Репост из: atewhidu awelen
"ወሎ"
✍✍✍✍✍✍✍
እስኪ ልጠይቅሽ አንቺ ሚስኪን ሀገር፤
የፍቅር ተምሳሌት የደጋጎች መንደር፤
እንዴት ከርመሽ ይሆን ፍቅርሽ ወዘወዘኝ፤
ጉዳትሽን ስሰማ እንባው እየናጠኝ፤
በሀሳብ ማእበል ሁሌም እቀዝፍና፤
እንቅልፍ ይነሳኛል ናፍቆቱ እየጠና።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ከወሎ ሰማይ ስር ምንድነው ምሰማው፤
እስኪ ልጠይቅሽ እውነት ነው ውሸት ነው?
ክብርሽ ተዋረደ በስግብግብ ጁንታ፤
እሳት ቀረበልሽ የጥይት ጋጋታ፤
ህፃናት አሰሙ ዋይ ዋይ የሚል ጩኸት፤
ረሀብ ሲበረታ አልችል ብሎ አንጀት፤
ያቺ ሚስኪን እህት በሱና አሸብርቃ፤
ተሰትራ ኖራ ከቤት ተደብቃ፤
ዛሬ የግድ ሆነ ልትሄድ ርቃ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
አባቶች ረገፉ በዱር በገደሉ፤
ከስግብግብ ጁንታ ወገኔን ሲያስጥሉ፤
እና ወገኖቼ ምንድነው ዝምታው፤
በእጁ ላጎረሰ ይሄ ነው እውነታው፤
በአርሂቡ ባህል እንግዳ ምትሸኘው፤
ዛሬ ጨልሞባት የለችም ከቀየው፤
በሮች ተዘግተዋል ቤቱም ወና ሆኗል፤
አዝመራው ብቻውን ዘንበል ዘንበል ይላል፤
ወፉ አራዊቱ በፍቅርሽ ተርቧል፤
ጭር ብሎ ሲያየው ስለአንቺ ያስባል።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ያ አሏህ ጀሊሉ አንተው እዘንልን፤
ወንጀላችን ማረን በእዝነት አይንህ እየን፤
መከራውም አልፎ ደስታውን አሳየን፤
በፍቅር ትቦርቅ ከደጇ ትቆየን፤
ህፃናት ይሩጡ ለጥ ባለው ሜዳ፤
አውጥተህ አሳየን ከስደቱ ጓዳ፤
የሱና ወንድሜ ከሀገር ርቋል፤
ጎጆ እንደሌለው ይሄው የትም ወድቋል፤
ከመስጂዱም ሸሸ ከቂርአት ማእድ፤
ምርጫው የግድ ሆነ ከሀገር መሰደድ፤
አንተው እዘንልን አዛኝ ነህ ምንግዜም፤
ወንድሜ ይመለስ ከሀገሩ ይክተም።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ምንም ብተነፍስ እርካታ አይሰማኝ፤
የምሰማው ወሬ ረመጥ ሆኖብኝ፤
ከውስጤ ተቀብሮ እያብሰለሰለኝ፤
መከራሽን ከማይ ክብርሽም ሲዋረድ፤
ደስስ ይለኝ ነበረ ከፊት ሆኜ ብነድ፤
ጥይት ቢበሳሳኝ አንገቴም ቢቀላ፤
ደረቴን በሰጠሁ ያንቺ ህይወት ቀጥላ፤
ደስ ይለኝ ነበረ እንደሻማ ብቀልጥ፤
ባንቺ ንፅህና ከማይስ ሲላገጥ፤
በፅኑ ብገረፍ በረሀብ አለንጋ፤
ያቺን የዋህ እናት ከማያት ጠውልጋ፤
አጥንት ከስጋው ተጣብቆ አንድ ላይ፤
እዝነቱን ከጅለው ዞሩ ወደ ሰማይ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
በጣም የገረመኝ ወሎ ምን አጠፋች፤
ከሌማቱ አጥፋ በፍቅር ባጎረሰች፤
ያጎረሰውን እጅ መንከስ ምን ይሉታል፤
አይንን በጨው አሽቶ የሰውን ልጅ መግደል፤
ይሄ የሰው አውሬ ወገን በላሽ ጭራቅ፤
ይጠፋል ከምንጩ አይቀርም ከመድረቅ።
ኢ ን ሻ አ ሏ ህ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
እኔ ግን በአሏህ እርግጠኛ ነኝ፤
በጭብጡ ወድቆ ፍርዱን እንደሚያገኝ፤
ስለዚህ እህቴ ሶብርን ሰንቂ፤
በፅናት ተውበሽ ከአሏህ ስር ውደቂ፤
ምንግዜም አያፍርም በሱ የተመካ፤
ከችግር በኃላ ይኖራል ሲፈካ፤
በመርከቡ እለፊ ፈተናውን ቀዝፈሽ፤
ኢማንሽም ይስበት በችግር ላይ አልፈሽ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ወሎ ለምለሚቷ የውበቷ ሙዳይ፤
ገራገር ደግነት ያስጌጡሽ አማላይ፤
ከመከራ ወጥተሽ ስትቦርቂ ልይሽ፤
በክፉ ያሰበሽ ይሁን አመድ አፋሽ፤
ጨለማው ይወገድ ብርሀን ይፈንጥቅ፤
ጉልበቱ ይብረክረክ ይበልልሽ ድቅቅ፤
የጠላትሽ ጡንቻ ይሁነው ቄጠማ፤
ድል ካንቺጋ ይሁን በፍልሚያው አውድማ።
https://t.me/AbuSarahh
https://t.me/AbuSarahh
✍✍✍✍✍✍✍
እስኪ ልጠይቅሽ አንቺ ሚስኪን ሀገር፤
የፍቅር ተምሳሌት የደጋጎች መንደር፤
እንዴት ከርመሽ ይሆን ፍቅርሽ ወዘወዘኝ፤
ጉዳትሽን ስሰማ እንባው እየናጠኝ፤
በሀሳብ ማእበል ሁሌም እቀዝፍና፤
እንቅልፍ ይነሳኛል ናፍቆቱ እየጠና።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ከወሎ ሰማይ ስር ምንድነው ምሰማው፤
እስኪ ልጠይቅሽ እውነት ነው ውሸት ነው?
