"የዓለም መሪዎች ገለልተኛ ቡድን አባላት በኢትዮጵያ የተኩስ አቁምና ድርድር እንዲደረግ ጠየቁ
የዓለም መሪዎች ገለልተኛ ቡድን አባላት፣ 'ዘ ኤልደርስ' (ታላላቅ ሰዎች) በትግራዩ ጦርነት እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች የተኩስ አቁም እንዲያደርጉና እንዲደራደሩ ለማበረታታት እርምጃ እንዲወስድ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትን ጠየቁ።
ቡድኑ ይህንን ያቀረበው ዓለም አቀፍ ደኅንነትና ሰላም ለማስፈንና የፀጥታው ምክር ቤት ሊኖረው ስለሚገባው ሚና ጳጉሜ 2፣ 2013ዓ.ም በተደረገ ጉባኤ ላይ ነው።
ምክር ቤቱ በአንድነት እርምጃ እንዲወስድና በብቃትም ቀውሶችን የመፍታት ሚና እንዲጫወት ተጠይቋል።
በዓለም ላይ እየተከሰቱ ካሉ ዋነኛ ቀውሶች ተብለው ከቀረቡት ጉዳዮች መካከል የትግራይን ጦርነት ጨምሮ አፍጋኒስታን፣ ምያንማር እንዲሁም በፍልስጥኤም እየተከሰቱ ያሉ ጉዳዮች ተነስተዋል።
"ጦርነቱን ማስቆም እየተከሰተ ያለውን ስቃይ ማክተሚያ ብቸኛው መንገድ ነው" በማለትም በዚህ ወቅት የቡድኑ ሰብሳቢ፣ የቀድሞ የአየርላንድ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት እና የቀድሞው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሜሪ ሮቢንሰን ተናግረዋል።
ከጦርነቱም መባባስ ጋር ተያይዞ የሴቶችና የታዳጊዎች ጥበቃ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ሰብሳቢዋ አፅንኦት ሰጥተዋል።
"ምክር ቤቱ በጦርነቱ ምክንያት እየተከሰተ ስላለው አስከፊ የሰብዓዊ ቀውስ ሁኔታና የምግብ ዋስትና አደጋ ውስጥ መውደቅ ከዚህ ቀደም ገለጻ ተደርጎለታል። በተጨማሪም በትግራዩ ጦርነት ረሃብና ወሲባዊ ጥቃት እንደ ጦር መሳሪያ መዋላቸውን ጨምሮ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ ጥሰቶች እየተፈፀሙ ነው" ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ምክርቤቱ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ለመረዳት ትግራይን ጨምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርግና አስቸኳይ የፖለቲካዊ መፍትሄም ሊበጀለት እንደሚገባም ተጠቁሟል። ሰብሳቢዋ "ወታደራዊ መፍትሄ አይበጅም" ብለዋል።
በዚህም ወቅት በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ "ቡድኑ በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያሉትን ምክክር እንደግፋለን" ከማለት በተጨማሪ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው በቅርቡ መሾማቸውንም ጥሩ እመርታ ነው ብለዋል።
በትግራይ ኃይሎችና በፌደራሉ መንግሥት መካከል የተነሳው ጦርነት አስረኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን ወደ አጎራባቾቹ አፋርና አማራ ክልሎች ተዛምቶ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አፈናቅሏል።
በአፋር ክልል ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ112 ሺህ በላይ መድረሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አስታውቋል።
በትግራይ ወደ 900 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን ሌሎች 5 ሚሊየን የሚሆኑት የክልሉ ነዋሪዎች ደግሞ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ገልጿል። ።
የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል።"
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube