ክፍል 2…
3. በልጆች ባህሪይና ትኩረት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ/IMPACT on BEHAVIOR and ATTENTION/
ልጆች በቀን ውስጥ ለረዥትም ሰዓታት የተለያዩ ትዕይንቶችን በሚዲያ የሚመለከቱ ከሆነ በባህሪያቸውና በነገሮች ላይ ትኩረት የማድረግ ብቃታቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደር ለእንቅልፍ መዛባትን በማስከተል የአእምሮ እድገታቸው ላይ የከፋ ጉዳት ያደርሳል፡፡ እ.አ.አ በ2016 የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው በስክሪን ነገሮችን የመመልከት ጊዜ እና ዝቅተኛ የመኝታ ሁኔታ እና የባህሪ ችግሮች እንደሚያያዙ አረጋግጧል፡፡ በታዳጊ እድሜያቸው ቴሌቪዥንን የሚመለከቱበት የሰዓት ብዛትና ለወደፊት ከሚኖር የትኩረት ችግር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለ ሲሆን በተለይ እድሜያቸው አንድ እና ሶስት አመት የሆናቸው ልጆች በቀን ውስጥ ለሰዓታት ቴሌቪዥን የሚመለከቱ ከሆነ እነዚሁ ልጆች ሰባት አመት ሲሞላቸው ለትኩረት ችግር እንደሚገጥማቸው በዚህ ጥናት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
4. ለወሲብ ተጋላጭ የሆኑ ባህሪያቶችን እንዲላመዱ አስተዋፅኦ ያደርጋል ፡፡ IMPACT of MEDIA on SEXUAL RISK BEHAVIORS
በፊልሞች፣ በቴሌቪዥን፣ እና በሙዚቃ ክሊፖች በአብዛኛው ወሲባዊ መልዕክቶች በግልፅ የሚሰራጩ ቢሆነንም አነዚህ መልዕክቶች የተሳሳቱና ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ የሚመሩ ናቸው፡፡ እንዳለመታደል ሁኖ እነዚህ መልዕክቶች በታዳጊዎች እውነተኛ እንደሆኑ ተድሮጎ ተቀባይነት ማግኘታቸው ነው፡፡ በሚዲያ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች እና የማስታወቂያ ይዘቶች በብዛት ወሲብ ነክ ናቸው፡፡ ወጣቶችም ሚዲያን እንደ ዋነኛ የወሲባዊ ባህሪያት የመረጃ ምንጭ አድርገውታል፡፡ በዚህም ምክንያት ታዳጊዎች ባገኙት የተሳሳተ የወሲብ መረጃ በራሳቸው ህይወት ያለጊዜያቸው በመሞከር ለተለያዩ ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ወሲባዊ ይዘት የተቀላቀለባቸው የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን አብዝተው የሚያዩ ወጣቶች ከማያዩ ወጣቶች የበለጠ ያለጊዜያቸው የተለያዩ ወሲባዊ ተግባሮችን ለመጀመር ይነሳሳሉ፡፡ታዳጊ ወጣቶች ከፍተኛ ደረጃ የወሲብ ይዘት ላለው ነገር የተጋለጡ ከሆነ ከሌሎች ካልተጋለጡ ወጣቶች ጋር ሲነፃፀሩ ሁለት እጥፍ በቀጣዮች ሦስት አመታት የማርገዝ እድል አላቸው፡፡ አነዚህ ጥናቶች በተጨማሪ እንደሚያሳዩት ወሲብ ነክ የንግግር ልውውጥ በቴሌቪዥን መስኮት የሚመለከቱትም ልክ ወሲባዊ ተግባራትንም እንደሚመለከቱ ወጣቶች ተመሳሳይ ችግር ይጋለጣሉ፡፡
5. አልኮልና ሲጃራ ተጠቃሚነት ያስከትላል፡፡ /IMPACT on TOBACCO and ALCOHOL USE/
ከመጠን ያለፈ የቴሌቪዠን፣ ፊልሞችን እንዲሁም የኮምቢውተርና የቪዲዮ ጌሞችን መመልከት ለአልኮልና ሲጃራ ሱሰኝነትን ያስከትላል፡፡ በቅርቡ የተሰራ ጥናት እንደዘገበው ወላጆች ልቅ የሆነ ፊልሞችን ልጆቻቸው እንዳይመለከቱ በማገዳቸው ምክንያት ሲጃራ ለመጨስ የመመከር ሂደት መቀነሱ ተረጋግጦል፡፡
6.በእንቅልፍና አመጋገብ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል/ IMPACT on SLEEP and NUTRITION/
ሚዲያን መጠቀም በቂ እንቅልፍ እና ጥሩ እንቅልፍ እንዳይኖር ማለትም በእንቅልፍ ልብ መንቃት፣ ቅዠት፣ የተዛባ የእንቅልፍ ልማድ እንዲከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም በልጆች በሽታን የመቋቋም ችሎታን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ የምግብ የመፈጨት ሂደትን በማስተጓጎል ልጆችን ከመጠን ላለፈ ውፍረት ይዳርጋቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ልጆች በሽታን የመቋቋም ብቃታቸውን እንዲቀንስ እና ለተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ እንዲል የሚያደርግ ሲሆን የትምህርታቸው ውጤታቸውም እንዲቀንስ አሉታዊ አስተዋፅኦ ያደርጋል ፡፡
በአንድ ጥናት ልጆቻቸው በመዋለ ህፃናት የሚማሩ 495 ወላጆች ስለልጆቻቸው ቴሌቪዥን የመመልከት ልማድና እና የመኝታ ሁኔታ ተጠይቀው ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ 25 ፐርሰንት የሚሆኑት ወላጆች የተገኘው መረጃ በልጆች መኝታ ክፍል ቴሌቪዥን እንዳለ አሳይቶል፡፡ ይህም ልጆች ለረዥም ሰዓታት ቴሌቪዥን የመመልከት ልማድ እንዲኖራቸውና በቂ የእንቅልፍ ጊዜ እንዳይኖራቸው በማድረጉ ነው፡፡ የእንቅልፍ መዛባት ችግር የሚያያዝ የበለጠ የበዛበት ምክንያት የቴሌቪዥን ምልከታው የጨመረው በልጆቹ መኝታ ቤት በመገኘቱ ምክንያት እንደሆነ የጥናቱ ተመራማሪዎች ተናግረዋል፡፡
የእንቅልፍ ማጣት ችግር ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት፣ ከስኮር በሽታ፣ ከትምህርት ችግር፣ እና ከተለያዩ የባህሪ ችግሮች ጋር እንደሚያያዝ ጥናቶች በተደጋጋሚ ይዘግባሉ፡፡
7. ሚዲያ በትምህርት ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል /IMPACT on ACADEMIC PERFORMANCE
ከመጠን ያለፈ የሚዲያ መጋለጥ በትምህርት ውጤት ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖ እንደለው ይታወቃል፡፡ ይህን አስመልክቶ ዘመሪመን እና ክሪስታኪስ የተባሉ ተመራማሪዎች አስከሰባት አመት የሚሆናቸውን ታዳጊ ልጆች የቴሌቪዥን ምልከታ በአስተሳሳብ እና በአእምሮዊ እድገታቸው ላይ የሚሳድረውን ተፅዕኖ ለመገምገም የሚከሩ ሲሆን የግምገማ ውጤቱ እንደሚያሳያው ልጆች ሶስት አመት ከመሆናቸው በፊት ለብዙ ሰዓታት በቀን ውስጥ ቴሌቪዥን የሚመለከቱ ከሆነ በአእምሮ እድገታቸው ላይ የከፋ ጉዳት እንደሚያደርስና ነገሮችን አንብቦ ለመረዳት እንደሚቸገሩ እና በትምህርታቸውም ዝቅተኛ ውጤት እንደሚያሰመዘግቡ ጠቁመዋል፡፡
8. ሚዲያ ለድብርት ያጋልጣል/ IMPACT on DEPRESSION/
ትዕይንቶችን በሚዲያ መስኮት ለረዥም ጊዜ መጠቀም ከድብርት ጋር እንደሚያያዝ ብዙ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ በሃገረ ዴንማርክ በተመሳሳይ የዕድሜ ክልል የሚገኙ 435 ወጣቶች ላይ ለረዥም ጊዜ በተካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው በእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰዓት ወይም ቀን ቴሌቪዥን መመልከት በጎልማሳነት የእድገት ወቅት ለከፍተኛ ድብርት እንደተጋለጡ ተጠቁሞል፡፡
9. ሚዲያ ለጠብ አጫሪነትን እና ለሁከት ፈጣሪነት ያጋልጣል/ IMPACT on AGGRESSIVE BEHAVIOR and VIOLENCE/
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በትዕይንት መስኮት ሁከትና ብጥብጥ ያለቸውን ነገሮች መመልከት በእውነተኛው ህይወትም የጠብ አጫሪነት እና ሁከት ፈጣሪነት ባህሪያት እንዲጨምር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡ በኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ፊልሞችና ድራማዎች በአብዛኛው በይዘታቸው የጠብ አጫሪነት፣ የሁከት፣ የጥፋት፣ የድብድብ፣ ወዘተ ትዕንቶችን የተካተቱበት በመሆኑ የልጆችን አስተሳሰብ ከፍተኛ ተፅዕኖ በማሳደር እውነተኛው አለም የጥፋትና የሁከት እንደሆነ እንዲያምኑ ምክንያት በመሆን ለጠብ አጫሪነትና መሰል ባህሪያትን እንዲያሳዩ ምክያት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ህፃናት እንደዚህ አይነት ባህሪያት ያሳያሉ ማለት ሳይሆን ዝንባሌ እንዲኖራቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል ለማለት ነው፡፡ ሌሎች ነገሮች ለምሳሌ በአካባቢያቸው የጠብ አጫሪነትና ሁከትን የሚያበረታቱ ሁኔታዎች ከተጨመሩ ከሌሎች ልጆች አንፃር የጎላ የባህሪ ችግሮችን የማሳየት እድላቸው ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
ከቴሌቪዥን በተጨማሪ በስማርት ስልኮችና እና በኮምፒውተር ላይ የሚጫኑ ሁከት እና ብጥብጥን የሚያንፀባርቁ ጌሞች/ጨዋታውች/ በልጆች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን ያሳድራሉ፡፡
.....ክፍል 3 ይቀጥላል