የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ "ከሰሞኑን ጉንፋን መሰል ነገር" ተጠንቀቁ ብሏችኋል!!!
ሰሞኑን በስፋት የሚስተዋለውን ጉንፋን መሰል በሽታ ለመከላከል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮ ለኢፕድ እንደገለጸው " ከሰሞኑ በስፋት የተከሰተው የጉንፋን በሽታ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነው " ብሏል።
በሽታውን ለመከላከልና እንዳይስፋፋ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ሲልም አሳስቧል።
የተከሰተው ጉንፋን መሰል በሽታ በዋነኝነት በተለይ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረሶች አማካኝነት የሚከሰት መሆኑን ገልጾ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም ፦
- አፍንጫን፣
- ጉሮሮን
- የአየር መተላለፊያ ባንቧን እንደሚያጠቃ ቢሮው አመልክቷል።
ከወቅታዊው የቅዝቃዜና ደረቅ የአየር ፀባይ ጋር ተያይዞ ለቫይረሶች ምቹ የመራቢያ ወቅት በመሆኑ በስፋት የሚሰራጭ መሆኑ ተጠቅሷል።
ትምህርት ቤቶችና ክረምቱን ተከትሎ የሚዘጉ የሥራ ተቋማት በመከፈታቸው የሰዎች ግንኙነት ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ስርጭቱ የጨመረ መሆኑ ተመላክቷል።
° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታት፣
° ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ከፍተኛ ድካም፣
° ብርድ ብርድ ማለት፣
° የትንፋሽ ማጠር እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ምልክቶች ናቸዉ ተብሏል።
ቫይረሱ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በቫይረሱ የተጠቃ ግለሰብ በሚያስልበት እና በሚያስነጥስበት ጊዜ ከሚወጡ ጠብታዎች ጋር ንክኪ፣ ቫይረሱ ያረፈበትን ቁሳቁስ ንክኪ ማድረግ ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች ናቸው።
በመሆኑም ፦
🔴 የእጅና የቁሳቁስ ንጽህናን በመጠበቅ፣
🔴 ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል በማድረግ፣
🔴 ስፖርታዊ እንቅስቃዜን ማዘወትር፣
🔴 መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር ማድረግ
🔴 በቂ የጸሀይ ብርሀን ማግኘትና አትክልትና ፍራፍሬ በመመገብ በሽታውን መከላከል እንደሚገባ ቢሮው ገልጿል።
በሽታው በሁሉም ሰው ላይ የሚከሰት ቢሆንም በተለይም እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት፣ አዛውንቶችና እና ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ የሚጠነክር በመሆኑም በትኩረት መከላከልና ከተያዙ አስፈላጊው ክትትልና የህክምና ድጋፍ ሊያገኙ ይገባል ሲል አሳስቧል።
በመከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ማድረግ በሽታውን ከመከላከል ጀምሮ በህመሙ ከተያዙ በቤት ውስጥ ከሚደረጉ ክትትሎች እና ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት ይገባል ተብሏል።
#EPA