Репост из: TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar
🚨“ የሟቾች ቁጥር 8 ነው። ቁስለኞች ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ” - ነዋሪዎች
➡️ “ ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ነው፡፡ የሟቾች ”ቁጥር እስካሁን ባለኝ መረጃ ስምንት ነው" - ኤሊዳዓር ወረዳ
በአፋር ክልል ኤሊዳዓር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት በአርሶ አደሮች፣ ሴቶች፣ ህፃናት ሞትና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎችና ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ በሰጡን ቃል፣“ 8 ሰዎች ተገድለዋል። ከ10 በላይ ደግሞ ቆስለው ዱብቲ ሆስፒታል ገብተዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከወደ ጅቡቲ አቅጣጫ በመጣ ድሮን ነው ” ብለዋል።
መረጃ አቀባይ ነዋሪዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?
“ ትላንት ሌሊት አካባቢ መጀመሪያ ሦስት ሰዎች ተገደሉ። ሦስቱንም ዱሮን ነው ያጠቃቸው። ከዚያ ዛሬ ጠዋት ሟቾቹን ሊቀብሩ የነበሩ ሰዎችን ዱሮን እንደገና መጥቶ ነው ያጠቃቸው።
መጀመሪያ ሦስት ወንዶች የሞቱ ሲሆን፣ እንደገና መጥቶ ሦስት ጊዜ ነው ጥቃት የተፈጸመው። ሦስቱ ከተገደሉ በኋላ ድሮን መጥቶ ሴቶችና ህጻናትን አታክ ተደረጉ።
አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ስምንት ነው። ቁስለኞች ደግሞ ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ዱብቲ ሆስፒታል ገብተው ነው የሚገኙት።
ጥቃት የተፈጸመበት አካባቢ ድንበር ነው ለጅቡቲ። ድሮኑ በየት አቅጣጫ እንደሚመጣ ይታውቃል። ይታያል ማለት ነው ከጅቡቲ እንደመጣ ይታወቃል።
‘ ጅቡቲን የሚቃወሙ ታጣቂ ኃይሎች አሉ ’ ብለው ነው ጥቃቱን የሚፈጽሙት። ከቁስለኞቹ ውስጥ የአስር አመት ህጻናት አሉ። ሴቶች አሉ። ዱብቲ ሆስፒታል እግሯና እጇ የተቆረጠች ልጅ አለች ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ “ የድሮን ጥቃት ደርሷል ” መባሉን እንዲያረጋግጡልን የጠየቃቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኤሊዳዓር ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን አካል፣ “ አዎ። ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ነው፡፡ የሟቾች ቁጥር እስካሁን ባለኝ መረጃ ስምንት ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።
“ ጥቃት የደረሰበት ሲያሩ ቀበሌ የጅቡቲ ድምበር ” መሆኑን ጠቅሰው ለተጨማሪ መረጃ በቦታው ያሉ የጸጥታ አካላት ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል።
“ በዚያኛው በኩል በስንት ኪሎ ሜትር እንደሆነ፣ በዚህኛው በኩል በስንት ኪሎ ሜትር እንደሆነ የጸጥታ አካላት ምላሽ እየተጠበቀ ነው ” ሲሉ ጠቁመዋል።
ከሟቾች በተጨማሪ በሴቶችና ሕጻናት ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል ስለዚህስ ጉዳይ ምን ይላሉ ? ምን ያክል ሰዎች ናቸው የተጎዱት? ስንል ላቀረብነው ተጨማሪ ጥያቄም የወረዳው አካል ምላሽ ሰጥተዋል።
በምላሻቸውም፣ “ አዎ፡፡ እኛ በቦታው ስላልቆምን የጸጥታ አካላት ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ፤ ቁስለኛው ፣ምን ያህል እንደሆነ አጣርተው እስከሚያመጡ እየተጠበቀ” ነው ብለዋል።
ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቃቸው አንድ የክልሉ ፓሊስ አባል፣ “ ከመረጃ ውጪ ነኝ ” ሲሉ የስልክ ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ኔትዎርክ የሌለበት ቦታ ነው ያለሁት። በእርግጥ መረጃ የለኝም። እያሉ ግን ሰምቻለሁ ” ከማለት ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
(በጉዳዩን ተጨማሪ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia