Репост из: TIKVAH-ETHIOPIA
የአዲስ አበባ ከተማ የተርሚናል አገልግሎት አሰራርና ቁጥጥር ደንብ ቁጥር 186/2017 ምን ይላል ?
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 95 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ደንብ አውጥቷል፡፡
ደንቡ ምን ይላል ?
በተርሚናል አገልግሎት ሥራ ላይ የሚደራጁ ተርሚናል ኢንተርፕራይዞች የሥራ እና ክህሎት ቢሮ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት እንደሚደራጁ ይገልጻል።
ቀደም ሲል ተደራጅተው በህጋዊ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የተርሚናል ኢንተርፕራይዞች መስፈርቱን አሟልተው ሲቀርቡ ዳግም እንዲደራጁ እንደሚድረገም ያመለክታል።
የአደረጃጀት መስፈርቱን ያሟሉ ማህበራት ሲደራጁ በተርሚናል ኢንተርፕራይዙ ስም መደበኛና ዝግ የሂሳብ አካውንት መክፈት እንደሚኖርባቸውም ይገልጻል።
በተርሚናል አገልግሎት ሥራ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የሥራ ውል እንዲገቡ ይደረጋሉ።
የሚገቡት ውል ለ1 ዓመት ነው። የስራ አፈጻጸማቸው እየታየ ለአንድ አመት ለአንድ ጊዜ ብቻ ሊታደስ እንደሚችል ደንቡ ይገልጻል።
የተርሚ ማል ኢንተርፕራዞቹ የውል ዘመናቸው ከመጠናቀቁ በፊት የቁጠባ ካፒታላቸውን ታሳቢ በማድረግ ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ የሚሸጋገሩበር ሥራ በሥራና ክህሎት ቢሮ በኩል ይሰራል።
ኢንተርፕራይዞቹ ከሰበሰቡት ጠቅላላ ገቢ 30% (ሰላሳ በመቶ) የግዴታ ቁጠባ ይቆጠባሉ። 50% (ሃምሳ በመቶ) በመደበኛ ተንቀሳቃሽ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ገቢ ይደርጋሉ።
የተርሚናል ኢንተርፕራይዞች ከሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ ላይ 20% (ሀያ በመቶ) ለመንግስት ገቢ ያደርጋሉ።
(ሙሉ ደንቡ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia