Postlar filtri


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጎዴ የተገነባውን የኮር ጠቅላይ መምሪያ ካምፕ መርቀው ከፈቱ።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ በሶማሌ ክልል ጎዴ የተገነባውን የመከላከያ ሠራዊት የኮር ጠቅላይ መምሪያ ካምፕ መርቆ ከፍቷል።

በመርሐ ግብሩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኝ፣ የመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያ ኀላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ፣ የምሥራቅ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተስማ፣ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አብዲ አሊዚያድን ጨምሮ ከፍተኛ የሠራዊት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


"ኢትዮጵያ የዓለም ሥርአት ቅርጽ እንዲኖረው በማድረግ ባለክብር ናት" በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኢሚስበርገር

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሠረቱበትን 50ኛ ዓመት አክብረዋል።

በመግለጫቸውም ኅብረቱ እና ኢትዮጵያ ሰላም፣ ደኅንነት፣ ሽብርን መከላከል፣ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ውህደት እና ለብልጽግና መትጋት አንድ የሚያደርጓቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።

የአውሮፓ ኅብረት የሕግ የበላይነት እንዲከበር፣ ሰላም እና መረጋጋት አንዲሰፍን ውይይት እና ሀገራዊ ምክር ቀዳሚ ስፍራ እንዲይዝ የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለብዙ ወገን ድፕሎማሲ ተምሳሌት መኾኗን ጠቅሰዋል። "ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት እንዲመሠረት በማድረግ የዓለም ሥርአት ቅርጽ እንዲኖረው በማድረግ ባለክብር ናት" ነው ያሉት።


https://vm.tiktok.com/ZMBF1oyCu/
Amhara Media Corporation is LIVE | TikTok
Check out Amhara Media Corporation LIVE videos on TikTok! Watch, follow, and discover the latest content from Amhara Media Corporation.


በአሚኮ ቲክቶክ በቀጥታ እንመካከር!

በአማራ ክልል ባለው የትምህርት መስተጓጎል ዙሪያ ዛሬ ከ10፡30-11፡30 በአሚኮ ቲክቶክ በቀጥታ መስመር ላይ እንመካከራለን ይጠብቁን፡፡
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ


"መትጋት፥መሥራት፥ ማየት ከቻልን፣ ኢትዮጵያ ከመረዳት አልፋ ሌሎችን መርዳት ትችላለች" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በምሥራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ልማትን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በምሥራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ልማትን ተመልክተናል። መትጋት፥መሥራት፥ ማየት ከቻልን፣ ኢትዮጵያ ከመረዳት አልፋ ሌሎችን መርዳት ትችላለች። ይህንን ስራ አጠናክረን እንድንቀጥል አደራ እላለሁ ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!


ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ።

ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ እና ምክትል ርእሰ አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ኮምቦልቻ ከተማ ገብተዋል።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ወሎ ዞን፣ የደሴ ከተማ አሥተዳደር እና የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር መሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ በደሴ በሚኖራቸው ቆይታ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!


https://www.ameco.et/72071/
ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው አብሮነትን ሊሸረሽሩ የሚችሉ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ አካላትን በጽኑ እንደሚያወግዝ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ።


https://www.ameco.et/72068/
“ባለፉት ሰባት ዓመታት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የኮሚኒኬሽን ዘዴ ለየት ባለ መንገድ ግልጽነት እና ተደራሽነትን በማለም የተከናወነ ነው” ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት


አሚኮ እለታዊ የምንዛሬ መረጃ
መጋቢት 2/2017 ዓ.ም


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ጥቂት ስለ ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ !
👉በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ የሚገኘው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ እና ቋሚ የሥራ እድል ፈጥሯል
👉ፋብሪካው ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን 7 ሚሊየን ኩንታል ሲሚንቶ ለገበያ አቅርቧል
👉አሁን ላይ በቀን 100 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ እያመረተ ነው
👉በኢትዮጵያ 33 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሲሚንቶ አቅርቦት መሸፈን ችሏል
👉ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በ2017 በጀት ዓመት የጥንካሬ ደረጃዎችን ካሳኩ አቻ ኢትዮጵያዊያን ምርቶች በጥራት ተሸላሚ መሆን መቻሉም ተመላክቷል፡፡
👉በአማራ ክልል ግዙፍ ፋብሪካዎች ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ትልቅ ማሳያ ነው።


#አንኳር
"የዘንድሮውን የሴቶች ቀን ከአዳራሽ ውይይት እና ቀኑን አስቦ ከመዋል ባለፈ የሴቶችን ተጠቃሚነት እና ተሳታፊነት ባረጋገጠ መልኩ በልዩ ልዩ ኹነቶች በድምቀት ማክበር ተችሏል"
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ


አሚኮ እለታዊ የምንዛሬ መረጃ
መጋቢት 1/2017 ዓ.ም


የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት!

ዛሬ የስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንደስትሪን መርቀናል።

ከጥቂት ዓመታት በፊት በሀገር ውስጥ ድሮን ስለማምረት ማሰብ የማይታሰብ ነበር። ብዙ አይነት ችሎታ ያላቸው ድሮኖችን በራሳችን ባለሞያዎች ዲዛይን አድርጎ የማምረት አቅም ትልቅ የታሪክ እጥፋት ነው። ይኽን እድገት ለማዝለቅ ቀጣይነት ባለው የምርምር ሥራ ላይ፣ ገበያ በማስፋት ተግባር ላይ እና በሀገር ውስጥ የስማርት ሴንሰር ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ላይ መሥራት ይገባናል።

እንደዚህ እና እንደሆሚቾ የተተኳሽ ኢንጂነሪንግ ፋብሪካ ያሉትን አቅሞቻችንን የምናሳድገው ግጭትን ለማቀጣጠል አይደለም። ግጭትን ለማስቀረት እንጂ። ግጭትን በሚፈልጉ ተዋንያን ፊት ግጭትን ለማስቀረት የሚችል አቅም በመፍጠር ሰላም እና መረጋጋትን ለማፅናት ነው ፍላጎታችን።


ጠንካራ ሀገር የመገንባት ግብን መሠረት በማድረግ ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸውን ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።

ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተጠናቅቋል።

ስኬቶችን ለማስቀጠል፣ ክፍተቶችን ለመሙላት እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ተጠቁሟል።

ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ፣ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ እና ከተረጂነት መላቀቅ ሀገራዊ ግብን ለማሳካት የተሠሩ ውጤታማነት ሥራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።


https://www.ameco.et/72026/
ጠንካራ ሀገር የመገንባት ግብን መሠረት በማድረግ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።


#አንኳር
"የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው ነፃነት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፤ ማኅበራዊ እሴቶችና ባሕሎችን ለማፅናት ያበረከቱት አስተዋፅዖ የላቀ ነው፤ እንቅፋቶችን እና ጎታች እሳቤዎችን በመጣል፣ በመላ አቅማቸው የሀገራችን የመዘመን መንገድ ዋነኛ መሪና ተዋናይ መኾናቸው እሙን ነው"
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ


https://www.ameco.et/71998/
የሕዝብ ውክልናን ለመወጣት የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ አሳሰቡ።


ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።
ደሴ: የካቲት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለ16ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 320 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!


በሚሊዮኖች የምትጎበኘው ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ የምትገኘው የጻድቃኔ ማርያም መካነ ቅዱሳን ገዳም በሰላ ድንጋይ ከተማ አቅራቢያ ትገኛለች። ቦታው ከክልሉ ርእሰ ከተማ ባሕር ዳር 767 ኪሎ ሜትር፣ ከአዲስ አበባ 202 ኪሎ ሜትር እና ከዞኑ ርእሰ ከተማ ደብረ ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

ይህ ቅዱስ ሥፍራ በአፄ ዘርዓያዕቆብ እንደተቆረቆረ ሊቃውንቱ ይናገራሉ ። ጽላቷ ወደቦታው ስትመጣ ንጉሠ ነገሥቱ በእልልታና በደስታ ተቀብለው በዘመኑ ለነበሩት ካህናትና ዲያቆናት አስረከቧቸው፡፡
ቀጥሎም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ጅባት ከተባለው ከተማ ወደ እንጦጦ አምጥተው ለብዙ ጊዜ አስቀምጠዋታል፡፡ እንደገናም ከእንጦጦ አንስተው ወደ ደብረ ብርሃን አመጧት።
ከዚያም አሁን ወዳለችበት አካባቢ ወደ ሰላ ድንጋይ ሞሊያ በተባለው ከፍተኛ ቦታ ለብዙ ዓመታት መቆየቷን የገዳሟ መረጃ ይጠቁማል።

https://ameco.et/tourism/953/

19 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.