Postlar filtri




part 3


part 2




የአል-ዓፊያ ት/ቤቶች ማህበረሰብ_Al-Afia Community dan repost
ይመዝገቡ!

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና #በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ #የግል አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ አድርጉ!

ከዚህ ቀደም በመደበኛ ፕሮግራም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ያላመጣችሁና ፈተናውን በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ የግል አመልካቾች ምዝገባ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

https://register.eaes.et/Online ሊንክ ላይ በመግባት Apply Now የሚለውን ይጫኑ፤ የሚመጣላችሁን ቅፅ በጥንቃቄ ይሙሉ፤ አስፈላጊ ሰነዶችን ይጫኑ፤ የምዝገባ ክፍያ ብር 750 ክፍያ በመፈጸም ምዝገባዎትን ያከናውኑ፡፡

ምዝገባው የሚያበቃው 👇
ማክሰኞ ጥር 20/2017 ዓ.ም

በምዝገባ ሒደቱ ማንኛውም ድጋፍ ቢያስፈልግዎ ከላይ በምስሉ ላይ በተጠቀሱት የስልክ ቁጥሮች በመደወል ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡

@tikvahuniversity


በፈተና ሰሞን ለልጆች የሚደረግን ድጋፍ ማጠናከር

እንደሚታወቀው ልጆች ከጨቅለነታቸው ጊዜ ጀምሮ ፈተና ላቀ ስፍራ እንዳለው በተደጋጋሚ የሚሰሙበት አጋጣሚ በርካታ ነው፡፡ ለዚህም ተገቢውን ዝግጅትና ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ከየአቅጣጫው ይነገራቸዋል፡፡

መረጃዎች እነደሚያሳዩት በርካታ ቁጥር ያላቸው ልጆች ፈተና የሚያስከትልባቸው መጨናነቅ ከልክ በላይ ሲሆን ለከፍተኛ ጭንቀት እና ጤና መታወክ ይዳረጋሉ፡፡ይኸውም የፈተና ሰሞን ውጥረት በጊዜ ተረድቶ በወጉ መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ወላጆች ልጆች በፈተና ሰሞን የሚገጥማቸውን ውጥረትና የመጨናነቅ ስሜት ለመቆጣጠር ባላቸው ሚና (role) በመታገዝ ልጆች የዚህ አስከፊ ችግር ሰለባ እንዳይሆኑ ጭምር መርዳት እና ማገዝ ይቻላሉ፤ ይጠበቅባቸዋልም፡፡

ወላጆች ከማንም በላይ ልጆችን በተሻለ ቅርበት የማግኘት ዕድሉ ስላላቸው በፈተና ሰሞን በልጆች ላይ የሚስተዋልን ውጥረትና ጭንቀት ለመቆጣጠር ሚናቸው የገዘፈ ነው፡፡ወላጆች በፈተና ሰሞን ልጆች በቤት ውስጥ ሳሉ ሲያጠኑ ሊከሰት የሚችልን ውጥረትና ጭንቀት መቆጣጠር እንዳለባቸው መረዳትና በዚህ የተነሳ ለከፋ ችግር እንዳጋለጡ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አለባቸው፡፡፡፡

ልጆች በፈተና ሰሞን የሚሰማቸውን ጭንቀትና የውጥረት ስሜት እንዲቆጣጠሩ ወላጆች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ተግባራት መካከል የተወሰኑትን እንመልከት፡-

ልጆችዎ እነዲያጠኑ ይርዷቸው
ወላጆች በማስጠናት አሊያም ለጥናት የሚሆኑ አመቺ አካባቢን በማመቻቸት ልጆች ሳይረበሹ በርትተው እንዲያጠኑ ሊረዷቸው ይገባል፡፡

በፈተና ሰሞን ልጆችዎን ካሉባቸው ሃላፊነቶች ይቀንሱላቸው

ሁላችንም እነደምንረዳው ፈተና በልጆች ላይ ጠንከር ያለ ጫና ይፈጥርባቸዋል፡፡በዚህን ጊዜ ልጆች በቤት ውስጥ በሚከናወኑ በርካታ ሃላፊነቶች እንዳይጠመዱ ወላጆች የተቻለንን ሁሉ ለልጆቻችን ልናደርግ ይገባል፡፡በተለይ በፈተና ሰሞን ከልጆች ጋር የሚከሰት ያለመግባባት ልጆች ላይ የከፋ የአዕምሮ ውጥረት ሊየስከትል ስለሚችል ይህን መሰል ስሜት በልጆች ላይ ከሚፈጥር ተግባርና ንግግር አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡

ልጆችዎ ጥናታቸውን በዕቅድ እንዲያካሂዱ ይርዷቸው

በፈተና ሰሞን ልጆችዎ የሚያደርጉት የፈተና ዝግጅት (ጥናት) በዕቅድ የተመራ ይሆን ዘንድ ይተባበሯቸው፡፡ ከዚያም በወጣው የጥናት ፕሮግራም መሰረት ልጆችዎ ለፈተና ተገቢውን ዝግጅት እያደረጉ ስለመሆናቸው መቆጣጠር እንዲሁ የእርሶ ድርሻና ኃላፊነት ነው፡፡

የልጆችዎ የፈተና ዝግጅት (ጥናት) ከመጠን ያለፈ እንዳይሆን ተገቢውን ክትትል ያድርጉ

ልጆች በፈተና ሰሞን ውጥረት ውስጥ ሲገቡና ከልክ በላይ ሲጨንቃቸው የሚያደርጉትን ጥናት ማመጣጠን ይቸግራቸዋል፡፡ጤናማ ከሆነው በላይ ጥናት ሊገቡም ይችላሉ፡፡ በዕርግጥ ልጆችዎ በተለይ በፈተና ሰሞን ማጥናት እንዳለባቸው ምንም ጥርጥር የለውም ፡፡ ሆኖም ግን ጥናቱ (የፈተናው ዝግጅት) ያስከተለው ጫና ልጆችዎ አዕምሯቸውን የሚያዝናኑባቸውን ተግባራት ሁሉ አስወግደው የፈተና ግዞተኛ አድርጎ ሊያስቀር አይገባም፡፡

ለልጆችዎ ነፋሻ እና ንጹህ አየር የሚገኝበትን ሁኔታዎች ያመቻቹ

ነፋሻና ንጹህ አየር እንዲሁም የፀሀይ ብርሃን ልጆች በፈተና ሰሞን የሚያጋጥማቸውን ውጥረትና ጭንቀት እነዲቆጣጠሩ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታል፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች ልጆች መልካም ስሜት እንዲሰማቸው ያግዛቸዋል፡፡ እናም በፈተና ሰሞን ነፋሻ አየር እና የፀሀይ ብርሃን ልጆችዎ በበቂ ሁኔታ ስለማግኘታቸው እርግጠኛ ይሁኑ፡፡

ልጆችዎ ተገቢ የሆነ የአካል ብቃት (ስፖርታዊ) እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ይከታተሉ፡፡

ለረጅም ጊዜ ሳይንቀሳቀሱ በአንድ ቦታ ተቀምጦ መቆየት  ወደ አካልም ሆነ አዕምሮ ጤናማ ያልሆኑ ስሜቶችን ይጋብዛል፡፡ ይህም ልጅዎች የሚያደርጉት የፈተና ዝግጅትን በንቃት አንዳያከናውኑ ተጽዕኖ ሊያደርግ ይችላል፡፡  ስለዚህ ወላጆች ልጆቻቸው በፈተና ሰሞን በሚያጠኑበት ወቅት ተገቢውን የአካል እንቅስቃሴ ያደርጉ ዘንድ በሚገባ ማበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡

የልጆችዎን የአመጋገብ ስርዓት ይከታተሉ

ልጆች በፈተና ሰሞን የሚገጥማቸው ውጥረት እና  መጨናነቅ እየከፋ ሲሄድ ፈተና ዝግጅቱ ላይ ይበልጥ ትኩረት ለማድረግ ካላቸው ጉጉት የተነሳ ከምግብ ጭምር ሊዘናጉ አንዳንዴም ሆን ብለው ለረጅም ጊዜ መታቀብን ሊመርጡ ያችላሉ፡፡ይህ ደግሞ በአግባቡ እንዳያጠኑ ብቻ ሳይሆን በፈተና ሰሞን የሚገጥማቸውን  ውጥረትና ጭንቀት የመቆጣጠር አቅማቸውን ሊያዳክምባቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም ወላጆች ልጆቻቸው በፈተና ዝግጅት ላይ ሳሉ ተገቢውን የተመጣጠነ ምግብ በተገቢው ሰዓት የሚያገኙባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ሲሆን ልጆች ለፈተናው የሚያደርጉትን ጥናት በተሻለ አቅምና የመንፈስ ብርታት ማካሄድ ይችላሉ፤ውጤታማም ይሆናሉ፡፡

ልጆችዎን በተገቢ መልኩ ያበረታቱ

ልጆች በፈተና ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ የሚደረግ ማበረታቻ ተገቢ ነው፡፡ ሆኖም ልጆች በጥናት ይጎብዙ ዘንድ የሚደረግ ከመጠን ያለፈ የማበረታቻ ጋጋታ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ስለሚችል ተገቢውን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡

በሚያበረታቱበትም ጊዜ ቢሆን ወላጆች ልጆች ላይ የሚያደርጉት አሉታዊ (negative) ተፅእኖ ልጆች በፈተና ሰሞን የሚሰማቸውን ውጥረትና ጭንቀት ለመቆጣጠር አይጠቅማቸውም፤ቢያባብሰው እንጂ፡፡

ስለዚህ ወላጆች ልጆችን በትክክል የማበረታታት አግባብ እንዴት ያለ እንደሆነ ሊረዱት ይገባል፡፡“ልጄ አጥንቶ ጥሩ ውጤት ሊያመጣ ይገባል፡፡” ከሚል ወላጃዊ ስሜት ብቻ ተነሳስተው ልጆች ላይ በተለይ በፈተና ሰሞን ተገቢ ያልሆነ ጫና ማሳደራቸው ጉዳቱ የከፋ ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ እኛም ወላጆች ይህን ከማድረግ ልንቆጠብና ሚዛናዊ ልንሆን ይገባል ስንል ለዛሬ ያዘጋጀነውን በፈተና ዝግጅት ላይ ያተኮረ ወቅታዊ መልዕክት በዚህ እንቋጫለን፡፡

ውድ ተማሪዎቻችን ፡-
በመንፈቀ- ዓመቱ ላሳያችሁት መልካም ስነ-ምግባር እንዲሁም ንቁ የትምህርት ተሳትፎ ከልብ እናመሰግናለን
መልካም የጥናት ጊዜ!! መልካም ውጤት !!!


ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች፦

የማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥበት መርሃግብር በየቅርንጫፎቹ በወላጅ መምህር መጽሀፍ በሚላከው መልዕክት መሰረት ይሆናል::

በመርሀግብሩ መሰረት ተማሪዎች ለፈተና እንድታዘጋጃዎቸው በድጋሚ እናስታውሳለን።


ለፈተና የሚጠቅሙ ምክሮች

ውድና የተከበራችሁ የት/ቤቶቻቸን ወላጆች/አሳዳጊዎች

የትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያ መንፈቀ-ዓመት የትምህርት መርኃግብር  ተጠናቆ የ2017 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ መንፈቀ-ዓመት ማጠቃለያ ፈተና  ሐሙስ፣ ጥር 15/2017 መውሰድ ይጀምራሉ፡፡
እኛም ለዛሬው ሳምንታዊ መልዕክታችን ለፈተና የሚጠቅሙ አንዳንድ ጠቃሚ ነጥቦች ማስታወስ እንዲሆን መርጠናል፡፡
መረጃውን ከብርቲሽ ካውንስል ያገኘነው ሲሆን በመጠኑ አሻሽለን እንደሚከተለው አቅርበንላችኃል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

ፈተና በጣም የተረጋጉ በሚባሉ ተማሪዎችም ላይ ሳይቀር ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል። ይሁንና የተወሰነ ዝግጅት በማድረግና የታሰበበት ፕሮግራም አውጥቶ ትምህርቱን በመከለስ ተማሪዎች የሚገባቸውን ውጤት ማግኘት ይችላሉ።

የፈተናው ቀን ከመድረሱ በፊትተማሪዎች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፦

ተማሪዎች አሁን ክለሳ የሚያደርጉበትን ፕሮግራም ስለማውጣት በቁም ነገር ማሰብ መጀመር ይኖርባቸዋል።

የሚከተሉትን ነገሮች ያድርጉ፦
➡️ ፈተናውን በተመለከተ አንዳንድ መረጃዎች ለማግኘት ይሞክሩ (ለምሳሌ ያህል ጥያቄዎቹ ምርጫ ናቸው ወይስ በተጻፉ ነገሮች ላይ የተመሠረቱ?)
➡️ክለሣ የሚያደርጉበትን ፕሮግራም ያዘጋጁ።

ለክለሣ የሚጠቅሙ አንዳንድ ሐሳቦች፦

ተማሪዎች የተማሩትን የሚከልሱበት ፕሮግራም ሲያወጡ ከቀኑ ውስጥ ይበልጥ ውጤታማ የሚሆኑበትን ጊዜ ይምረጡ። ለምሳሌ ያህል ጠዋት ላይ ቀለል የሚላቸውና ነቃ የሚሉ ከሆነ ሰፊ ጊዜ መድበው ከማጥናት ወደኋላ አይበሉ። ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ለማድረግም ጥረት ያድርጉ፦

➡️በአንድ የትምህርት ዓይነት ብዙ ነጥብ ለሚይዙ የፈተና ዓይነቶች ቅድሚያ ይስጡ፣
➡️ አእምሯቸውን ለማደስ አዘውትረው የተወሰነ እረፍት ያድርጉ፣
➡️ መጽሐፎችን በድምፅ የተቀዱ መመሪያዎችንና  ለማጥናት የሚረዱ የተለያዩ ዝግጅቶችን ተጠቅመው ትምህርቱን ይከልሱ፣
➡️ ሲያጠኑ በያዙት ማስታወሻ ላይ ቁልፍ ነጥቦችን ያስምሩባቸው፣
➡️ ከእያንዳንዱ ርዕስ ጋር በተያያዘ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ የሆነ ሰው ጥያቄዎች እንዲጠይቃቸው ያድርጉ፣
➡️ የጥያቄዎቹን ዓይነትና የሚመደበውን ሰዓት በተመለከተ ግንዛቤ ማግኘት እንዲችሉ የድሮ ፈተናዎችን ይሥሩ፣
➡️ ከቤተሰብ ጋር ዘና የሚሉበት ጊዜ ይመድቡ።

ለፈተና ቀን የሚጠቅሙ ሐሳቦች

እንግዲህ ተማሪዎች ጥናታቸውንና ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ለቁርጥ ቀን ተዘጋጅተዋል። የመረበሽ ስሜት ቢሰማቸው ግራ እንዳይጋቡ፤ ይሄ ያለ ነገር እንደሆነ ሊረዱት ይገባል።ዘና ለማለትና በተቻለ መጠን ጥሩ ውጤት ለማምጣት ተማሪዎች የሚከተሉትን ጥቂት ተጨማሪ ምክሮች ተግባራዊ ያድርጉ፦

➡️ ለመረጋጋት ይሞክሩ እንዲሁም ደጋግመው በደንብ ይተንፍሱ፣
➡️ ፈተናውን መሥራት ከመጀመር በፊት የጥያቄ ወረቀቱን ከዳር እስከ ዳር ያንብቡ፣
➡️ የተመደበውን ጊዜ ይከፋፍሉ፣
ከባድ ጥያቄ ሲያጋጥም ወደሚቀጥለው ይለፉ፣
➡️ ጥያቄዎቹን በጥሞና ያንብቡ፣ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ትክክለኛ መልስ መስጠታቸውን እርግጠኛ ይሁኑ፣
በተለይ ፈተናውን በጊዜ ሠርተው ከጨረሱ የጻፏቸውን መልሶች ተመልሰው ይመልከቱ።

በመጨረሻም ወላጆች  ልጆቻችሁ የሚያደርጉትን የክለሳና የፈተና ዝግጅት ከላይ የቀረቡትን እና ሌሎችን ጠቃሚ ነጥቦች በማጋራት እና በመምከር ከሌላው ጊዜ በተሻለ ማገዝ እና ማበረታታት ተገቢ መሆኑን በድጋሚ በማስታወስ የዛሬውን ሳምንታዊ  መልዕክት እናጠናቅቃለን፡፡


7 BEST WAYS TO RAISE DISCIPLINED CHILDREN

Parenting is a journey filled with both joys and challenges. One of the most significant challenges parents face is disciplining their children. Traditional methods of punishment often lead to negative outcomes, such as resentment, fear, and a damaged parent-child relationship. Sarah’s Gentle Discipline offers a refreshing approach to parenting, emphasizing emotional connection and positive reinforcement over punishment

Dear parents:
Today, for our weekly message, we have chosen the following seven key lessons and insights from the book, "Gentle Discipline," Enjoy reading the seven points and try them in disciplining your children:

1. The Power of Connection
At the heart of gentle discipline is a strong emotional connection between parent and child. By building a bond of trust and understanding, parents can guide their children's behavior effectively. This connection fosters a sense of security and belonging, making children more receptive to guidance and less likely to misbehave.

2. Understanding Child Development
To effectively discipline children, it's essential to understand their developmental stages. By recognizing the cognitive, emotional, and social milestones of each age group, parents can tailor their approach to meet their child's specific needs. This understanding helps parents respond to challenging behaviors with empathy and patience.

3. The Importance of Positive Reinforcement
Positive reinforcement is a powerful tool for shaping children's behavior. By acknowledging and rewarding positive actions, parents can encourage desired behaviors and strengthen the parent-child bond. This approach is more effective than punishment, as it motivates children to repeat positive behaviors.

4. The Art of Effective Communication
Effective communication is crucial for gentle discipline. Parents should use clear, concise language to explain expectations and the consequences of negative behavior. Active listening is also essential, as it allows parents to understand their child's perspective and address their needs.

5. Setting Limits and Boundaries
While gentle discipline emphasizes positive reinforcement, it's still important to set clear limits and boundaries. Children need structure and consistency to feel safe and secure. By establishing clear expectations, parents can help children develop self-discipline and responsibility.

6. The Role of Empathy
Empathy is the ability to understand and share the feelings of another person. By empathizing with their child's emotions, parents can respond to challenging behaviors with compassion and understanding. This approach helps children feel heard and validated, reducing the likelihood of future misbehavior.

7. The Power of Self-Reflection
Gentle discipline is not just about changing our children's behavior; it's also about transforming ourselves as parents. By reflecting on our own emotions, triggers, and parenting style, we can become more mindful and responsive parents. Self-reflection allows us to grow and evolve as individuals and as parents.

Gentle Discipline is a valuable resource for parents seeking to raise confident, capable, and kind children. By embracing the principles of emotional connection, positive reinforcement, and empathy, parents can create a nurturing and supportive environment for their children to thrive.


TIKVAH-ETHIOPIA dan repost
#NationalExam : የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ምዝገባቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድመው እንዲያጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፈተና ይዘትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ተገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ ዘንድሮ በመደበኛው እና በግል 750,000 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ  ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

እስካለፈው ሳምንት ባለው ዳታ ወደ 500 ሺህ  ተማሪዎች ተመዝግበል።

በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ባለው 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ አከናውነዋል ፤ በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።

ኢንተርኔት ማይሰራበት ቦታ ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን እየተጫነ ነው።

የመረጃ ባለቤቶች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ኤፍኤምሲ መሆናቸውን እንገልጸለን።

@tikvahethiopia


እናመሰግናለን!!!
ሹክረን!!!

ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች፡-
“ሪድ አል-አፊያ” በሚል መሪ ቃል ለወራት በተሻለ እንቅስቃሴ ሲካሄድ የቆየው የ 2017 የንባብ ዘመቻ በሁሉም ካንፓሶቻችን በተለያዩ ንባብ ተኮር መርሃግብሮች በከፍተኛ ድምቀት በዚህ ሳምንት ተጠናቋል፡፡ እኛም የዚህ ሳምንት መልዕክታችን ስለንባብ እንዲሆን መርጠናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

በኣረብኛ አል-ኢልሙ ፊ ሲገር ከነቅሹ አለል ሃጀር ማለትም በልጅነት የሚቀሰም ዕውቀት እንደ ድንጋይ ላይ ፅሁፍ ነው ይባላል ፡፡ ንባብ ደግሞ ሁላችንም እንደምናውቀው የዕውቀት መግቢያ በር ነው፡፡ ልጆቻችን በንባብ ሲጠነክሩ የተሻለ ዕውቀት ይሰንቃሉ፤በዚህም የአስተሳሰብ አድማሳቸው እየሰፋ ይሄዳል፡፡ በዚያው መጠንም የሚኖራቸው ተቀባይነት እንዲሁም ተፅእኖ ፈጣሪነት እያደገ ይሄዳል፡፡ ለዚህም ነው ብዙውን ጊዜ አንባቢዎች መሪዎች ናቸው የሚባለው፡፡

ዓመታዊ የንባብ ዘመቻ በአል-ዓፊያ ት/ቤቶች የትምህርት ፅ/ቤት ስር በሚገኘው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲፓርትመንት አማካኝነት በ2016 በይፋ የተጀመረ ሲሆን ለ2ተኛ ጊዜ በ2017ም በተሻለ ሁኔታ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ለማካሄድ ተሞክሯል፡፡

በተለይ በዚህ ዓመት  በመንግስት ትምህርት ቢሮ በቅድመ-መደበኛ (ኬጂ) ጭምር የንባብ እንቅስቃሴው እንዲጀመር በሰርኩላር ደረጃ መውረዱ የንባብ ክህሎት ከስር ከመሰረቱ መጀመር እንደሚገባው ያረጋገጠ እንዲሁም ተቋማችን በዚህ ረገድ አንድ እርምጃ ወደፊት ቀድሞ መሄዱን ያመላከተ ልዩ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡

ሁላችንም ተማሪዎቻችን ማንበብ እንዲወዱ የመርዳት ፍላጎት አለን። ስለዚህ  ሁላችንም ይህንን ግብ ማሳካትይኖርብናል። ይህን ከባድ ሥራ ትምህርት ቤት በአመታዊ የንባብ ዘመቻ ብቻውን ሊወጣው አይችልም። ተማሪዎች ማንበብ ለመማር የሚያደርጉትን ጥረት ማህበረሰቡ እንዲደግፍ እንፈልጋለን። ወላጆች ልጆችን እንዲያበረታቱና እንዲያግዙ እንፈልጋለን። ወላጆች ለማንበብ፣ ሞዴል ንባቦችን ለማቅረብ የሚያግዙ ተግባራትንና ቦታዎችን በማመቻቸት እንዲተባበሩ እንፈልጋለን።ወላጆች/አሳዳጊዎች ተማሪዎች ጥሩ አንባቢ እንዲሆኑ እንዲያግዙና አቅጣጫ እንዲያመላክቱ እንፈልጋለን።

በዚህ መሰረት ወላጆች/አሳዳጊዎች  ልጆቻችንን ዛሬ ባሉበት ዕድሜ ክልል ይህንን መሰረታዊ የስኬት ቁልፍ የሆነ ክህሎት( ንባብ)  ፍላጎት እንዲኖራቸው በማበረታት እና ሁኔታዎችን በማመቻቸት ልጆች አንባቢ ሆነው እንዲታነፁ የድርሻችንን ኃላፊነት መወጣት ከቻልን በዕርግጥም የላቀ ውለታ ውለናቸዋል፡፡ ምክንያቱም ከላይ ቀደም ብሎ እንደተጠቆመው ልጆች ብዙ ባነበቡ ቁጥር የዕውቀት አድማሳቸው እየሰፋ ይሄዳል ፡፡ ይህም በትምህርታቸው ጎበዝ ፤በስነ-ምግባራቸውም እየተመሰገኑ ሆነው እንዲታነፁ ብሎም ወደፊት ኃላፊነት የመሸከም ብቃታቸው ክፍ እንዲል በእጅጉ ያግዛቸዋል፡፡

ከናንተ ጋር በአንድ ላይ ሆነን ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ልጆቻችን ስኬታማ አንባቢዎች እንዲሆኑ ማብቃት እንችላለን።  በመሆኑም ልጆች ገና ናቸው ብለን ሳንዘናጋ ከወዲሁ በዕድሜያቸው ልክ የንባብ ፍላጎት ማስረፅ ይቻል ዘንድ የተጀመረው የጋራ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥል!! እንዲሁም በዚህ ሳምንት የተጠናቀቀው በት/ቤቱ ሲካሄድ የቆየው ዓመታዊ የንባብ  ዘመቻ እንጂ ንባብ አለመሆኑን ሳንታክት ለልጆቻችን እናስታውስ!! እንምከር!! እናስረዳ!!

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፣አንባቢዎች አሸናፊዎች ናቸው፤አሸናፊዎችም አንባቢዎች  ናቸው፣የማያነብ ሰው መስኮት እንደሌለው ቤት ነው ይባላል እና እኛ እያነበብን ለልጆቻችን አርአያ በመሆን አንባቢ ትውልድ በማፍራት ልጆቻችን  የዕውቀት ጉዞዋቸው የተሳካ ይሆን ዘነድ የድርሻችንን እንወጣ!!  

ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች
እናንተም “ስለልጄ የንባብ ክህሎት መዳበር የድርሻዬን እወጣለሁ” በሚል ለልጆቻችሁ የተለያዩ መፅሀፍት በመግዛት፣ሰዓት መድባችሁም በማገዝና በማበረታታት እንዲሁም  ንባብን የሚያግዙ ሁኔታዎችንም በማመቻቸት ብሎም ንባብን ለማጎልበት ስንልክላችሁ የነበሩ መልዕክቶችን በሚገባ ተግባራዊ  በማድረግ ከት/ቤቶቻችን እንዲሁም ከመምህራኑ ጋር በመወያየት ጭምር የንባብ አርአያ በመሆን፤ ከዚህ ባሻገር በት/ቤቶቻችን ንባብ ማጠቃለያ ፕሮግራም መድረኮች እንድትገኙ የቀረበላችሁን ጥሪ አክብራችሁ በመገኘትና ስለንባብ አስፈላጊነት ገንቢ እና አነቃቂ መልዕክቶች በማቅረብ ለንባብ ዘመቻው ስኬታማነት ላሳያችሁት ቁርጠኝነትና ቀና ትብብር  ሁሉ በመላው የትቤታችን ማህበረሰብ ስም እጅግ አድርገን ከልብ እናመሰግናለን!!! ሹክረን!! በማለት የዛሬውን ሳምንታዊ መልዕክታችንን እንቋጫለን፡፡


ልጃችን ኢብቲሳም ዳግም ዛሬም ድል አደረገች !!!
በኮልፊ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት በተካሄደው ከ11 ወረዳ አሸናፊ ሁነው በመጡ ተማሪዎች መካከል በዛሬው እለት በተካሄደው የጥያቂና መልስ ውድድር ላይ ተማሪ ኢብቲሳም አብዱልበር 3ኛ ወጣች፡፡ ውድድሩ ከፍተኛ ፎክክር የነበረበት የተወዳዳሪ ተማሪዎች አቅም የታየበት እንደመሆኑ መጠን ተማሪ ኢብቲሳም ያላትን አቅም ለተወዳዳሪዎ ያሳየችበት ነበር፡፡
ለመላው የአል-ዓፊያ ት/ቤት ማህበረስብ እንኳን ደስ አላችሁ!!! አለን!!!


