በካዛንችስ እና አዋሬ ፥ ከህንፃዎች እና አንዳንድ በደንብ ከተያዙ መኖርያ ቤቶች በቀር ሁሉም ፈራሽ ናቸው መባሉ ተሰማ
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አመራሮች ባሳለፍነው ሳምንት ካዛንችስ ተገኝተው ነዋሪዎችን ባነጋገሩበት ወቅት ካዛንችስ እና አዋሬ ውስጥ ከህንፃዎች እና አንዳንድ በደንብ ከተያዙ መኖርያ ቤቶች በቀር ሁሉም ፈራሽ መሆናቸው እንደተነገራቸው ዳጉ ጆርናል ከመሠረት ሚዲያ ሰምቷል። ይህን የሚያስረዳ የድምፅ ሪከርድ ደርሶኛል ሲልም የዜና ምንጩ ዘግቧል።
ከበርካታ ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው በቅርብ ቀናት ካዛንችስ ከስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ጀርባ ያለው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
"መቼ እንደሚፈርስ ግን ትክክለኛው ግዜ አልተነገረንም" ያሉት ነዋሪዎቹ ይህም "እንቅልፍ ነስቶናል፣ ከዛሬ ነገ መጥተው ውጡ ሊሉን ይችላል" ብለው ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል።
Via መሠረት ሚዲያ
@Abbay_media☑️