ልጆችን ማበረታታት
ትምህርት ለልጆቻችን የወደፊት ስኬት ዋንኛው መሰረት መሆኑን ሁላችንም እንገነዘባለን፡፡በመሆኑም ወላጆች ልጆቻችን በትምህርታቸው ስኬታማ መሆን ይችሉ ዘንድ ተገቢውን ትኩረት አድርገን መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ልጆችን ማበረታታት ደግሞ የልጆቻችንን ስኬት ዕውን ማድረግ ከምንችልባቸው ቁልፍ ዘዴዎች መካከል ነው፡፡
በወላጅዎች የሚበረታቱ ልጆች ከሌሎቹ የበለጠ ውጤታማ የመሆን ዕድል እንዳላቸው በዘርፉ ጥናት ያካሄዱ በርካታ ሙሁራን ይናገራሉ፡፡ በወላጆቻቸው ተገቢውን ማበረታታት የሚደረግላቸው ልጆች ለትምህርት የሚኖራቸው አመለካከትም እየተስተካከለ እንደሚሄድ ጭምር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የዛሬው መልዕክታችን ርዕሰ-ጉዳይ ልጆችን ማበረታታት ላይ እንዲያተኩር መርጠናል፡፡ ልጆች በምን መልኩ ብናበረታታቸው ስኬታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ የተወሰኑ መንገዶችን እንዲካተት አድርገን ከዚህ በሚከተለው መልኩ አሰናድተን ለማቅረብ ሞክረናል፤ መልካም ንባብ፡፡
1.ከልጅዎ ጋር በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግልፅ እና አዎንታዊ ግንኙነት ተግባራዊ በማድረግ ልጅዎን ያበረታቱ
ይህን ማድረግ በልጅዎ ላይ እጅግ ተፅእኖ መፍጠር የሚችሉበት ታላቅ መሳሪያ ነው፡፡ ለልጅዎ በዚህ ርቀት ቅርብ መሆን ከቻሉ በእርግጥም በሚገባ እያበረታቱት መሆኖን ልብ ይበሉ፡፡
2. በልጅ አስተዳደጎ ሩህሩህ በመሆን ልጅዎን ያበረታቱ
ከሀይልና ከልክ በላይ ቁጥጥር እንዲሁም ቁጣና ቅጣት ታቅበው ለልጅዎ ሩህሩህ ፣ ተባባሪ አና ጽኑ ወላጅ ለመሆን የድርሻዎትን ይወጡ፡፡ከልጅዎ ጋር በሚኖርዎት ቅርርብ ለምትፈጠር እያንዳንዷ አሉታዊ ግንኙነት ብዙ እጥፍ አዎንታዊ አብሮነት በመፍጠር በጊዜ ያብሱት፡፡ልጆችዎን በሆነ ባልሆነ ከመጨቅጨቅና ከማስጨነቅ ይልቅ እነሱን ርህራሄ በተሞላበት ሁኔታ በማገዝና ማበረታታት ላይ ትኩረትዎ እንዲሆን ያድርጉ፡፡
3.ከልጅዎ ጋር የመነጋገር ባህል በማዳበር ልጅዎን ያበረታቱ
ልጆች በትምህርታቸው ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ስለትምህርት ፈላጎታቸው እና ችሎታቸው ማውራት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ወላጆች ልጆቻቸውን ሊያደምጧቸው፣ ጠንካራ ጎኖቻቸውንም እውቅና ሰጥተው ሊያበረታቷቸው ይገባል፡፡ ለምሳሌ “በጣም የምትወደው የትምህርት አይነት ምንድን ነው?” “ እንዴት ይሄ ሊሆን ቻለ?” እያሉ መጠየቅና መወያየት ፋይዳው የላቀ ነው፡፡
4.የልጅዎን የትምህርት ዝንባሌ ዝቅ አድርጎ ባለመመልከት ያበረታቱ
የልጅዎ የትምህርት ምርጫ(ፍላጎት) እርሶ ከሚያስቡትና ከሚጠብቁት የሚቃረን ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን የልጅዎን ፍላጎት ማክበርና በመረጠው ፊልድ ስኬታማ ይሆን ዘንድ ማበረታታት የላቀ ውጤት ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ ልጅዎ የስነ ፅሁፍ ፍላጎት እና ዝንባሌ ያለው ሆኖ እርሶ ግን ንባብ ላይ እምብዛም ስለሆኑ ብቻ ስነ ጽሁፍን ፋይዳቢሰ የትምህርት ዘርፍ (ፊልድ) አድርገው የልጅዎን የአስተሳሰብ ነፃነት መጫን አይገባም፡፡ ባይሆን ልጆዎን በዝንባሌው መሰረት ውጤታማ ይሆን ዘንድ በተለያየ መልኩ ግብዓቶችን በማቅረብ እንዲሁም ወደ ቤተ-መጽሀፍት ይዘው መሄድ ከሁሉም ወላጅ የሚጠበቅ ልጆችን በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ የማበረታታት አይነተኛ ዘዴ ነው፡፡
5. ለልጅዎችዎ ጥረት ተገቢውን ዕውቅና በመስጠት ያበረታቱ
ልጆች ከውጤታማነት በላይ ጥረቶቻቸው በወላጅዎቻቸው ተገቢውን እውቅና ተሰጥቷቸው መመልከት ደስተኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፤ የበለጠም ያበረታታቸዋል፡፡ለልጆቻቸን ጥረቶች ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተን የምናበረታታ ከሆነ ልጆች ከውጤት ባሻገር ትምህርትን ጠንክሮ መማር የበለጠ ዋጋ እንዳለው መረዳት ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ ልጅዎ ፈተና የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግብ ከውጤቱ በላይ ጠንክሮ ማጥናቱ ላይ ትኩረት አድርገው አስተያየት ይስጡ፡፡ “አየህ ለፈተና ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ ከንቱ አልቀሩም፤ በእርገጥም በውጤትህ ተንፀባርቋል፡፡ ” በማለት የልጅዎን ብርቱ የጥናት ሂደት ማበረታታት በልጅዎ የትምህርት ስኬት የላቀ ሚና ይጫወታል፡፡
6.ልጅዎችዎ ውጤት ባያስመዘግቡምኳ የበረታቷቸው
ልጅዎችዎ እንደጠበቁት ውጤታማ ሆነው ሳይገኙ ሲቀሩ ወደፊት እንዴት ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገንቢ ምክሮትን በመለገስ ያበረታቷቸው፡፡ ውጤት ስላልተመዘገበ ብቻ የልጅዎን ጥረትና ድካም በፍጹም ዝቅ አድርገው አይመልከቱ፡፡እነዲህ የሚያደርጉ ከሆነ ልጅዎ ወደፊት ስህተቱን አርሞ፤ ክፍተቱንም ሞልቶ ወደ ውጤታማነት ከመገስገስ ይልቅ ጠንክሮ ማጥናትና ጥረት ማድረጉ ፋይዳ እንደሌለው በማሰብ ፊቱን ከትምህርት ይልቅ ወደ ሌላ በማዞር ቀጣይ የትምህርት ህይወቱ ላይ አደጋ ሊደቀን ፤ስኬታማነነታቸውንም ሊያጨናግፍ ይችላል፡፡ ልጆች ውጤታቸው ምንም ያህል ዝቅ ቢልኳ “ አንተ ሰነፍ፤የማይገባህ፣ ” እና መሰል እጅግ ጸያፍ እና አፍራሽ የፍረጃ ቃላትና ውንጀላዎች ወላጅዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ለልጅዎ ካስመዘገበው ውጤት በላይ እነደሚጠብቁና ለዚህም ተባብሮ ለመስራት እስከመጨረሻው
ዝግጁነትን ከማንጸባረቅ ውጭ ልጆችን በወቀሳ ናዳ ማስበርገግ ፤ በዛቻ ማዕበል ማጥለቅለቅ የማበረታታት ተቃራኒ የስኬታማነትም ፀር ነው፡፡
7.በልጅዎችዎ ላይ የሚተገብሯቸው የቅጣት ዕርምጃዎች ሁሉ ልጆችዎ የተሻሉ ሆነው ይቀረጹ ዘንድ ለማበረታተት እንጂ ለሌላ አለመሆኑን በተግባሮትና በቃልዎ ይረጋግጡላቸው፡፡
ለምሳሌ “አበዛኛውን ሰዓት ለቲቪ ሰጥተህ ከጥናትህ በመዘናጋትህ ውጤትህ ምን ያህል መበላሸቱን ተመልከት?!” ብሎ መገሰጥም ልጆችን ከአገጓጉል ተግባራት እንዲታቀቡ በመርዳት ማበረታታት ሊሆን የችላል፡፡
8..ለልጅዎ ውጤታማነት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ያበረታቱ፤የአጠናን ዘዴዎቻቸውንም ይፈትሹ
የተለያዩ የመማር ወይም የጥናት ዘዴዎችን ለልጆችዎ በማመላክትም ማበረታታት ይችላሉ፡፡ ልጆች መጽሀፍና ደብተሮቻቸው ላይ አፍጥጠው እንዲታዩ ብቻ ማስገደድ ልጆችን ከማሸማቀቅና ከማሰልቸት የዘለለ ሚና ላይኖረው ይችላል፡፡ ልጆች ጥናታቸውን በተገቢ መልኩ እንዲያካሂዱ የሚመቻቸወን የጥናት ዘዴ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከነሱ ጋር በጋራ መወያየት እና መመካከር ያስፈልጋል፡፡ የልጅዎችዎን መምህርም በዚህ ዙሪያ እያወያዩ ፤ ጥናት ፕሮግራም በማዘጋጀት ክትትልና ድጋፎችን በማድረግ ማበረታታት ልጅዎን የላቀ ውጤት ባለቤት እንዲሆን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
ስለዚህ ሁላችንም ልጆቻችንን በተገቢው ሁኔታ ሳንታክት በማበረታታት ስኬታቸው ዕውን ይሆን ዘንድ ሁሌም ከጎናቸው ልንሆን ይገባል፡፡