#ጥቆማ

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩና የ " 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ " ስልጠናዎችን ለመሰልጠን ላሰቡ ጥሩ እድል መመቻቸቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አሳውቋል።

ስልጠናዎቹን ለመውሰድ ለሚመጡ ሰልጣኞች የኮምፒውተር እና ኢንተርኔት አቅርቦት ዝግጁ መደረጉ ተጠቁሟል።

የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ እንዲመዘገቡም ጥሪ ቀርቧል።

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ የመንግስትና የግል ሰራተኞች፣ በአጠቃላይ ሁሉም ዜጎች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ ስልጠናዎችን መሰልጠን ይችላሉ ተብሏል።

ስልጠናው ከጥር 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሁልጊዜ በሳምንቱ የእረፍት ቀናት (ቅዳሜና እሁድ) እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የስልጠና ቀናት
#ቅዳሜ እና #እሁድ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ አመሻሽ 11:30 እንደሆነ ተመላክቷል።

የስልጠና ቦታው አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ቢሮ ሲሆን ለመመዝገብ ይህን ሊንክ 
https://awareness.insa.gov.et/index.php/143154?lang=am መጠቀም ይቻላል ተብሏል።

@tikvahethiopia


እንግሊዝኛ ቋንቋን መልመድ የሚቻለው እንዴት ነው?

ውድ ወላጆች፡-

የምርምር ጥናት እንደሚያሳየው: በልጅነት እድሜ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋዎችን መማር፤ለአእምሮ መዳበር ይረዳል፡፡ ከአንድ ቋንቋ በላይ መናገር የልጆችን አእምሮ ያዳብራል። እንዲሁም በበለጠ የፈጠራ አስተሳሰብ እንዲኖራቸውና ለችግሮች በቀላሉ መፍትሄ ማግኘት እንዲችሉ ይረዳል። ብሎም ልጆች የተሻሉ አንባቢዎች፣ አድማጮችና በቀላሉ ተግባቢዎች እንዲሆኑ ይረዳቸዋል። የማስታወስ፣ የማስተዋል ትኩረትና የቁጥር ትምህርት ችሎታንም ያዳብራል፡፡

በዚህም መሰረት የዛሬው ሳምነታዊ መልዕክታችን ከቋንቋ በተለይ አለማቀፍ በሆነው እንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡ መረጃውን ያጋራን EM ነው፡፡ መልካም ንባብ፡፡

እንግሊዝኛንም ሆነ ማንኛውንም ቋንቋ ለመልመድ፣ በመጀመሪያ ደፍረን መናገር መቻል አለብን። ትንሽም ትሁን የምናውቃትን ቃል እየደጋገምን መናገር አለብን! መናገር ስንጀምር ነው ሁ ሉ ም ነገር ፈር እየያዘ የሚሄደው!

አብዛኞቻችንኮ በርካታ የእንግሊዝኛ ቃላትንና ሀረጋትን እናውቃለን፤ እንዲሁም ሙሉ ዓረፍተ ነገሮችን መመስረት እንችላለን፤ ነገር ግን የመናገር ልምድ ስለሌለን መናገር ይከብደናል። የምናውቀውን ቃላትና ህግጋት እንዴት አሰካክተንና ቅደም ተከተል አሲዘን መናገር እንደምንችል አናውቅም። ለመናገር አንደፍርም፤ እንፈራለን። ሰው ምን ይለኝ ይሆን የሚል ይሉኝታ ያሸማቅቀናል።

ምን መሠላችሁ፣ ችግሩ ያለው አመለካከታችን ላይ ነው። እንግሊዝኛ ለመናገር መፍራት የለብንም;; ፈረጆቹኮ አማርኛ ሲናገሩ በፍፁም አይፈሩም ወይም ደግሞ አያፍሩም። የፈለገ ቢሰባብሩትም ዘና ብለው ነው የሚናገሩት። ትንሽ አማርኛ ካወቁ "አማርኛ እንችላለን!" ብለው ያስባሉ። እኛ ሁልጊዜ በመማርና በማጥናት ላይ ነው ትኩረታችን። ቲዮሪ ብቻ ፋይዳ የለውም ተግባር ነው ዋናው።

የፈለገ Vocabulary ብናውቅ የፈለግ Grammar ብናጠና፣ የተማርነውን ነገር ካልተለማመድነው ወይም ባገኘነው አጋጣሚ ውስጥ ጣልቃ እያስገባን ካልተጠቀምነው፣ እንረሳዋለን። ትርጉሙ፣ ህጉና አገባቡም ይጠፋብናል፥ እውቀታችን አይዳብርም! ልምዳችን አይጨምርም። ልጆቻችን በእንግሊዝኛ የመናገር ልምድ ሲያዳብሩ ፣ በራስ መተማመናቸውም ይጨምራል። በዚህ ሰአት ያለ ምንም ጭንቀት መናገር ይጀምራሉ።

እንደዚህ ሲባል ግን ቃላትን፣ ግራመርን ወይም ስፖክን ኢንግሊሽን ማጥናት የለባቸውም  ማለት አይደለም። እነዚህን ነገሮች ማጥናት በጣም አስፈላጊ ነው። ገቢ ከሌለ ወጭ አይኖርም። ከየት አምጥተው ያወጡታል? If there is no input, there is no output. ይላሉ ፈረንጆቹ። ገቢ ሲኖር ነው ወጪም የሚኖረው። ስለዚህ ማጥናት የግድ ያስፈልጋል። ነገር ግን ያጠናነውን ነገር በደንብ እየደጋገምን መለማመድ አለብን። አንድ ጊዜ ብቻ አንብቦ ወይም አድምጦ ዘወር ማለት በቂ አይደለም።


የምንፈራው ለተወሰነች ጊዜ ብቻ ነው፤ ከዛ ፍርሃታችን እኛኑ እስከሚደንቀን ድረስ ለቆን ይጠፋል። አንድ ማወቅ ያለብን ነገር አለ፣ ማንኛውንም ነገር በትክክል መሥራት የምንችለው ብዙ ጊዜ ካጠፋንና ከተሳሳትን በኋል ነው። ይህን ማወቅ አለብን። ካልተሳሳትን ደግሞ እየሞከርን አይደለም፤ ካልሞከርን፣ ምንም ነገር ማሳካት ወይም ከእቅዳችን መድረስ አንችልም ማለት ነው። አስታውሱ፣ ትንሽም ትሁን የምናውቃትን ቃል እየደጋገምን መናገር አለብን! መናገር ስንጀምር ሁ ሉ ም ነገር ፈር እየያዘልን ይመጣል!ሲል የመረጃ ምንጫችንን የቀረበውን መልእክት ከጥቂት ማስተካከያ ጋር እንዲህ አጋራናችሁ፡፡

በትምህርት ቤታችንም  የእንግሊዝኛ ቋንቋ በትምህርት ዓይነትና በማስተማሪያ ብሎም በመግባቢያ ቋንቋነት እየተሰጠ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ተማሪዎች በድፍረት ቋንቋውን እንዲጠቅሙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያግዙ ሪዲንግ ካምፔይን ፣ ስፔሊንግ ቢ፣ዲቤት ፣ ስቶሪ ዴይ ፣ሞቲቬሽናል ስፒች እና ግራንድ ኢንግሊሽ ዴይ የመሳሰሉ ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ስለዚህ ወላጆች፡-
ከላይ እንግሊዝኛ ቋንቋን ለመልመድ የቀረበውን ጠቃሚ መልዕክት ከልጆች ጋር በመወያያት እና ለተግባራዊነቱ ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ተማሪዎቻችን የሚማሩትን ትምህርት በአግባቡ እንዲረዱና ውጤታማ እንዲሆኑ እንግሊዝኛ ቋንቋን የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመናገርና የማዳመጥ ክህሎታቸውን በሚገባ በማሳደግ አለም አቀፍ ተወዳደሪ ይሆኑ ዘንድ እየተደረገው ያለውን ጥረት በማገዝ የጋራ ሓላፊነታችንን ዕንወጣ ስንል የዛሬውን መልዕክታችንን አጠናቀቅን፡፡


How Children Succeed

In his book entitled "How Children Succeed," Tough explores the factors that contribute to children's success beyond traditional measures of intelligence and academic achievement. Through research and real-life examples, he argues that character traits such as perseverance, curiosity, and resilience play a crucial role in helping children thrive.