ክብርሽ ተዋረደ በስግብግብ ጁንታ፤
እሳት ቀረበልሽ የጥይት ጋጋታ፤
ህፃናት አሰሙ ዋይ ዋይ የሚል ጩኸት፤
ረሀብ ሲበረታ አልችል ብሎ አንጀት፤
ያቺ ሚስኪን እህት በሱና አሸብርቃ፤
ተሰትራ ኖራ ከቤት ተደብቃ፤
ዛሬ የግድ ሆነ ልትሄድ ርቃ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
አባቶች ረገፉ በዱር በገደሉ፤
ከስግብግብ ጁንታ ወገኔን ሲያስጥሉ፤
እና ወገኖቼ ምንድነው ዝምታው፤
በእጁ ላጎረሰ ይሄ ነው እውነታው፤
በአርሂቡ ባህል እንግዳ ምትሸኘው፤
ዛሬ ጨልሞባት የለችም ከቀየው፤
በሮች ተዘግተዋል ቤቱም ወና ሆኗል፤
አዝመራው ብቻውን ዘንበል ዘንበል ይላል፤
ወፉ አራዊቱ በፍቅርሽ ተርቧል፤
ጭር ብሎ ሲያየው ስለአንቺ ያስባል።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ያ አሏህ ጀሊሉ አንተው እዘንልን፤
ወንጀላችን ማረን በእዝነት አይንህ እየን፤
መከራውም አልፎ ደስታውን አሳየን፤
በፍቅር ትቦርቅ ከደጇ ትቆየን፤
ህፃናት ይሩጡ ለጥ ባለው ሜዳ፤
አውጥተህ አሳየን ከስደቱ ጓዳ፤
የሱና ወንድሜ ከሀገር ርቋል፤
ጎጆ እንደሌለው ይሄው የትም ወድቋል፤
ከመስጂዱም ሸሸ ከቂርአት ማእድ፤
ምርጫው የግድ ሆነ ከሀገር መሰደድ፤
አንተው እዘንልን አዛኝ ነህ ምንግዜም፤
ወንድሜ ይመለስ ከሀገሩ ይክተም።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ምንም ብተነፍስ እርካታ አይሰማኝ፤
የምሰማው ወሬ ረመጥ ሆኖብኝ፤
ከውስጤ ተቀብሮ እያብሰለሰለኝ፤
መከራሽን ከማይ ክብርሽም ሲዋረድ፤
ደስስ ይለኝ ነበረ ከፊት ሆኜ ብነድ፤
ጥይት ቢበሳሳኝ አንገቴም ቢቀላ፤
ደረቴን በሰጠሁ ያንቺ ህይወት ቀጥላ፤
ደስ ይለኝ ነበረ እንደሻማ ብቀልጥ፤
ባንቺ ንፅህና ከማይስ ሲላገጥ፤
በፅኑ ብገረፍ በረሀብ አለንጋ፤
ያቺን የዋህ እናት ከማያት ጠውልጋ፤
አጥንት ከስጋው ተጣብቆ አንድ ላይ፤
እዝነቱን ከጅለው ዞሩ ወደ ሰማይ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
በጣም የገረመኝ ወሎ ምን አጠፋች፤
ከሌማቱ አጥፋ በፍቅር ባጎረሰች፤
ያጎረሰውን እጅ መንከስ ምን ይሉታል፤
አይንን በጨው አሽቶ የሰውን ልጅ መግደል፤
ይሄ የሰው አውሬ ወገን በላሽ ጭራቅ፤
ይጠፋል ከምንጩ አይቀርም ከመድረቅ።
ኢ ን ሻ አ ሏ ህ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
እኔ ግን በአሏህ እርግጠኛ ነኝ፤
በጭብጡ ወድቆ ፍርዱን እንደሚያገኝ፤
ስለዚህ እህቴ ሶብርን ሰንቂ፤
በፅናት ተውበሽ ከአሏህ ስር ውደቂ፤
ምንግዜም አያፍርም በሱ የተመካ፤
ከችግር በኃላ ይኖራል ሲፈካ፤
በመርከቡ እለፊ ፈተናውን ቀዝፈሽ፤
ኢማንሽም ይስበት በችግር ላይ አልፈሽ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ወሎ ለምለሚቷ የውበቷ ሙዳይ፤
ገራገር ደግነት ያስጌጡሽ አማላይ፤
ከመከራ ወጥተሽ ስትቦርቂ ልይሽ፤
በክፉ ያሰበሽ ይሁን አመድ አፋሽ፤
ጨለማው ይወገድ ብርሀን ይፈንጥቅ፤
ጉልበቱ ይብረክረክ ይበልልሽ ድቅቅ፤
የጠላትሽ ጡንቻ ይሁነው ቄጠማ፤
ድል ካንቺጋ ይሁን በፍልሚያው አውድማ።
https://t.me/AbuSarahh
https://t.me/AbuSarahh