🚫 የአሕባሽ ሙሪዶች ነፍሳችሁን አድኑ
አብዛኞቹ የአሕባሽ ሙሪዶች መሪዮቻቸው እንደሚሏቸው ወሀብዮች የነብዩን ዲን አጥፊዮች የዲን ጠላቶች ናቸው እነርሱን መግደል ዲንን መነሰር ነው ብለው ያስተምሯቸዋል ። በመሆኑም እነርሱን መጥላት በእነርሱ ላይ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ወደ አላህ ያቃርባል ብለው ያምናሉ ።
ለዚህ ነው እነርሱ ወሀብይ የሚሏቸውን ከልክ ያለፈ ጥላቻ የሚጠሏቸው ። እነርሱ ላይ የቻሉትን ጉዳት አድርሰው ወደ አላህ ለመቃረብ አመቺ ጊዜና ቦታ የሚጠባበቁት ‼።
ለእነዚህ ምስኪን አካላት የምለው ከዚህ የጥፋት አካሄድ ራሳችሁን አውጡ !!! ተውበት አድርጋችሁ ወደ አላህ ተመለሱ !!! መሪዮቻችሁ እውነት የነብዩ ዲን አሳስቧቸው አይደለም ።
ለዚህ በቂው ማስረጃ ከቁርኣንና ሐዲስ በፊት እናንተን ወደ ጥፋት የሚያሰልፏችሁ ዱንያዊ ጥቅም ባለባቸው መስጂዶች ላይ ነው ‼። ይህ ማለት ለጥቅም ብለው ነው ማለት ነው ። ከእነርሱ ወጪ የሚፈልግ መስጂድ አካባቢ ምንም ጭቅጭቅ የለም ።
እናንተ እያጠፉት ነው በምትሉት ዲን እይታ ስናየው የትኛው ኢስላም ነው ቀብር ማምለክ የሚያስተምረው ? የቱ የቁርኣን አንቀፅ ነው የሙታን መንፈስ ማምለክን የሚያስተምረው ? የቱ የነብዩ ሐዲስ ነው ወልይን መገዛት የሚፈቅደው ? እውነት ለእስልምና ከሆነ መቆርቆራችሁ ቆም ብላችሁ አስቡ ‼ አላህ ነብዩን የላከው ሙሽሪኩል ዐረብን ከቀብር አምልኮ አውጥተው ወደ አላህ አምልኮ እንዲያሸጋግሯቸው ነው ። ፍጡርን ከማምለክ ፈጣሪን ወደ ማምለክ ሊያሸጋግሯቸው ነው የላካቸው ። በሳቸውና በዐረብ አጋሪያን መካከል የነበረው ጥል ምክንያት አንገት ላንገት የተቀላሉበት ፣ ከሀዲና አማኝ ተብሎ የተለያዩበት የቀብር አምልኮ ነበር ። ቀብር ማምለክ ኩፍር ነው ። አላህን ማምለክ እስልምና ነው ። ቀብር ማምለክ ሽርክ ነው አላህን ማምለክ ተውሒድ ነው ። ወልይን ማምለክ የጀሀነም ያደርጋል ። አላህን ማምለክ የጀነት ያደርጋል ።
ነብዩ ደማቸው የፈሰሰው ፣ ጥርሳቸው የተሰበረው ፣ ክብራቸው የተነካው ፣ ሀገር ጥለው የተሰደዱት ለተውሒድ ብለው ነው ። ከሳቸው በኋላ ሶሓቦች አንገታቸው የተቀላው ፣ አጥንታቸው የተሰባበረው ፣ በየበረሀው ለአውሬ እራት የሆኑት መንገድ ላይ የቀሩት ጀናዛቸው አሞራ የበላው ለተውሒድ ብለው ነው ።
አሁን የናንተ መሪዎች ወሀብይ የሚሏቸው ወደ ተውሒድ የሚጣሩትን ፣ ወደ ቁርኣን የሚጣሩትን ፣ ወደ ነብዩ ሱና መተግበርና መከተል የሚጣሩትን ነው ። ነብዩን መውደድ የሳቸውን ትእዛዝ በመከተል እንጂ በማመፅ አይደለም የሚሉትን ነው ወሀብይ የሚሉት ። በመሆኑም ቆም ብላችሁ ፈትሹ !!!
የሚያጠጡዋችሁ የሽርክና ቢዳዓ ኸምር ስካሩ እያዳፋ ወደ ጀሀነም ነው የሚነዳችሁ ። ለራሳችሁ ስትሉ ወደ አላህ ተመለሱ !!! እስኪ አስቡት አላህን ብቻ ተገዙ ያላችሁን ገላችሁ ጀነት የምትገቡ ይመስላችኋል ? ጀነት የአላህ ነው ብላችሁ ነው የምታምኑት ወይስ በሸይኾቻችሁ እጅ ? በአላህ እጅ ነው የምትሉ ከሆነ አላህን ተገዙ የሚላችሁን ገላችሁ አላህ ጀነት የሚሰጣችሁ ይመስላችኋል ‼? ከርሱ የምትርቁ ወይስ ወደርሱ የምትቃረቡ ይመስላችኋል ? ቆም ብላችሁ አስቡ ለራሳችሁ ብላችሁ ተመለሱ !!! አላህ አጃኢበኛ ጌታ ነውና ተውበት አድርጋችሁ ከተመለሳችሁ ገዳይና ተገዳይን በጀነት ሊያገናኛችሁ ይችላል !!!!!! ።
የአሕባሽ መሪዮች የአላህን ባሮች አላህን ከማምለክ አውጥታችሁ እናንተን እንዲያመልኩ የአላህንና የነብዩን ትእዛዝ ጥሰው የናንተን ትእዛዝ እንዲያከብሩ አድርጋችሁ ወደ ጀሀነም እየነዳችኋቸው ነውና አላህ ፍሩ ። አላህ በዱንያም በአኼራም የውርደት ካባ ያለብሳችኋል ። ለናንተ ምክር እንደማይጠቅም ልባችሁ የነዋይ ጥማት እንዳሳወረው አውቃለሁ ግን አይታወቅምና አላህ ልቡን የሚከፍትለት ሊኖር ይችላልና አላህን ፍሩ እላለሁ ።
https://t.me/bahruteka