"ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 29 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ
ኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ኪራሙ ወረዳ ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 29 ሰዎች መገደላቸውንና ከ40 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።
በኪራሙ ወረዳ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 ቀን 2014 ዓ.ም በተፈጸሙ ሦስት ተያያዥ ጥቃቶች 18 ሲቪል ሰዎች ሲገደሉ በተመሳሳይ መስከረም 8 ቀን 2014 ዓ.ም ውልማይ በተባለው ቀበሌ በተፈጸመ ሌላ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት እንደደረሰው ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፉትን ጥቃቶች በመሸሽም ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ በኪራሙ ወረዳ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች አካባቢያቸውን ጥለው ወደ አጎራባች ቀበሌዎች ተሰደዋል።
በተከታታይ በሚፈጸሙት በእነዚህ ጥቃቶች ሳቢያም በወረዳው የሚገኙ ሰላማዊ ነዋሪዎች ለደኅንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው እንደሚያሳስበው ኢሰመኮ ጨምሮ ገልጿል።
ባለው አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች የተፈናቀሉት ሰዎች በአሁኑ ጊዜ በኖሌ ቀበሌ፣በሀሮ እና ኪራሙ ከተሞች ተጠልለው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አመልክቷል።
ተፈናቃዮቹ ለወራት ከቀያቸው ርቀው በመጠለያዎች ውስጥ ቢገኙም አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታና ሌሎች ድጋፎችን ባለማግኘታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ለኢሰመኮ መግለጻቸውን አስታውቋል።
በአካባቢው ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያትም በአሁኑ ወቅት ኪራሙ ወረዳን ከቡሬና ነቀምቴ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ዋና ዋና መንገዶች ለተሸከርካሪ እንቅስቃሴ ተዘግተው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ማረጋገጡን ገልጿል።
ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ላይ ለበርካታ ሰዎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት የሆነው ጥቃት በማን እንደተፈጸመ ያለው ነገር ባይኖርም በአካባቢው ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ጥቃት ሲፈጸም መቆየቱ ይታወቃል።
ለእነዚህ ጥቃቶች መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀው ሸኔ የሚባለውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይከሰሳል።
ኢሰመኮ ጥቃቶቹን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የፌዴራል መንግሥትና የክልሉ መስተዳደር የፀጥታ ኃይሎች በኪራሙ ወረዳ የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።
የሚመለከታቸው አካላት በወረዳው ላለው የፀጥታ ስጋት "ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እና በነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ ኃይሎችን ከሕግ ፊት ለማቅረብ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ" አሳስቧል።
ኢሰመኮ ጨምሮ እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ የተዘጉት ወረዳውን ከሌሎች አካባቢዎች ጋር የሚያገናኙት መንገዶች እንዲከፈቱና አስፈላጊው ሰብአዊ እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።"
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube