"ታሊባን ፀጉር አስተካካዮች ጺም እንዳይቆርጡ ወይም እንዳይላጩ አገደ
ታሊባን ከሥልጣን ከተወገደ በኋላ የወንዶች የውበት ሳሎኖች በአፍጋን ወንዶች በስፋት ሲዘወተሩ ቆይተዋል
ታሊባን የእስልምና ሕግን ይጻረራል በሚል በአፍጋኒስታን ሄልማድን ግዛት ውስጥ የሚገኙ ፀጉር አስተካካዮች የደንበኞቻቸውን ጺም እንዳይላጩ ወይም እንዳይቆርጡ አገደ።
ታዲያ ይህንን እገዳ የሚጥስ ማንኛውም የፀጉር አስተካካይ ቅጣት እንደሚጠብቀው የታሊባን የሐይማኖት ፖሊስ አስጠንቅቋል።
በመዲናይቱ ካቡል የሚገኙ አንዳንድ ፀጉር አስተካካዮችም ተመሳሳይ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
አሁን እየወጡ ያሉ መመሪያዎች ታሊባን ከሳምንታት በፊት ስልጣን ሲጨብጥ ከገባው ቃል በተቃራኒ ቡድኑ ቀደም ሲል በነበረው የሥልጣን ዘመኑ ሲያስፈጽማቸው የነበሩትን ጥብቅ ውሳኔዎች እየመለሰ እንደሆነ ጠቋሚ ነው ተብሏል።
ታሊባን ነሐሴ ወር ላይ ስልጣኑን መልሶ ከያዘ በኋላ በተቃዋሚዎቹ ላይ ከባድ ቅጣት እየፈጸመ ይገኛል።
ቅዳሜ የቡድኑ ተዋጊዎች አራት ጠላፊዎች ናቸው የተባሉ ሰዎችን በጥይት ገድለው አስከሬናቸው በሄራት ግዛት ጎዳናዎች ላይ እንዲሰቀል አድርገዋል።
የታሊባን መኮንኖች በደቡባዊ ሄልማንድ ግዛት ውስጥ በፀጉር ማስተካከያ ቤቶች ላይ በለጠፉት ማስታወቂያ የፀጉር አስተካካዮች ለፀጉር እና ጢም የሸሪዓ ሕግን መከተል እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል።
በቢቢሲ የተመለከተው ማስታወቂያ "ማንም ቅሬታ የማሰማት መብት የለውም" ሲል ይነበባል።
በካቡል አንድ ፀጉር አስተካካይ "ተዋጊዎቹ መጥተው ጺም እንዳናሳጥር አዘውናል። ከመካከላቸው አንዱ በስውር የሚቆጣጠሩንን እንደሚልኩ ነገሮኛል" ሲል ገልጿል።
በከተማዋ ካሉ ስመ ጥር የወንዶች የውበት ሳሎኖች ውስጥ አንዱን የሚያስተዳድረው ሌላ የፀጉር ሥራ ባለሙያ ፣ የመንግሥት ባለሥልጣን ነኝ ከሚል ሰው ተደውሎለት እንደነበር ተናግሯል።
"የአሜሪካን ስታይል መከተል አቁም" ብሎኛል ያለ ሲሆን የማንንም ጺም መላጨት ወይም ማሳጠር እንደሌለበት እንደተነገረውም ተናግሯል።
እንደ አውሮፓውያኑ ከ1996 እስከ 2001 ታሊባን በስልጣን በነበረበት ጊዜ የተለያዩ የፀጉር አቆራረጦችን ከልክለው የነበረ ሲሆን ወንዶች ጺም እንዲያሳድጉ አጥብቀው ያዙ ነበር።
ሆኖም ጺምን ሙለጭ አድርጎ መላጨት በአብዛኛው አፍጋኒስታኒዊ ወንዶች ዘንድ የተለመደ ተግባር ነው።
ለደኅንነታቸው የሰጉና ስማቸውን ያልጠቀሱ ፀጉር አስተካካዮች "አዲሶቹ ሕጎች ኑሮን ለመቀጠል አስቸጋሪ አድርጎብናል" ይላሉ።
"ለብዙ ዓመታት ወደ ፀጉር ማስተካካያ ቤቴ ወጣቶች እየመጡ እንደፍላጎታቸው እና ወቅቱን መስለው መታየት የሚችሉበት ቦታ ነበር። ከዚህ በኋላ እዚህ ሥራ ላይ መቆየት ምንም ፋይዳ የለውም" ሲል ለቢቢሲ ተንግሯል።
ሌላኛው የፀጉር ባለሙያ ደግሞ "የፋሽን ሳሎኖች እና የፀጉር አስተካካዮች የሚከለከሉ ሥራዎች እየሆኑ ነው። ይህ ለ15 ዓመታት የቆየሁበት ሥራዬ ነበር፤ ከዚህ በኋላ መቀጠል የምችል አይመስለኝም" በማለት ገልጿል።
በምዕራባዊው ሄራት ከተማ የሚገኝ አንድ ፀጉር አስተካካይ ደግሞ ጺም እዳይቆርጥ በግልጽ ትዕዛዝ ባይደርሰውም ይህንን አገልግሎት መስጠት ማቆሙን ተናሯል።
"ደንበኞች ጺማቸውን አይላጩም [ምክንያቱም] በጎዳና ላይ በታሊባን ተዋጊዎች እንዲነኩ አይፈልጉም። መቀላቀል እና መምሰል ይፈልጋሉ። የፀጉር ማስተካከያ ዋጋ ቢቀንስም ለፋሽን ማንም ግድ የለውም" ብሏል።"
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube