Репост из: ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️
ከመሬት መንቀጥቀጡ በኋላ...
----◉-----
ከበርናባስ በቀለ
አዲስ አበባና በዙሪያው የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የእኛንም ሰፈር ረብሾ ነበርና ሰው እየሮጠ ሲወጣ እኔና ቤተሰቤም ከቤታችን (ከሕንጻው) ወደ መሬት ስንወርድ ከለበስነው የምሽት (የቤት ውስጥ) ልብስና እጃችን ላይ ከያዝነው ስልክ ውጭ ምንም ይዘን አልወጣንም።
ከሰፈሩ ሕዝብ ጋር በውጭ ስንገናኝም ማንም ምንም አልያዘም፤ ሁሉም ራሱን ብቻ ይዞ! ባዶ እጁን። ሁሉም እኩል በውጭ ባለ ሜዳ ተሰብሷል፤ ድሃ የለ፣ ሃብታም የለ! ባለ ሥልጣን የለ... ወዛደር የለ.. ሁሉም በምሽት ልብሱና በነጠላ ጫማው!
ሕይወት ይህችው ናት። በመጨረሻም የምታስመልጡት ራሳችሁንና ራሳችሁን ብቻ ነው። ያከማቻችሁት የእናንተ አይደለም፤ እጃችሁም ያለው እናንተን (ራሳችሁን) አይደለም። እናንተ ማለት ይዛችሁ የወጣችሁት ማንነታችሁ ነው። በዚያ ሰዓት ዘር፣ ዝና.. ታዋቂነት እና አዋቂነት አይሠሩም። ሁሉም እኩል! አለኝ የምትለው በፍጻሜ የአንተ አይደለምና ይዘኸው መሸሸ የቻልኸው ራስህን (አንተነትህን) በትኩረት እይ! ትምክህትም አለኝ በምትለው አይሁን፤ ከደቂቃዎች በፊት የተፈጠረው ክስተት አለኝ የምትለው እንደማይከተልህ አስተውለሃልና።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