እናት ባንክና የተለያዩ ተቋማት በመተባበር ያዘጋጁት የ2017ዓ.ም ብሩህ እናት የተሰኘ ሀገር አቀፍ የሴቶች የቢዝነስ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር ይፋ ሆነ፡፡
ውድድሩን እናት ባንክ፣ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ኢንተርፕርነሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት እና የተባበሩት መንግስታት ሴቶች ጉዳይ በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን ይህንኑ አስመልክተው ተቋማቱ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ተቋማቱ በመግለጫቸው ከዛሬ የካቲት3- 24 2017ዓ.ም ድረስ የተወዳዳሪዎች ምዝገባ የሚካሄድበት፤ከመጋቢት8-19 /2017ዓ.ም ድረስ የቡት ካምፕ ስልጠና የሚሰጥበት፣መጋቢት 20/2017ዓ.ም የእውቅናና የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
ውድድሩ አዳዲስ የቢዝነስ ሀሳቦችና የሴቶችን ሥራ ፈጠራ ለማበረታታት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር፣የሴቶች የቴክኖሎ ፈጠራ ተሳትፎ ለማሳደግ፣ችግሮችን የመፍታት ባህላቸው እንዲያዳብሩ ድጋፍ ለማድረግ አላማ ያደረገ ነው፡፡
ሴቶች በስፋት በሚሳተፉባቸው የስራ ዘርፎች ጊዜ ቆጣቢ፣ድካምና ጫናን የሚያቃልሉ የቤት ውስጥ ስራ፤የእንክብካቤ አገልግሎት፣የግብርናና መሰል ስራዎች ላይ በስልጠና የተደገፉ ቴክኖሎጂ ተኮር የፈጠራ ውድድር ነው፡፡
ፕሮግራሙ ማሰልጠን፣መሸለም ማብቃት በሚል መሪ ሀሳብ ከመላ አገሪቱ ለተውጣጡ 50 ለሚሆኑ ሴት ስራ ፈጣሪዎች በቡት ካፕ የኢንተርፕርነርሽ ስልጠና፣ የማማከር አገልግሎት፣የሥራ ትስስርና የልምድ ልውውጥ የሚያገኙበት እንደሆነ ተገልጻል፡፡
በውድደሩ አሸናፊ ለሚሆኑ 10 ሴቶች እውቅናና ከ100ሺህ እስከ 500ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተመላክቷል፡፡
ፕሮግራሙ ሁሉም አጋር አካላት የሴቶች ተጠቃሚነት ለማጎልበት ምቹ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት ቁርጠኝነታቸውን የሚያሳዩበትም እንደሆነ ተገልጿል፡: