ቤስት - ሚዲያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


🇪🇹🇪🇹🇪🇹ስለ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀን በቀን የሚወጡ ዜናዎችን እና እንዲሁም አለም አቀፍ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን 🙏ሰላምና ፍቅር ለእናት ሀገራችን ይሁን❤
👉 ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @Gebrel or @Wizbeki7 ያናግሩን።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




ጎልልልልልልልልልል ሮናልዶዶዶዶ

ሮናልዶ አሁን ለአል ናስር ተገልብጦ ያስቆጠራትን አስደናቂ ኳስ ይመልከቱ 👇👇
https://t.me/+4JpAYkA-01QyMDU8


ፒኤስፒ ከ ሊቨርፑል የሚያደርጉትን የቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በስልኮ ለመከታተል LIVE ሚለዉን ይጫኑት 👇👇👇
https://t.me/addlist/fDJhM0jRWXAwOGVk






የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ያበሻቀጡት የአሜሪካው ም/ፕሬዚደንት ጄዲ ቫንስ ቤተሰብ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩክሬን ደጋፊ ተቃዋሚዎች የቬርሞንት የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያውን ካጨናነቁ በኋላ ወደ 'ያልታወቀ ቦታ' ተዛውረዋል።

@Ethiobestzena


❗ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እኔን መተካት ከባድ ነው አሉ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሀገራቸው የኔቶ አባል ከሆነች በምትኩ ስልጣን እንደሚለቁ ተናግረዋል

የአሜሪካ ፖለቲከኞች ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለቦታው አይመጥኑም የሚል ሀሳቦችን እያንሸራሸሩ ይገኛሉ

@Ethiobestzena


ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ ይጠበቅባቸዋል ተባለ

ደንበኞች የብሔራዊ መታወቂያ ከሌላቸው የተቋሙ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉም ተነግሯል

የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ አክስዮን ማህበር ከዛሬ የካቲት 24 ጀምሮ መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ከፍተኛ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ወይዘሮ እስራኤል ወልደመስቀል ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የመንገደኞችን እንግልት ለመቀነስና ለጋራ ደህንነት መንገደኞች ከዛሬ ጀምሮ የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት በመቁረጥ አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ተደርጓል።

ማህበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ዲጂታላይዝድ ማድረጉን የገለጹት ባለሙያዋ፤ ደንበኞች የብሔራዊ መታወቂያ ከሌላቸው የተቋሙ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉም ተናግረዋል።

ይህንንም ለደንበኞች የማሳወቅ ሥራው ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ ሲሰራ እንደነበርና ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር መታወቂያውን እንዲያገኙት እየተደረገ እንደነበር አስታውሰዋል።

የብሔራዊ መታወቂያ ተግባራዊነቱ ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ብቻ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ተጠቃሚዎች ፓስፖርታቸውን በመጠቀም ትኬት ማግኘት እንደሚችሉ ወይዘሮ እስራኤል ገልጸዋል።

በኦንላይን ትኬት የመቁረጥ አገልግሎት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል።

@Ethiobestzena


አውሮፓ የሩሲያን ጥቃት ለመመከት ተጨማሪ 1000 የኑክሌር አረሮች ያስፈልጓታል ተባለ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ለአውሮፓ የሰጡትን የደህነት ዋስትና ያነሳሉ የሚለው ስጋት አውሮፓውያን ከአሜሪካ ነጻ ሆነው ራሳቸውን የሚከላከሉበትን ለመቀየስ እየወያዩ ይገኛሉ።

@Ethiobestzena


ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ስርቆት እና ውድመት እንደተፈጸመበት አገልግሎቱ አስታወቀ

በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሰባት ወራት 50 ሚሊየን 222 ሺህ 987 ነጥብ 7 ብር የሚገመት የንብረት ስርቆት እና ውድመት እንደተፈጸመበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ በ22 የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች ላይ ርምጃ መውሰዱንም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የተፈፀመው ስርቆትና ውድመትም የኃይል ስርቆት፣ የትራንስፎርመር ስርቆት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ጉዳት፣ የመሰረተ ልማት ስርቆት፣ የተቋሙ ሠራተኞችን ሥራ እንዳይሠሩ ማወክና የኬብል ስርቆትን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጿል።

በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ 163 የኃይልና መሰረተ-ልማት ስርቆት ወንጀል መፈጸሙን የገለጸው ተቋሙ ከእነዚህ መካከል 11 የወንጀል ጉዳዮች ውሳኔ ማግኘታቸውን አስታወቋል። በዚህም 13 ተከሳሾች ከሁለት ወር ቀላል እስራት እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ መቀጣታቸውን አክሎ ገልጿል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ከ መተሃራ እስከ ባቡር ትራክሽን ጣቢያ አንድ ድረስ ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና 25 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የኦፕቲካል ፋይበር መስመር በአስር ቀናት ውስጥ መዘረፉን ተቋሙ ማስታወቁ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እያለ ከደንበኞች የቀረቡ የብልሹ አሠራርና ሙስና ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ በ22 አመራርና ሠራተኞች ላይ አሥተዳደራዊ ርምጃ መውሰዱንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመግለጫው አስታወቋል፡፡ በዚሁ መሠረት አስፈላጊው ማጣሪያ ተደርጎ ሦስቱ በጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እና 19ኙ ደግሞ በደመወዝ ቅጣት መቀጣታቸውን ነው ያስታወቀው፡፡

@Ethiobestzena


🚨ነዳጅ

የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።


➡ አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር

➡ አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር

➡ አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር

➡ የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር

➡ አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

➡ አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር

@Ethiobestzena


በቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ

በቶኪዮ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቅቀዋል።

በወንዶች ታደሰ ታከለ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ አትሌት ሱቱሜ አሰፋ በበላይነት አጠናቅቃለች።

በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው ማራቶን በሴቶች አትሌት ሱቱሜ አሰፋ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች።

በወንዶች የቶኪዮ ማራቶን አትሌት ታደሰ ታከለ በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቱን ጭምር በማሻሻል አሸንፏል።

አትሌት ደረሳ ገለታ በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

@Ethiobestzena


ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) የአድዋ ድል በዓልን በማስመልከት ያስተላለፈው መልዕክት።

@Ethiobestzena


የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለእስራኤል የ4 ቢሊዮን ወታደራዊ እርዳታ በአስቸኳይ እንዲደርሳት ማዘዛቸውን ገለጹ

የትራምፕ አስተዳደር በቅርብ ሳምንታት ውስጥ መሳሪያዎችን በፍጥነት ለእስራኤል ለመሸጥ የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን ሲጠቀም ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተብሏል።

@Ethiobestzena


"የገሃነም በሮች የሚከፈቱበት ጊዜ አሁን ነው

መብራት እና ውሃ ማቋረጥ፣ ወደ ጦርነት መመለስ - "

የእስራኤል የቀድሞ ባለስልጣን ቤን ጊቪር ወደ ጋዛ ከበባ ፈጣን እና ጭካኔ የተሞላበት መመለስን ደግፈው ተናገረዋል።

@Ethiobestzena


❗የውጭ ዜጋ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ የሚያግድ ሕግ እየተዘጋጀ ነው

የአሜሪካው ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የገንዘብ እርዳታ ካቆመ ወዲህ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች መካከል 85 በመቶዎቹ ሥራቸውን ማቆማቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

በተለይ በሰብዓዊ መብቶች፣ በሰላም፣ በጤና እና ልማት ዘርፎች የሚሠሩ ድርጅቶች ይበልጥ ተጎጂ እንደኾኑ የጠቀሰው ዘገባው፣ በትግራይ ለ100 ሺሕ የጦርነት ተፈናቃዮች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያቀርብ የነበረ መንግሥታዊ ያልኾነ ድርጅትም ሥራ ማቆሙን አመልክቷል።

መንግሥትም፣ የውጭ ዜጋ የሆኑ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ የሚያግድ ሕግ እያዘጋጀ መኾኑን ምንጮች መናገራቸውን የዜና ምንጩ ዘገባ ያመለክታል።

@Ethiobestzena


ዓድዋ‼️

"ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል!"
እንኳን ለ129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ -አደረሰን!