Dear parents:

Today, for our weekly message, we have chosen the following ten key lessons and insights from the book, "How Children Succeed,"  Enjoy reading the ten points and try your best to help your child succeed. 

1. The Importance of Character:

The author, Tough emphasizes that character traits, often referred to as "non-cognitive skills," are critical for success in life. Qualities such as determination, resilience, and emotional intelligence are just as important, if not more so, than IQ in determining a child's long-term outcomes.

2. Understanding Determination and Resilience:

The author highlights the concepts of determination and resilience as key components of success. Determination refers to the passion and perseverance needed to achieve long-term goals, while resilience is the ability to bounce back from setbacks. Both traits are essential for navigating challenges.

3. The Role of Adversity:

Tough discusses how experiencing adversity can actually foster resilience in children. He notes that overcoming obstacles can teach valuable life lessons and develop coping strategies, ultimately leading to greater success in the future.

4. The Impact of Environment:

The book explores how a child's environment influences their development of character traits. Supportive environments, whether at home or in school, encourage the growth of resilience and determination, while toxic environments can hinder these qualities.

5. The Importance of Relationships:

Tough emphasizes the significance of strong relationships in a child's life, particularly with adults. Positive mentorship and supportive adult interactions can help children develop the skills and confidence needed to succeed.

6. Teaching Self-Regulation:

The author discusses the concept of self-regulation, which involves managing emotions, thoughts, and behaviors. Teaching children how to self-regulate can improve their academic performance and social interactions, contributing to their overall success.

7. The Role of Failure:

Tough argues that experiencing failure is an essential part of personal growth. Allowing children to face challenges and learn from their mistakes fosters resilience and helps them understand the value of perseverance.

8. Educational Approaches:

The book examines various educational models that prioritize character development alongside academic achievement. Schools that focus on social and emotional learning create environments where children can develop the necessary skills for success.

9. Mindset Matters:

Tough explores the concept of a growth mindset, popularized by psychologist Carol Dweck. Encouraging children to view challenges as opportunities for growth rather than as threats can significantly impact their motivation and willingness to take risks.

10. Long-Term Strategies for Success:

Finally, the author advocates for long-term strategies that prioritize character development from an early age. Programs that focus on social-emotional learning, mentorship, and building resilience can set children on a path toward lifelong success.

In his book "How Children Succeed," Paul Tough presents a compelling argument for the importance of character and resilience in children's success. By highlighting these ten key lessons, he encourages parents, educators, and policymakers to prioritize the development of non-cognitive skills alongside traditional academic measures, ultimately fostering a generation of capable, resilient individuals.


ለአል-ዓፊያ ማኀበረሰብ በሙሉ
እንኳን ደስ አላችሁ!

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በወረዳ 06 ት/ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ትምህርታዊ ውድድር የአል-ዓፊያ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ቤተል ቅርንጫፍ ተማሪዎች በ8ኛ ክፍል 1ኛ፣ በ6ኛ ክፍል ደግሞ 2ኛ በመሆን አስደናቂ ውጤት ማስመዝገባቸው በጣም ያስደስታል!
እንኳን ደስ አላችሁ‼️‼️


ስለ እውነት dan repost
ክፍል 2

5. የልጆችዎን የትምህርት አቀባበል የሚመዝኑባቸው ቀላል ዘዴዎች ይኑርዎት

ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ለመርዳት በየዕለቱ ምን ተምረው እንደመጡ መፈተሸና መከታተል እንዲሁም ቀለል ባለ ዘዴ የምዘና ጥያቄ አዘጋጅተው መመዘን ይችላሉ፡፡ በተወሰነ የጊዜ ርቀት ይህን ተግባር በማከናወን ልጆችዎን ከተማሩት ምን ይህል በሚገባ እንደተረዱት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ ግን ልጅዎን በሚያሳስብና በሚያስጨንቅ መልኩ መካሄድ የለበትም፡፡ ልጆችዎ እተዝናኑና እየተጫወቱ ሊሰሩ የሚችሉበትን ድባብ መፍጠር ይገባል፡፡ ልጆችን በዚህ መልኩ የተማሩትን በተለያየ ዘዴ እየገመገሙ ማነፅ በልጆቻችን ትምህርት በስፋት ተሳታፊ እንድንሆን፤ ልጆችንም የተማሩትን ትምህርት በጊዜ በሚገባ እንዲከልሱና በጥልቀት እንዲረዱ እንዲሁም በቀላሉ የተማሩትን አስታውሰው በምዘና መለኪያዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እና በክፍል ውስጥም በንቃት እንዲሳተፉ ጭምር ያበረታታቸዋል፡፡

6. ልጆችዎን በትምህርታዊ ጉዞ ያዝናኑዋቸዋል

“ካሉበት ቦታ መቀየር ከድካም ዕረፍት የመውሰድ ያህል አስደሳች ነው” ይባላል፡፡ እንግዲያው እርስዎ ልጆችዎን ቀኑን ሙሉ ከሚውሉበት ት/ቤት እንዲሁም ከቤትዎ በተወሰነ ጊዜም ቢሆን በማላቀቅ ለምን በሽርሽር አያዝናኗቸውም? ከተለመደ ቦታ መቀየር ለሁሉም ቢሆን ያዝናናል፡፡ በተለይ ደግሞ ትምህርት በመማር ከፍተኛ ውጣ ውረድ በት/ቤትም ሆነ በቤት ለሚጋፈጡ ልጆችዎ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እዚህ ጋር ግን አንዴ ቆም ብለን ማሰብ የሚገባን አለ እሱም ልጆቻችን በሽርሽር/በጉብኝት ለማዝናናት ከመነሳታችን በፊት የምናዝናናበት/የምናስጎበኝበት ቦታ ለልጆቻችን የአካልም ሆነ የአዕምሮ ጤና እንዲሁም የሥነ ልቦና ደህንነታቸው ብሎም ሞራልና ግብረ-ገብነታቸው ላይ ምንም አይነት ጉዳት የማያስከትል (ዋጋ የማያስከፍለን) ስለመሆኑ ቅድሚያ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ አለያ ግን አተርፍ ባይ . . . ነው የምንሆነው፡፡

7. ልጆችዎ የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግቡ ዕውቅና ሰጥተው ያበረታቱ፤ ይሸልሙ

ልጆችዎን ለሚያስመዘግቧቸው የትምህርት ስኬቶች ዕውቅና ሰጥቶ ማበረታታትና መሸለም የተሻለ እንዲሰሩ በጣም ያግዛቸዋል፡፡ እርስዎ ታዲያ ልጆችዎ የላቀ ውጤት ይዘው ወደ ቤት ሲመጡ በማበረታታትና በሽልማት ሊቀበሏቸው ይገባል፡፡ ይህን ለማድረግ ግን የግድ ከፍተኛ የሆነ ወጪ ማውጣት አይጠበቅም፡፡ አቅም በፈቀደ ከወላጅ ለልጆች የሚደረግ ሽልማት ልጆች ደክመው ያመጡት ውጤት በወላጅ የላቀ ዋጋ እንደሚሰጠው መልዕክት ለማስተላለፍ መሆን ነው የሚገባው፡፡

8.ልጆችዎ እረፍት እንዲኖራቸው ያድርጉ! ለልጆችዎ ሰዓት ይኑርዎት! 

ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ከጥናት ዕረፍት መውሰድ ለልጆች ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም ልጆችዎን በትምህርት ለማገዝ የሚረዳ ቀላል መንገድ ነው፡፡ በቤት ውስጥም ቢሆን አንዳንዴ ልጆች ከትምህርት ተለይተው (አቋርጠው) ሊዝናኑ የሚችሉበት ጊዜ ያመቻቹላቸው፡፡ እርስዎም ካለዎት ሰዓት ምርጡን ከልጅዎ ጋር በመሆን ያሳልፉ፡፡ ግን ግን ስንቶቻችን ነን ካለን ሰዓት ምርጡን ነገ እኛን ይተኩናል ብለን ብዙ ከምንደክምላቸው ውድ ልጆቻችን ጋር የምናሳልፈው? ምን ያህል እርስዎ ለልጆችዎ ቅርብ ነዎት? ለልጅዎት ምርጡን ሰዓት ሰጥተው ያገኟቸዋል ወይስ . . . ? እኛ ለልጆቻችን ቅርብ ልንሆን ይገባል፡፡ ይህን የማናደርግ ከሆነ ግን ልጆቻችንን እኛ ሳንሆን የሚያንፃቸው ሌላ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክ፣ ቲቪ፣ እና የመሳሰሉት፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ነገ የምንመኘውን አይነት ትውልድ ማፍራት ባዶ ተስፋ ሆኖ ይቀራልና ለልጆቻችን ሰዓት መስጠታችን በሚገባ መፈተሽ ለነገ የማይባል ነው፡፡

9.ልጆችዎ በአግባቡ መመገባቸውንና በተገቢው ሰዓት ወደ መኝታቸው መሄዳቸውን ያረጋግጡ!

ት/ቤት እንደ ስያሜው እውቀት የሚቀሰምበት ቦታ ነው፡፡  ትምህርት ለመማር ደግሞ ተማሪ በአካልም ሆነ በአዕምሮ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ የምግብ ስርዓትና የመኝታ ሰዓት የተስተካከለ ሊሆን ይገባል፡፡ እንደ ወላጅ ለልጆች አሸክመን ለምንልከው ምግብ ምን ያህል ተገቢውን ጥንቃቄ እናደርጋለን? አንዳንዴ ልጆች እንደማይመቻቸው እየታወቀ የሚታሰርላቸውን ምግብ እንዲጨርሱ በት/ቤት የሚፈጠረው ግብ ግብ  ለጉድ ነው፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን ምግብ በዕርግጥ እየተመለከቱት ነውን? የሚል ጥያቄም ያስነሳል፡፡ በተመሳሳይ የልጆች የእንቅልፍ ሰዓትም ከፍተኛ ክትትል ያሻዋል፡፡ ልጆች መተኛት በሚገባቸው ሰዓት ስለመተኛታቸው እንደ ወላጅ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ልጆች ማረፍ በሚገባቸው የመኝታ ሰዓት ተገቢ ባልሆኑ ተግባራት የሚጠመዱ ከሆነ በአካልም ሆነ በአዕምሯቸው ላይ የሚፈጠረው ጫና በትምህርታቸው ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡

ውድ ወላጅ እንግዲህ ልጆቻችንን በትምህርታቸው ሥኬታማ ማድረግ ከሚቻልባቸው ቀላል ዘዴዎች 9ኙን የጠቆምንበት  መልዕክት በዚሁ ተጠናቋል፡፡

እንደ ወላጅ ከጽሑፉ ልጅዎን በትምህርቱ/ቷ ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ ነጥቦች እንዳገኙ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እባክዎ ልጆችዎን በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ ለመርዳት እንደወላጅ ሃላፊነትዎን በአግባቡ ይወጡ የዛሬው መልዕክታችን ነው፡፡ ሰላም!


ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ስኬታማ ማድረግ የሚችሉባቸው 9 ቀላል ዘዴዎች

Easy ways for parents to support their children's studies


ክፍል 1

ባለንበት ዘመን ልጆች ማሳደግ እጅግ ፈታኝ ከሆኑት ሃላፊነቶች አንዱ ነው፡፡ “ልጄ ምርጥ ትምህርት አግኝቶ ስኬታማ መሆን እንዲችል እኔ ምን ማድረግ አለብኝ?” የሚለውም እንደወላጅ በጣም አሳሳቢና ዕረፍት የማይሰጥ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ አፋጣኝና ተገቢ ምላሽ የሚሻ:: የልጅዎትን የትምህርት ሁኔታ ሲያስቡም ልጆችን በትምህርታቸው ለመርዳት ይህ ነው የሚባል አስተዋፅኦ ማበርከት የማይችሉ ሊመስልዎት ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ጥናቶች እንደሚነግሩን ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው መርዳት ወይም ሥኬታማ ማድረግ የሚችሉባቸው በርካታ ዘዴዎች መኖራቸውን እንገነዘባለን፡፡

እኛም ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ሥኬታማ ማድረግ ከሚችሉባቸው ቀላል ዘዴዎች መካከል 9ኙን ለዛሬው ሳምንታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት በርዕሰ ጉዳይነት መርጠናል፡፡ በጽሑፉ ልጆችዎትን በትምህርታቸው ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ ዕውቀቶችን እንደሚቀስሙበት እምነታችን ነው፡፡ መልካም ንባብ

1. ልጆችዎ ሲማሩ የሚቸገሩበት ስለመኖሩ ጊዜ ሰጥተው ይጠይቋቸው፡፡ ቀረብ ብለው ያወያዩዋቸው፤ የሚችሉትን ዕገዛም ያድርጉላቸው!!

