የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማውን አካሄደ።
ባንኩ በመጀመሪያ ስድስት ወራት ከፍተኛ የተሰብሳቢ ብድር እንደነበረው ነው የተገለጸው።
ጥር 23 እና 24 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ባካሄደው የግምገማ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች እና የማኔጅመንት አባላት፣ የዋና መስሪያ ቤት ዳይሬክተሮች፣ የዲቪዠን ኃላፊዎች፣ የዲስትሪክትና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በተገኙበት ተካሂዷል።
የኢትዮጽያ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ በግምገማ መርሃ ግብሩ ወቅት እንዳሉት በየደረጃው ያለው የባንኩ አመራርና ሰራተኛ የተሰጡ ብድሮችን ተከታትሎ ማስመለስ እና አዳዲስ የሚሰጡ ብድሮች ጊዜያቸውን ጠብቀውና ጤናማ ሆነው እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።
የቦርድ ሰብሳቢው አክለውም ባንኩ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውጤታማ ለማድረግ አመራሩና ሰራተኛው ሌት ከቀን መስራት እንደሚገባ ነው የጠቆሙት።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት አፈጻጸም ባንኩ አጠቃላይ በብድር መልቀቅ፣ በብድር መሰብሰብ እና ሌሎች የባንኩ ዋና ዋና ተግባራት ያስመዘገባቸውን መልካም ውጤቶች ማስቀጠል እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ወራት የባንኩ ማኔጅመንትና ሰራተኞች በከፍተኛ ርብርብ በመፈጸም ባንኩ የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግብ መስራት እንደሚገባ አቶ ተክለወልድ አሳስበዋል።
የኢትዮጽያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ በበኩላቸው ባንኩ ባለፉት ስድስት ወራት ያስመዘገባቸውን መልካም ውጤቶች እንቅፋቶችን በመፍታትና አስቸጋሪ አሰራሮችን በመቅረፍ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም የላቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
አፈጻጸሞችን በልዩ ትኩረት በመለየት በየደረጃው ያለውን አመራርና ሰራተኛ በአሰራር በማገዝ መፍታት እንደሚገባም ዶ/ር እመቤት መለሰ ገልጸዋል። በተለይ ተንከባለው የመጡና ባንኩን ለችግር የሚዳርጉ የአሰራር ግድፈቶችን በትኩረት መፍታት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የባንኩን የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የስትራቴጂና ቼንጅ ማኔጅመንት ዳይሬክተር ዶ/ር ሽመልስ አርአያ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት 10.3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 11.3 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ ከእቅድ በላይ ማሳካት ተችሏል።
መንግስት ባንኩን ለመታደግ በርካታ አዎንታዊ እርምጃዎችን ወስዷል ወደፊትም ይወስዳል ያሉት ዶ/ር እመቤት በባንኩ በኩል ግን መወሰድ የሚገባቸው በርካታ ተግባራት እንዳሉ አሳስበዋል።
በእለቱ የተካሄደው የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ግምገማው የባንኩ ቀጣይ ጉዞ ላይ በመምከር አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
ተጨማሪ ማብራሪያ በቀጣይ ክፍል ይዘን የምንመለስ ይሆናል