እንደ ቀላል አትዩት‼
ልጅቱ እንዲህ ትላለች
ከወራት በፊት ከቤት ልወጣ አሰብኩና ከነበሩኝ ሽቶዎች የበለጠ መልካም መዐዛ ያለውን ለመቀባት ወሰንኩ ፤ በእርግጥ ሴት ልጅ ሽቶ ተቀብታ መውጣት እንደሌለባትና ሽቶ ተቀብታ ከቤት መውጣቷ ከባድ ወንጀል እንደሆነ አውቃለሁ ፤ ነገር ግን ማንም ወንድ አያሸተውም ትኩረታቸውንም አልስብም እንዲሁም ከሴት ጓደኞቼ ጋር ስገናኝ ከኔ መልካም ሽታ እንዲያገኙ ብዬ በማሰብ ነበርና ለጥንቃቄም ብዬ ሁለት ሶስት ጊዜ ብቻ ነበር የተቀባሁት። የሆነው ሆኖ ከቤት ውስጥ ሆኜ በአፕሊኬሽን ኡበር ታክሲ ጠራሁና መንገዴን ጀመርኩ። ሹፌሩ እጅግ ዝምተኛና ስርአት ያለው ሰው ነበር ፣ መድረስ ከፈለግኩበት ስፍራም እንደደረስኩ ክፍያዬን ፈፅሜ ወረድኩ። ከታክሲ ከወረድኩ ሰላሳ ደቂቃዎች በኃላ ሞባይል ስልኬ ላይ መልዕክት ደረሰኝ ፤ ቁጥሩ ለኔ እንግዳ ነበር ፤ ማነው የማላውቀው ሰው ደሞ መልዕክት የላከብኝ ብዬ እራሴን እየጠየቅኩ መልዕክቱን ከፈትኩት፤
መልዕክቱ እንዲህ የሚል ነበር፦
『በጣም ውብ ነሽ በተለይ የተጠቀምሽው ሽቶ ደግሞ መዓዛው ልዩ ነው።』
ወይ ጥፋቴ ! ለካስ መልዕክቱን የላከው ያደረሰኝ የታክሲ ሹፌር ሆኗል ፤ በቃ ይህንን መልዕክት ሳነብ ሰውነቴን ሁሉ ነዘረኝ አለቀስኩም ፤ እጅግ ተፀፀትኩ ፤ ወደ ቤትም ተመልሼ ረከአተይን ሰገድኩና ወደ ጌታዬ ተፀፅቼ መሀርታን ጠየቅኩት ፤ ፊት ለፊቴ የመጣው ያ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ንግግር ነበር ፤ እንዲህ የሚለው ንግግራቸው፦ 【የትኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ ሰዎች እንዲያሸቱላት (ትኩረታቸውን ለመሳብ) በአጠገባቸው ካለፈች እርሷ ዝሙተኛ ናት።】
እናም እህቶቼ ነገሩ ከባድ ነው እንደምናስበው ቀላል አይደለምና እንጠንቀቅ !
http://t.me/AshaBuleyamine