ዛሬ እስኪ አንድ አስገራሚ ታሪክ እንጋብዛቹ እስከመጨረሻዉ አብራቹን ሁኑ
📍ጂሚ ጆንግ ይባላል በፈረንጆቹ በሜይ 24 በ1990 ከቻይናዊ ቤተሰቦቹ ተወለደ ፤ ጂሚ ቻይና ሻንጋይ ውስጥ ተወልዶ እድገቱን በትምህርት የተነሳ በአሜሪካ አደረገ
📍ይህ ቻይናዊ ታዳጊ በሃሺሽ እና በኮኬይን ሱስ ውስጥ ሆኖ ህይወቱን በሚገፋበት ወቅት ነበር በ2012 በአንዲት እለት ኮኬይን ለመግዛት ገንዘብ ለማውጣት ወደ አንድ ማርኬትፕሌስ ጂዮርጂያ ከተማ ውስጥ ያቀናው
📍ጂሚ ገንዘብ ለማውጣት ወደ አንድ ሲልክ ሮድ ያመራል ብላክ ማርኬት መገበያያ ቦታ ማለት ነው ፤ በዚህም ቦታ ጂሚ ያለውን የክሪፕቶከረንሲ ገንዘብ ሁሉ ለማውጣት ዊዝድሮ ያደርጋል
📍በዚህም ሰአት የክሪፕቶ ዊዝድሮውን ሲያዝ ሁለት ጊዜ ክሊክ ያደርጋል ከዛም ከነበረው ዋጋ ደብል ይሰጠዋል ፤ ማለትም 100$ ቫልዩ ያለው ከሆነ 200$ እንደማለት ሲሆን በሰአቱ ሲስተሙ ደብል እንዲያወጣ መፍቀዱን በመረዳት በወቅቱ Kyc አለመኖሩን ተከትሎ በፍጥነት 9 አካውንቶችን ይከፍታል
📍ከዛም በማግስቱ 500 ቢትኮይን ያስገባል ከዛም ዊዝድሮ የሚለውን አማራጭ በፍጥነት አራት ጊዜ ሲነካው 2,000 ቢትኮይን ይሆንለታል ። ከዛም በዛኑ ቀን 3,000 ቢትኮይን ከዛም ቁጥሩ ከፍ እያለ 50,000 ቢትኮይን ዊዝድሮ ወደ ዋሌቶቹ ያደርጋል ።