ የክልሉን ቦታ መቆጣጠራቸው ይታወሳል።
በመቀጠልም ህወሓት ያስቀመጠውን የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታዎችን የፌደራሉ መንግሥት እንዲቀበል ለማስገደድ በሚል ምክንያት የህወሓት አማጺያን ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች በመዝመት የተለያዩ ቦታዎችን መያዛቸው ይታወቃል።
የፌደራሉ መንግሥት ከክልል ኃይሎች ጋር በመሆን የህወሓት አማጺያንን ከያዟቸው ስፍራዎች ለማስለቀቅ ጥቃት እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።"
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube