እንግሊዝኛ ቋንቋን መልመድ የሚቻለው እንዴት ነው?
ውድ ወላጆች፡-
የምርምር ጥናት እንደሚያሳየው: በልጅነት እድሜ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋዎችን መማር፤ለአእምሮ መዳበር ይረዳል፡፡ ከአንድ ቋንቋ በላይ መናገር የልጆችን አእምሮ ያዳብራል። እንዲሁም በበለጠ የፈጠራ አስተሳሰብ እንዲኖራቸውና ለችግሮች በቀላሉ መፍትሄ ማግኘት እንዲችሉ ይረዳል። ብሎም ልጆች የተሻሉ አንባቢዎች፣ አድማጮችና በቀላሉ ተግባቢዎች እንዲሆኑ ይረዳቸዋል። የማስታወስ፣ የማስተዋል ትኩረትና የቁጥር ትምህርት ችሎታንም ያዳብራል፡፡
በዚህም መሰረት የዛሬው ሳምነታዊ መልዕክታችን ከቋንቋ በተለይ አለማቀፍ በሆነው እንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡ መረጃውን ያጋራን EM ነው፡፡ መልካም ንባብ፡፡
እንግሊዝኛንም ሆነ ማንኛውንም ቋንቋ ለመልመድ፣ በመጀመሪያ ደፍረን መናገር መቻል አለብን። ትንሽም ትሁን የምናውቃትን ቃል እየደጋገምን መናገር አለብን! መናገር ስንጀምር ነው ሁ ሉ ም ነገር ፈር እየያዘ የሚሄደው!
አብዛኞቻችንኮ በርካታ የእንግሊዝኛ ቃላትንና ሀረጋትን እናውቃለን፤ እንዲሁም ሙሉ ዓረፍተ ነገሮችን መመስረት እንችላለን፤ ነገር ግን የመናገር ልምድ ስለሌለን መናገር ይከብደናል። የምናውቀውን ቃላትና ህግጋት እንዴት አሰካክተንና ቅደም ተከተል አሲዘን መናገር እንደምንችል አናውቅም። ለመናገር አንደፍርም፤ እንፈራለን። ሰው ምን ይለኝ ይሆን የሚል ይሉኝታ ያሸማቅቀናል።
ምን መሠላችሁ፣ ችግሩ ያለው አመለካከታችን ላይ ነው። እንግሊዝኛ ለመናገር መፍራት የለብንም;; ፈረጆቹኮ አማርኛ ሲናገሩ በፍፁም አይፈሩም ወይም ደግሞ አያፍሩም። የፈለገ ቢሰባብሩትም ዘና ብለው ነው የሚናገሩት። ትንሽ አማርኛ ካወቁ "አማርኛ እንችላለን!" ብለው ያስባሉ። እኛ ሁልጊዜ በመማርና በማጥናት ላይ ነው ትኩረታችን። ቲዮሪ ብቻ ፋይዳ የለውም ተግባር ነው ዋናው።
የፈለገ Vocabulary ብናውቅ የፈለግ Grammar ብናጠና፣ የተማርነውን ነገር ካልተለማመድነው ወይም ባገኘነው አጋጣሚ ውስጥ ጣልቃ እያስገባን ካልተጠቀምነው፣ እንረሳዋለን። ትርጉሙ፣ ህጉና አገባቡም ይጠፋብናል፥ እውቀታችን አይዳብርም! ልምዳችን አይጨምርም። ልጆቻችን በእንግሊዝኛ የመናገር ልምድ ሲያዳብሩ ፣ በራስ መተማመናቸውም ይጨምራል። በዚህ ሰአት ያለ ምንም ጭንቀት መናገር ይጀምራሉ።
እንደዚህ ሲባል ግን ቃላትን፣ ግራመርን ወይም ስፖክን ኢንግሊሽን ማጥናት የለባቸውም ማለት አይደለም። እነዚህን ነገሮች ማጥናት በጣም አስፈላጊ ነው። ገቢ ከሌለ ወጭ አይኖርም። ከየት አምጥተው ያወጡታል? If there is no input, there is no output. ይላሉ ፈረንጆቹ። ገቢ ሲኖር ነው ወጪም የሚኖረው። ስለዚህ ማጥናት የግድ ያስፈልጋል። ነገር ግን ያጠናነውን ነገር በደንብ እየደጋገምን መለማመድ አለብን። አንድ ጊዜ ብቻ አንብቦ ወይም አድምጦ ዘወር ማለት በቂ አይደለም።
የምንፈራው ለተወሰነች ጊዜ ብቻ ነው፤ ከዛ ፍርሃታችን እኛኑ እስከሚደንቀን ድረስ ለቆን ይጠፋል። አንድ ማወቅ ያለብን ነገር አለ፣ ማንኛውንም ነገር በትክክል መሥራት የምንችለው ብዙ ጊዜ ካጠፋንና ከተሳሳትን በኋል ነው። ይህን ማወቅ አለብን። ካልተሳሳትን ደግሞ እየሞከርን አይደለም፤ ካልሞከርን፣ ምንም ነገር ማሳካት ወይም ከእቅዳችን መድረስ አንችልም ማለት ነው። አስታውሱ፣ ትንሽም ትሁን የምናውቃትን ቃል እየደጋገምን መናገር አለብን! መናገር ስንጀምር ሁ ሉ ም ነገር ፈር እየያዘልን ይመጣል!ሲል የመረጃ ምንጫችንን የቀረበውን መልእክት ከጥቂት ማስተካከያ ጋር እንዲህ አጋራናችሁ፡፡
በትምህርት ቤታችንም የእንግሊዝኛ ቋንቋ በትምህርት ዓይነትና በማስተማሪያ ብሎም በመግባቢያ ቋንቋነት እየተሰጠ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ተማሪዎች በድፍረት ቋንቋውን እንዲጠቅሙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያግዙ ሪዲንግ ካምፔይን ፣ ስፔሊንግ ቢ፣ዲቤት ፣ ስቶሪ ዴይ ፣ሞቲቬሽናል ስፒች እና ግራንድ ኢንግሊሽ ዴይ የመሳሰሉ ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ስለዚህ ወላጆች፡-
ከላይ እንግሊዝኛ ቋንቋን ለመልመድ የቀረበውን ጠቃሚ መልዕክት ከልጆች ጋር በመወያያት እና ለተግባራዊነቱ ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ተማሪዎቻችን የሚማሩትን ትምህርት በአግባቡ እንዲረዱና ውጤታማ እንዲሆኑ እንግሊዝኛ ቋንቋን የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመናገርና የማዳመጥ ክህሎታቸውን በሚገባ በማሳደግ አለም አቀፍ ተወዳደሪ ይሆኑ ዘንድ እየተደረገው ያለውን ጥረት በማገዝ የጋራ ሓላፊነታችንን ዕንወጣ ስንል የዛሬውን መልዕክታችንን አጠናቀቅን፡፡