የጅቡቲ ፖሊስ የሰነድ አልባ ስደተኞች አፈሳ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
የጅቡቲ ፖሊስ ትናንት ምሽት "ህገወጥ ስደትን መከላከል" በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፣ ትናንትና ጠዋት መጠነ ሰፊ የሆነ የሰነድ አልባ ስደተኞች አፈሳ መጀመሩን ገለጿል።
የአፈሳ ዘመቻው የተጀመረውም ሰነድ አልባ ስደተኞች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ከአንድ ወር በፊት በሀገሪቱ መንግስት የተሰጠው ቀነገደብ በመጠናቀቁ እንደሆነ ጠቅሷል።
በትናንትናው ዕለት የሀገሪቱ ብሔራዊ ፖሊስና የድንበር ጥበቃ የደህንነት ጥምር ግብረ ሀይል፣ በተለይም የአደገኛ ዕፅ ዝውውር በሚበዛባቸው አካባቢዎች አፈሳ መጀመሩን መግለጫው አስታውቋል፡፡
የህገወጥ ስደተኞች ቁልፍ መተላለፊያና ማረፊያዎች ናቸው በተባሉ የሀገሪቱ አካባቢዎችም አፈሳው መከናወኑን አመልክቷል፡፡
በአሰሳና አፈሳ ዘመቻው፣ ህገወጥ ስደተኞች የሚገኙባቸውን አካባቢዎች ለመለየት ድሮኖች ጥቅም ላይ መዋላቸውንም ገልጿል።
ቀደም ሲል የተሰጠው የአንድ ወር ጊዜ ቀነገደብ ሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ መንግስት በቅርብ ቀናት ውስጥ መጠነ ሰፊ የሰነድ አልባ ስደተኞች አፈሳ እንደሚጀመር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
@Addis_Reporter @Addis_Reporter