እማማ አፀደ የሚባሉ ጎረቤት አሉን የእናቴ ጓደኛ ናቸው። እማማ አፀደ አመም አድርጓቸው ሕመማቸው በባሰ ቁጥር እናቴን ጠሏት።
ይሰድቧታል... ሌባ ናት...መሠሪ ናት...ልትገለኝ ትፈልጋለች...መርዝ አበላቺኝ ይላሉ።
አትምጣብኝ ብለው ስሞታ ይናገራሉ።
.... ሌሊት እቤቴ ልትገባ ነበር ይላሉ።
....ሰው እንዳትመስላችሁ ይላሉ።
እናቴ ቤታቸው መሄድ አቆመች...
ከቤት መውጣት እያቆሙ ግቢያቸው መዋል ጀመሩ ....
እናቴ እሷ መሆኗን አትንገሩ ብላ ፤ ምግብ ትልክላቸዋለች።
በእህታቸውን ልጅ ፤ ምን ጎደለ ጤናቸው እንዴት ነው እያለች ትሰልላቸዋለች...
ንዴት ሊገድለኝ ይደርሳል....
እቆጣታለሁ "ስምሽን እያጠፉሽ እየሰደቡሽ እየጠሉሽ አትተያቸውም ወይ?"....እላታለሁ!!
"ጭንቅላታቸው ዕጢ ወጥቶባቸዋል እሱ ነው ትንሽ ቀየር ያደረጋቸው እንጂ፤እሳቸው እንኳን ሳልበድል ብበድላቸው እንኳን በክፉ አያነሱኝም"...ትለኛለች
በእህታቸው ልጅ በኩል የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መግዣ ከኛ ወስዳ ... ተበድራም ቢሆን ትገዛላቸዋለች።
እሳቸው ያቺ ምናምንቴ ...ድግምታም... ያቺ ነጠላ እያሉ ጮክ ብለው እናቴን ሲሰድቧት ይውላሉ።
እኔ ጠላኋቸው... !!
አንድ ቀን ለምን ግን እንዲ ስምሽን እያጠፉ እየጠሉሽ እያልፈለጉሽ አልጠላሻቸውም...? ብዬ እናቴን ጠየቅኋት
"ጓደኛዬ ናቸው..! እዚህ ሠፈር ስመጣ እሳቸው ናቸው ያለመዱኝ።
ዕድር ያስገቡኝ... የሌለኝን ዕቃ ያዋሱኝ...የተቆረቆሩልኝ....የአረሱኝ ....የመከሩኝ...እንዲህ አይባልም እያሉ መንገድ ያሳዩኝ እርሳቸው ናቸው።
ድንገት ታመው ነው የተቀየሩት....ከሁሉም ጋር ነው መጣላት የጀመሩት እኔ ላይ ትንሽ ጠንከር አሉ እንጂ ...
በክፉ ግዜ እንኳን ወዳጅ ላይ ጠላት ላይ አይጨከንም...!!
የጨዋ ሰው ልክ የሚታየው ሲጣሉት ነው...
...በፍቅር ግዜ ሰው አይመዘንም።
አፀዱ እንዴት ዓይነት ጥሩ ሰው መሰሉህ ዛሬ ሕመም ተጣብቷቸው እን'ጂ...
ስንት ቀን መሰለህ እጦት በእርሳቸው ሳብያ ከቤታችን የተባረረው....
አፀደ ደግ ....ሩህሩህ ናቸው...
እናንተ ሳትወለዱ ማንም ሳይኖረኝ ነው ከኔ ጋር የነበሩት...
የአፀደ ውለታ አለብኝ...
. !
✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988