ልጆችዎን በትምህርታቸው ከሚረዱበት ዘዴዎች እጅግ ቀላል የሚባለው የልጆችዎን የትምህርት እንቅስቃሴ እርስዎም ጉዳዬ ብለው እንደሚከታተሉዋቸው ማሳየት፤ የሚከብዳቸው ትምህርት ካለም እነርሱን መጠየቅ ነው፡፡ “ትምህርት እንዴት ነው? ምን ችግር ገጠመህ/ሽ? የምረዳህ/ሽ ነገር አለ?” እና መሰል ጥያቄዎችን ልጆችን ቀርቦ መጠየቅ ቀላል ግን የላቀ ፋይዳ የሚገኝበት ነው፡፡ ግን ስንቶቻችን ነን ሥራዬ ብለን ይህን የምናደርገው? ስንቶቻችን ነን ልጆቻችንን ት/ቤት ከመላክ በዘለለ እንዲህ በትምህርታቸው ተጨንቀን የምንጠይቅ? እራሳችንን እንጠይቅ! ልጆችዎ የርስዎን ዕርዳታ ሲፈልጉ ለዚህ ዝግጁ መሆንዎን ማወቃቸው በራሱ እርስዎ ለእነርሱ ትምህርት ዋጋ እንደሚሰጡ ብሎም ከጎናቸው መሆንዎን ለማሳየት ጭምር ይጠቅማል፡፡ ልጀችዎ የሚቸገሩበትን የትምህርት ርዕስ (topic) ለእርስዎ መጥተው ካሰረዱዎት በቻሉት መጠን ሳይዘገዩ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይገባዎታል፡፡ ልጅዎን የገጠመው/ማት የትምህርት ችግር ከአቅም በላይ ከሆነም በጉዳዩ ዙሪያ የተሻለ መርዳት የሚችሉ ባለሙያዎችን በማማከር አለያም በትምህርቱ ዙሪያ የተዘጋጁ መጽሐፍትን ገዝተው ማቅረብን እንደ መፍትሔ መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን ልጆችዎ ላይ የሚያስተውሉት የትምህርት ችግር እየከፋ ከሄደና ለመስተካከል ረጅም ጊዜ የሚፈልግ አይነት ከሆነ ልጅዎን በትምህርት አይነቱ (subject) ዙሪያ የግል አስጠኚ መቅጠርዎ ሌላው አማራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ ልጅዎ ከትምህርት ገበታ የቀረ ወይም ታሞ ከነበረ አለያም ሌላ የጤና ችግር ገጥሞት የትምህርት አቀባበሉ ላይ ጉልህ ችግር ከተፈጠረ ከት/ቤት ባሻገር ቤት መጥቶ በግል የሚረዳው የትምህርት ባለሙያ (አስጠኚ) ቀጥሮ ልጅዎ እንዲረዳ ማድረግ ተገቢ ነው የሚሆነው፡፡

2. ልጆችዎ ማንበብን የደስታ ምንጫቸው እንዲያደርጉ ያበረታቱ

ማንበብ የብዙ ስኬታማ የሆኑ ተማሪዎች አይነተኛ ባህሪ ነው፡፡ ወላጆች ይህን ተግባር ልጆች ይተገብሩት ዘንድ ማበረታታት አለባቸው፡ ይህን ማድረግ ምን ይከብዳል? ወደ ቤተ-መጻሕፍት ሲሄዱ ልጆችዎንም ይጋብዟቸው ፣ በቤትዎ በቂ መጽሐፍ እንዲኖር ያድርጉ ከተቻለም የቤት ውስጥ ቤተ-መጻሕፍት (ላይብረሪ) ይኑርዎት፤ ልጆችዎ የተሻለ የትምህርት ውጤት ካመጡም መጽሐፍ ይሸልሟቸው፤ ስጦታም ያበርክቱላቸው፡፡ እነዚህ ተግባራት በየትኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ልጆች የንባብ ፍቅርን ለማስረፅ የሚያስችሉ ቀላል ዘዴዎች ሆነው ማገልገል ይችላሉ፡፡

3. በቤት ውስጥ የፀጥታ ጊዜ እንዲኖር ያድርጉ

በቤት ውስጥ ያሉ ህጻናትም ሆኑ ዐዋቂዎች እየተንጫጩና እየረበሹ ሌሎች ልጆች ሀሳባቸውን ሰብሰብ አድርገው በአንድ ልብ ማንበብ፣የቤት ስራቸውንም ሆነ ሌሎች በትምርት ቤት የታዘዙትን መስራት ይቸግራቸዋል፤ ሀሳባቸው ይበታተንባቸዋል፡፡ የተሰበሰበ ትኩረት ማድረግ ይሳናቸዋል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ ታዲያ በቀን ውስጥ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ምንም አይነት የልጅዎትን ትኩረት የሚነሳ ጫጫታና ረብሻ የማይኖርበት የጸጥታ ጊዜ ስርዓት በቤትዎ ውስጥ ሊኖር ይገባል፡፡ ይህም ልጆች በቤት ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት ተግባራት በተረጋጋና ፀጥታ የሰፈነበት (distraction-free) በሆነ ሁኔታ እንዲሰሩ ያመቻቻል፡፡


4. ከልጆችዎ ት/ቤትና መምህራን ጋር ቅርብ ይሁኑ

ት/ቤት የነገ የልጅዎ ማንነት የሚቀረፅበት ስፍራ ነውና እንደ ወላጅ የልጆችዎን ት/ቤት ጉዳዬ ብለው ሊከታተሉ ይገባል፡፡ አሁን እያነበቡ ያሉት ሳምንታዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክትን  ጨምሮ ሌሎች በት/ቤቱ የሚዘጋጁ መልዕክቶችን (ዕለታዊ፣ወርሃዊ … ) በሚገባ ማንበብና ቦታ ሰጥተው መረዳት እንዲሁም ከልጆችዎ መምህራን ጋር በቅርብ መነጋገር ይጠበቅቦታል፡፡ ከዚህ ባሻገር በየጊዜው ስለ ልጆችዎ የትምህርት ጉዳይ ሳይታክቱ ከመምህራን ጋር በመወያየት (በመጠየቅ) ልጅዎ ምን አይነት ድጋፍ ከእርስዎ እንደሚያስፈልገው መረዳት ይጠበቅብዎታል፡፡ ከልጅዎ መምህራን ጋር ቅርርብ በመፍጠር በሚኖርም ውይይት ልጆችዎ ተጨማሪ ድጋፍ የሚፈልጉባቸው ክፍተቶችንም ይገነዘባሉ፡፡

ክፍል 2 ይቀጥላል


በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለአቅም ማሻሸያ (Remedial) ትምህርት ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የምዝገባ ጊዜ እንደሚከተለው መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል፣

👉ለመደበኛ Remedial ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ታህሳስ 21 እና 22/2017 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

⚡️በቅጣት ምዝገባ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

👉በግል ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

💥ለምዝገባ ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና አንድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ፣ 3*4 የሆነ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፤

• የካምፓስ ምደባ በሚመለከት ከዚህ በታች በተገለጸዉ መሠረት ይሆናል።

Natural Science

ስማቹህ A to G የሆናቹህ ዱራሜ ካምፓስ
ስማቹህ H to Z የሆናቹህ ዋና ግቢ

Social Science

ስማቹህ A to J የሆናቹህ ዱራሜ ካምፓስ
ስማቹህ K to Z የሆናቹህ ዋና ግቢ

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

#WachamoUniversity #Remedial

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.