‘’የዓመቱ ድንቅ እናት’’ እና ‘’ለእናቴ’’ የፅሁፍ ውድድር ለመወዳደር የሚያስፈልጉ መስፋርቶችን ያውቃሉ?
= = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = = =
የእናት ባንክ በ2017 ዓ.ም ከሁለተኛው "ለእናቴ" ከተሰኝው የጹሑፍ ውድድር በተጨማሪ ‘’የዓመቱ ድንቅ እናት’’ የተሰኝ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል።
ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው “ለእናቴ” የተሰኘ የጽሑፍ ውድድር፡ ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሑፍ (ግጥም ያልሆነ፣ በወግ መልክ፣በደብዳቤ ቅርፅ የሚወዳደሩበት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው “የዓመቱ ድንቅ እናት” የተሰኘው ውድድር፣ተወዳዳሪዎች በአካባቢያቸው በሕይወት ያሉና የሚያውቋቸውን ወይም የራሳቸውን እናቶች በጹሑፍ በድምጽና በምስል ቀርጸው በቀጥታ በመጠቆም የሚሳተፉበት ውድድር ነው።
የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-
"ለእናቴ"
1. በሌሎች የኅትመት እና የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ያልቀረበ ወጥ፣ አዲስና የተለየ መሆን ይኖርበታል፤
2. ጽሑፉ ግልጽ እና ተነባቢ እንዲሆን በኮምፒውተር ተጽፎ፣ በ12 ፎንት የፊደላት መጠን እና በ1.5 የኅዳግ መስመር መቅረብ አለበት፤
3. በ ኤ ፎር (A4) የወረቀት ምጣኔ፣ ከሦስት /3/ ገጽ ያልበለጠ መሆን ይኖርበታል፤
4. ተወዳዳሪዎች፣ ስማቸውን እና አድራሻቸውን የጽሐፍ ሥራቸውን ባቀረቡበት ወረቀት ላይ መጻፍ የለባቸውም፤ ይልቁንም ሥራቸውን በሚያሽጉበት ፖስታ ላይ ብቻ መጻፍ ይጠበቅባቸዋል።
5. የማስረከቢያ ጊዜ እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
"የአመቱ ድንቅ እናት"
1. ለውድድር የሚቀርቡት ባለታሪኮች በሕይወት ያሉ እናቶች መሆን አለባቸው፤
2. ታሪካቸው የሚነገርላቸው እናቶች ግዴታ ወላጅ እናት (የስጋ እናት) መሆን አይጠበቅባቸውም፤ ለምሳሌ አሳዳጊ ወይም ደግሞ በሰፈር አሊያም በጎረቤት ያሉ እናቶችን ታሪክ ማቅረብ ይቻላል።
3. በዚህ ውድድር ላይ ስለ ሚያቀርቡት ታሪኮች በጽሑፍ አሊያም በድምፅ ወይንም ደግሞ በቪዲዮ ሥራዎቻቸውን ቀርፀው ማቅረብ ይችላሉ።
4. የማስረከቢያ ጊዜ እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩቡት የውድድር አይነት የሚያቀርቧቸውን ስራዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የእናት ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት አሊያም በፌስ ቡክ የመልዕክት ሳጥን እና በኢሜል አድራሻ፡ lenate@enatbankSc.com ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል። ማስታወሻ ፦ ተወዳዳሪዎች ለመወዳዳሪያ ከቀረቡት ሀሳቦች መካከል በአንዱ ብቻ መርጠው መወዳዳር ይኖርባቸዋል፡፡