ሚዲያ በልጆች አእምሮዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ስሜታዊ፣ ማህበራዊ እድገት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለመቀነስ ወላጆች ሊተገብሯቸው የሚገቡ ምክሮች።
ክፍል 1…
እንደሚታወቀው በሀገራችንም ሆነ በዓለማችን ሚዲያ በልጆች አስተዳደግ እና ሁለንተናዊ ማንነት ላይ ከባድ አደጋ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡በየቤቱ በርካታ ልጆችን አንዳንዴ አዋቂዎችን ሳይቀር አጉል ጠልፎ እየጣለ አያሌ ቤቶችን እያናጋ፤ ሰላምንም እያደፈረሰ ይገኛል፡፡ታዲያ እኛም ለዛሬ በዚህ ዙሪያ ጠቃሚ ግንዛቤ ያስጨብጣል ያልነውን መረጃ ለናንተ ለወላጆች እነደሚከተለው አቅርበነዋል።
መረጃው ጥናትን መሰረት አድርጎ በዘርፉ በለሙያ የቀረበ በመሆኑ ሁላችንም አንብበን ከልጆቻችን ጋር በመወያየት የመፍትሔ አካል መሆን ይጠበቅብናል።
መልካም ንባብ፡፡
የመገናኛ ሚዲያዎች በሁለት ዋና ክፍሎች የሚመደቡ ሲሆን አንደኛው ኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በመባል የሚጠራ ሲሆን እንደ ቴሌቪዥን፣ ኮምፒውተር፣ ስማርት ስልኮችን፣ ወዘተ በመጠቀም ፊልሞችን፣ ድራማዎችን፣ ፕሮግራሞችን፣ ጨዋታዎችን፣ ሙዚቃዎችን እና የሙዚቃ ኪሊፖችን የሚተላለፉበት ነው፡፡ ሌላኛው ፕሪንት ሚዲያ የሚባል ሲሆን በወረቀት ላይ የሰፈሩ ፁህፎች፣ ታሪኮች፣ ዜናዎች፣ ልቦለዶች፣ ወጎች፣ መረጃዎችን፣ ወዘተ የሚያካትት ነው፡፡
ሁለቱም የሚዲያ አይነቶች በልጆች ላይ አወንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ያሳድራሉ፡፡ አዎንታዊ ተፅዕኖዎች ለምሳሌ የልጆችን ስነምግባር፣ ስነልቦና፣ የፈጠራና ችግር የመፍታት ችሎታዎች የሚያሳድጉ የተለያዩ ትምህርቶች፣ ምክሮች፣ መረጃዎች በሚዲያ አማካኝነት ሲተላለፉ ነው፡፡
ሚዲያ በዚህ ትውልድ ልጆችና ወጣቶች ዘላቂ ተፅእኖ አለው፡፡ ምክያቱም በሚዲያ የሚተላለፉ ይዘቶች በቀላሉ መደጋገም ስለሚችሉ በቀላሉ በልጆችና በወጣቶች አእምሮ የመቀመጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ የሚቀርቡት ይዘቶች የልጆችን ትኩረት ለመሳብ በማራኪ መልኩ መቅረባቸው ሌላኛው ምክንያት ነው፡፡
የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በተለይ ቴሌቪዥን በልጆች ላይ የሚያሳድረው ጉልህ ተፅዕኖ መተቸት የተጀመረው ቆየት ላለ ጊዜ ነው፡፡ ከነዚህም ትችት ውስጥ አንደኛው በለጋ እድሜያቸው ልጆች ለሚዲያ መጋለጥ የአስተሳሰብ እድገታቸው እና የትምህርት ውጤታቸው ላይ የሚያስድረው ተፅዕኖ ነው፡፡ በአጠቃላይ ከተለያዩ ጥናታዊ ውጤቶች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ሚዲያ በልጆች ሁለንታዊ መዳበር ላይ የሚከተሉትን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ያሳዳራል፡፡
እነሱም፡-
1. ሚዲያ ታዳጊ ልጆች ጤናማ ተግባራት ለማከናወን የሚኖራቸውን ጊዜ ይቀንሳል/ Media use decreases time spent in more healthful activities/
ጤናማ የሆኑ ተግባራት የምንላቸው ከቤተሰብ ፣ ከጓደኝ ጋር የሚኖረን መስተጋብር በመስተጋብሩም ውስጥ ልጆች የሚያገኞቸው ጠቃሚ ነገሮች ለምሳሌ የፈጠራ ችሎታ መዳበር፣ ችግሮችን የመፍታት ክህሎት፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ፣ የማንበብ፣ በቤት ውስጥ ወላጆችን ማገዝ፣ በቂ እንቅልፍ ማግኝት ናቸው፡፡ እነዚህ ጠቃሚ ተግባራት አብዛኛውን የልጆች ጊዜ በመውሰድ ቀድመው መዳበር የሚገባቸው ሲሆን ለብዙ ሰዓት ሚዲያዎችን መጠቀም ለነዚህ ተግባራት የሚኖርን ጊዜ እንዲቀንስ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
2. ሚዲያ በልጆች የጨዋታ እና የመዳበር ሁኔታ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ /IMPACT on PLAY and DEVELOPMENT/
ታዳጊ ልጆች የወላጆቻቸውን ስልኮች በመጠቀም ለረዥም ሰዓት በስክሪን ላይ መጋለጣቸው በጣም እየጨመሩ በመምጣቱ ተመራማሪዎች በታዳጊ ህፃናት ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተፅዕኖ መገምገም ጀምረዋል፡፡ ለምሳሌ በቅረቡ የወጡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች ተገቢ ክህሎቶችን፣ የሚጠበቁ ተግባራትን ፣ ችሎታወችን ከማከናወን ይልቅ የስክሪን ላይ የተመለከቷቸውን የገፀ-ባህርያት ድርጊቶችን፣ እንቅስቃሴዎችና ንግግሮችን አስመስለው ማሳየት እንደሚቀናቸውና በእድሜያቸው የሚጠበቁ መሰረታዊ ክህሎቶችንና ተግባራትን ለምሳሌ ጫማቸውን እራሳቸውን ችለው ማሰር፣ ብስክሌት መንዳት፣ መዋኘት፣ ፊታቸውና እጃቸው መታጠብ፣ መፀዳዳት ወዘተ ላይ ዝቅተኛ የሆነ ክንውን አሳይተዋል፡፡
የሚገርመው በአንድ መዋለ ህፃናት ላይ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው በጥናቱ ከተሳተፉት ህፃናት 58% የሚሆኑት የኮምፒተር ጨዋታዎችን እንዴት መጫወት እንዳለባቸው ህጎችን ጠንቅቀው የሚያውቁ ቢሆኑም ከነዚህም ውስጥ ጫማቸውን እንዴት ማሰር እንደሚችሉ የሚያውቁት 9% ብቻ ናቸው፡፡ ይህ የሚያሳየው ልጆች ለሚዲያ ያላቸው መጋላጥ በመጨመሩ እና የልጆች ሁለንተናዊ መዳበር አሉታዊ ተፅዕኖ በማሰደሩ ነው፡፡ ምንም እነኳን ልጆች የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎችን እንደ ቴሌቪዥን ጨዋታዎች፣ ስማርት ስልኮች፣ ኮምፒውተርን ላይ በተጫኑ ጨዋታዋችን በመጠቀም የሚጫወቱ ቢሆኑም እነዚህ ጨዋታዎች የልጆችን ከማዝናናት ባሻገር የልጆችን አእምሮ፣ አስተሳሰብና የፈጠራ ችሎታ የሚያሳድጉ አይደሉም፡፡ ይልቁንም በተጨባጭ እውነታና በአካባቢያቸው የሚገኙ ነገሮችን በመጠቀም ልጆች እንዲጫወቱ ማድረግ የልጆችን ሁለንተናዊ እደገት እንዲጨምር ያደርጋል ምክንያቱም ልጆች በቀጥታ ከመጫወቻዎቹ ጋር ያላቸው መስተጋብር ሰፊ እና ሁሉንም የስሜት ህዋሶቻቸው በንቃት መረጃን መሰብሰብ ስለሚችሉ ነው፡፡ በተቃራኒው በሚዲያዎች አማካኝነት የሚጫወቱ ከሆነ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ስለሚሆን በጨዋታው ብቻ ተወስነው ሌሎች ለእድገታቸው አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ተግባሮችን ማከናወን ስለማይችሉ መረጃ ተቀባይ ብቻ እንዲሆኑ ስለሚያደርጋቸው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በሃገረ እንግሊዝ በመምህራን ማህበር አማካኝነት በቅድመ የልጆነት ወቅት የሚገኙ ታዳጊ ልጆች በኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ብዙ ሰዓት መጠቀማቸው መሰረታዊ ክህሎቶችን ማከናወን ላይ ዝቅተኛ ችሎታ እንደሚያሳዩ አበክረው ይመክራሉ፡፡ እነዚህ ልጆች የተለያዩ ነገሮች በመደርደር መጫወትና እንዲሁም ለተለያዩ የትምህርት ቤት ተግባራትን ለመስራት ብዕርና እርስሳስ መጠቀም በደንብ እንደማይችሉ ጥናታቸው አረጋግጧል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁለት ጥናቶችን በአካባቢ በሚገኙ ቁሳቁሶች በመጠቀም የሚዘጋጁ መጫወቻዎች ለታዳጊ ልጆች የቋንቋ መዳበር ጠቃሚ እንደሆኑ አረጋግጠዋል፡፡የመጀመሪያ ጥናት እደሜያቸው ከ18 እስከ 30 ወር የሆናቸው ታዳጊ ህፃናት ከወላጆቻቸው ጋር ነገሮችን በመደርድር የሚጫወቱት የቋንቋ ወጤታቸው የተሻለ ሲሆን በሌላኛው ጥናት የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ የሚጠቀሙ ታዳጊ ልጆች ዝቅተኛ የንግግር የቋንቋ ክህሎት አሳይተዋል፡፡
አዋቂዎች መረጃን ከቴሌቪዥን ላይ በመመልከት የሚፈልጉት መረጃ መርጠው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የወሰደቱን መረጃ እውነተኛ ይሁን ምናባዊ መለየት ይችላሉ፡፡ ልጆች ግን ያዩት ነገር መርጠው መውሰድ አይችሉም፡፡ የሚያዩትን ነገር እውነተኛ በገሃዱ አለም ያለ ይሁን በምናብ የተፈጠረ መሆኑን መለየት ይቸገራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ታዳጊ ህጻናትም በቴሌቨዥን መስኮት ያዩትን ባህሪዎች ትርጉም ባለው መልኩ አስመስለው ማሳየት ይችላሉ፡፡ ታዳጊ ልጀች በምስል ለሚታዩ ነገሮች ከፍተኛ ትኩረት የሚያደርጉ ሲሆን በአብዛኛውም ከምስሉ ጋር የቀረበውን ታሪክ ወይም ንግግር ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ታዳጊ ልጆች በቴሌቪዥን መስኮት ያዩዋቸው የሚያሰፈሩ ምስሎች በወስጠ አእምሮዋቸው ለረዥም ጊዜ መቀመጥ ስለሚችሉ ለተለያዩ የመኝታ ችግሮችና ለቅዠት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
........ክፍል 2 ይቀጥላል