የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ5 ቢሊየን ፓውንድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ5 ቢሊየን ፓውንድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።
ከአዲስ አበባ በ25 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ አቅራቢያ የሚገኘው ይህ የወደፊት አየር ማረፊያ በ2029 ሲጠናቀቅ እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን በዓመት የሚያስተናግድ ትልቅ ተርሚናል እና አራት ማኮብኮቢያዎችን ይይዛል ተብሏል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዳር አል ሀንዳሳ አማካሪዎች ጋር በመተባበር የሚመራው ይህ የ5 ቢሊዮን ፓውንድ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ዋና ተዋናይ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል።
በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መጨናነቅ ቢያጋጥመውም "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ይህን ችግር በመቅረፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ያሳድጋልም ተብሎለታል።
Via: አዲስ ማለዳ
@Addis_Mereja