@Ethiobestzena


የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ እንዳስታወቀው አብዳላቲ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በአህጉራዊ የጋራ ጉዳዮች በተለይም በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላምና ደህንነትን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፣ በሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እና ሉዓላዊነቷን በሁሉም ግዛቶቿ ላይ ለማስረፅ የሚያስችል የሃሳብ ልውውጥ ተካሂዷል።

ስብሰባው በሊቢያ እና በአፍሪካ ቀንድአካባቢ ስላለው ሁኔታ እንዲሁም በቀይ ባህር ውስጥ ያሉ ለውጦች እና ማንኛውም ቀይ ባህር አካል ያልሆነ መንግስት በፀጥታ እና በአስተዳደር ውስጥ ተሳትፎን ውድቅ በማድረግ ላይ ትኩረቱን አድርጓል ።

በተጨማሪም በጥቅምት 2024 በኤርትራ ከተካሄደው የመጀመሪያው የመሪዎች ጉባኤ በኋላ ተመሳሳይ የሚኒስትሮች ስብሰባዎችን በሞቃዲሾ እና በአስመራ ለማካሄድ እና በቅርቡ ለሁለተኛው የፕሬዝዳንት ጉባኤ ለመዘጋጀት መምከራቸውን አብዳላቲ ጠቁመዋል።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በበኩሉ ትላንት ምሽት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዳላቲ ከተመራ ልዑካን ጋር በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይቶች ማድረጋቸውን አስታውቋል፡፡

በሱዳን ሶማሊያ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በቀይ ባህር አካባቢዎች የሰላም እና የደህንነት ፈተናዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት መካሄዱንም መግለጫው አክሏል፡፡

@Ethiobestzena


❗ግብፅ ኢትዮጵያ የባህር ሃይል እንድታቋቁም አልፈቅድም አለች

ወደብ አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ በቀይ ባህር የራሷን ወደብ ለማግኘት እና የባህር ሀይል ለመቋቋም እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል።

ግብጽ የቀይ ባህር አካል ያልሆነ ማንኛውም ሀገር በባህሩ ዙሪያ የሚያደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና የባህር ሀይል ለማቋቋም የሚደረግ ጥረት እንደማትቀበል አስታወቀች፡፡

ይህ የተባለው በግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዳላቲ የተመራ ልዑክ በኤርትራ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ነው፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት የቀይ ባህርን ጨምሮ የጋራ በሚያደርጓቸው ቀጠናዊ እና በተለያዩ መስኮች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ተስማተዋል፡፡

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር “የቀይ ባህር ደህንነት በተዋሳኝ ሀገራቱ ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው ፤ምንም አይነት ወታደራዊም ሆነ የባህር ሃይል በአካባቢው መገኘትን አንፈቅድም” ብለዋል።

አክለውም “ወደብ አልባ ሀገራት በቀይ ባህር ዙሪያ የባህር ሀይል ማቋቋም የቀጠናውን እና የባህሩን ደህንነት ለመጠበቅ የተደረሰውን ስምምነት ክፉኛ የሚጎዳ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

@Ethiobestzena


🚨ከዛሬ ለሊት 6:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ ነገ 7:00 ሠዓት ድረስ መንገዶች ይዘጋሉ።

129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ነገ ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይከበራል።

ይህን ተከትሎ ፦

- በቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት
- ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር
- ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጎል አደባባይ
- ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት
- ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ
- ከእንቁላል ፋብሪካ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ዮሐንስ መብራት የሚወስዱት መንገዶች ከዛሬ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ከለሊቱ 6፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

ህብረተሰቡም ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በ 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም የሚቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

@Ethiobestzena

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.