Postlar filtri


ማስታወቂያ

ጉዳዩ፡- የብሄራዊ ድህረ-ምረቃ (NGAT) መግቢያ ፈተና እና ምዝገባ ቀናት    የተራዘሙ መሆኑን ስለማሳወቅ

በ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ዙር የNGAT አመልካቾች ምዘገባ መጋቢት 01/2017 መጠናቀቁ እና ፈተናው መጋቢት 05/2017 ከ3፡00 ጀምሮ  እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወሳል።  ይሁን እንጂ በአንዳንድ ተፈታኞች ጥያቄ መሰረት ምዝገባው እስከ መጋቢት 04/2017 ዓ.ም እስከ ምሽቱ 12:00 የተራዘመ ሲሆን ፈተናው ደግሞ መጋቢት 12/2017 ከ3:00 ጀምሮ ይሰጣል።

በዚሁ መሰረት በተለያየ ምክንያት ምዝገባ ያመለጣችሁ አመልካቾች ምዝገባችሁን ቀደም ሲል በተገለጸው ሊንክ በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ፈተናውን ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ስዓት በምትመደቡበት የፈተና ማዕከላት ተገኝታችሁ እንድትፈተኑ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
1. ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል በምትሄዱበት ወቅት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
2. ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት ይጠበቅበታል፡፡
3.  የሞባይል ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
4. የፈተና ማዕከላት ምደባ በምዝገባ ፕላትፎርም የሚገለጽ ይሆናል፡፡


መጋቢት 02/2017
የጤና ሚኒስቴር ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ከ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ በእርዳታ መልክ ሰጠ፡፡
*******
የማስተማሪያ ሆስፒታሉን የጤና አገልግሎት ሥራን ለመደገፍና ደረጃዉን ለማሻሻል ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅርበት ሲሰራ የቆየ መሆኑን በርክክቡ ወቅት የተገኙት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የጤና ኢንስቲትዩት ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳፋይ ኤለማ ገልጾዋል፡፡

አያይዘዉም ዶ/ር ሳፋይ በድጋፍ መልኩ የተሰጡ ቁሳቁሶች በአሁኑ ሰዓት ለሆስፒታሉ በጣም አስፈላጊና እጥረት የሚታይባቸዉ ቁሳቁሶች መሆናቸዉን በመጥቀስ ለተደረገዉ ድጋፍም ምስጋናቸዉን አቅርቧል፡፡

የህክምና ቁሳቁሶቹ ድጋፍ የተደረጉት በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ድርጅት በኩል ሲሆን የቀረቡ ቁሳቁሶችም Warmer-radiant infant, Refrigerator- Blood Bank, phototherapy ,Couch Examination Adult ,Couch Delivery ,Bed-patient adult ,Unesthesia Machine እና የመሳሰሉት ቁሳቁሶች መሆናቸዉን ከመረካከቢያ ሰነዱ ላይ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡


አሬሮ የካቲት 30/2017 ዓ.ም (ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ)
ከቡሌ ሆራ ዩኒሸርሲቲ የተወጣጡ የልኳን ቡድን በ72ተኛው የቦረና ባሊ ስልጣን ሽግግር ላይ ተገኙ።
********
በገዳ እና ባህል ጥናት ኢንስቲትዩት የሚመራዉ የልኳን ቡድን ከስረዓቱ አንድ ቀን በፊት በአሬሮ ወረዳ አረዳ ጅላ በዳሳ በመገኘት በ72ተኛዉ የቦረና ባሊ ርክክብ ላይ ታድመዋል።

የስልጣን ርክክቡ ከፋላሳ ጎጌሳ አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ኩራ ወደ መርዲዳ ጎጌሳ አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የስልጣን ርክክቡ ተከናዉነዋል። በስርዓቱ ላይ ከሀገር ውስጥ እና ከዉጭ ሀገር ትላልቅ የመንግስት ባለስልጣናት ፣የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕረዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ ታዋቂ ሙዚቀኞች ፣ አባ ገዳዎች እና ሌሎች ታዳሚዎች የተሳተፋ ሲሆን ፣ ስረዓቱ በደማቅ ሁኔታ ተከናዉነዋል።

በስረዓቱ ላይም የገዳ የእርከን ደረጃ የሚያሳዩ ደበሌዎች፣ ትንሹ ጋሜ፣ ትልቁ ጋሜ፣ ኩሳ፣ ራባ ፣ዶሪ ፣ገዳ ፣ዩባ1ኛ እስከ ዩባ 3ተኛ እንዲሁም ገደሞጂ ጭምር ተገኘተዋል።በተጨማሪም የተለያዩ የባህላዊ መገልገያ መሳሪያዎች፣ የባህላዊ አለባበስ እና ባህላዊ ገልማዎች በመዘጋጀት ለእይታ ለታዳሚዎች ቀርበዋል።

የቡሌ ሆራ ዩኒሸርሲቲ







6 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.