"የመን ያሉ ወደ 5 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አገር ቤት ለመመለስ እየተጠባበቁ መሆኑ ተገለጸ
በየመን ካለው አለመረጋጋትና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ወደ 5 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ሪሊፍዌብ ዘግቧል።
በያዝነው ሳምንት 300 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በገዛ ፈቃዳቸው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) በሚያዘጋጃቸው በረራዎች ወደ አገራቸው ለመመለስ ተዘጋጅተዋል።
ድርጅቱ እአአ እስከ 2021 መጠናቀቂያ ድረስ በሳምንት ሁለት በረራዎችን በማድረግ በገዛ ፈቃዳቸው የሚመለሱ ስደተኞች ወደ አገራቸው ለማስገባት እየሠራ እንደሆነ አስታውቋል።
"የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ የመን የሚገኙ ስደተኞች በእጅጉ እየተረሱ ነው" ብለዋል በየመን የአይኦኤም ምክትል የሚሽን ኃላፊው ጆን ማኪው።
በ2021 እስካሁን ድረስ ወደ 600 የሚጠጉ ፈቃደኛ ስደተኞች ከየመን፣ ኤደን ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ሲሆን፤ ሌሎች 79 ስደተኞች ደግሞ ከሰነዓ ተነስተው አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዛሬ ከኤደን የተነሳ ስደተኞችን የጫነ አውሮፕላን አዲስ አበባ እንደሚገባ ይጠበቃል።
ይህ ስደተኞችን በገዛ ፈቃዳቸው ወደ አገራቸው የመመለስ ተግባር ቀላል እንዳልሆነና አይኦኤም ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ 3 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ ገንዘብ ከበረራዎች በተጨማሪ በየመን እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማትን ለመርዳትም ይውላል።
"እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ተጨማሪ ድጋፎችን እንዲያደርጉልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በየመን መሄጃ አጥተው ይገኛሉ። ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ይህንን አስቸጋሪ ሁኔታ በማምለጥ ወደ አገራቸው መግባት ነው" ብለዋል ምክትል የሚሽን ኃላፊው።
በየመን እስከ 32 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ የተደናቀፈባቸው ናቸው።
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ከፍተኛ ፈተና ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ስደተኞቹን ለሌሎች አላማዎች እያዋሏቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።
አንዳንድ ስደተኞች እዳቸውን ለመክፈል የእርሻ ማሳዎች ላይ የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ የሚገደዱ ሲሆን፤ ሌሎች ደግሞ ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል።
በተጨማሪም ስደተኞቹ እየታገቱ ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ካላስላኩ እንደሚገደሉ ይነገራቸዋል።
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ እነዚህን ሁሉ መከራዎች አልፈው በሕይወት መቆየት የቻሉት ደግሞ በቂ የሆነ ንጹህ ውሃ፣ ምግብ እና የጤና አገልግሎትን ማግኘት አይችሉም።
ከስደት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ አንዷ የሆነችው የ24 ዓመቷ ትዕግስት "ከባድ ድብደባ ደርሶብኛል፣ ታስሬያለሁ፣ እንዲሁም ያለአግባብ መብቴ ተጥሷል" ትላለች።
"አብዛኛውን ጊዜ እየራበኝ ነው የምተኛው። ይሄ ሁሉ ነገር ከደረሰብኝ በኋላ ወደ አገሬ እና ወደ ቤተሰቦቼ መመለስ መቻሌ በጣም አስደስቶኛል" ስትልም ታክላለች።
በፈቃዳቸው ወደ አገራቸው የሚመለሱ ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የአይኦኤም ማዕከል በኩል ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን፤ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ የመጓጓዣ ወጪያቸው ይሸፈንላቸዋል።
በተጨማሪም ወደ ማኅበረሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት የሥነ ልቦና ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
"በየመን የሚገኙ ፈቃደኛ ስደተኞችን የመመለስ ሥራ በጣም ወሳኝ ነው። ሥራውም ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጡ በሚችሉ ሂደቶች መደገፍ አለበት" ብለዋል በኢትዮጵያ በአይኦኤም በኃላፊነት የሚሠሩት ማላምቦ ሙንጋ።
የአይኦኤም መረጃ እንደሚያመላክተው እአአ በ2019 ብቻ በአጠቃላይ 138 ሺህ ስደተኞች ወደ የመን የገቡ ሲሆን፤ በ2021 ደግሞ 37 ሺህ 500 ስደተኞች የመን ገብተዋል።"
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube