በታቦተ ሕጉ ላይ የተሳለቁ ግለሰቦችና ቡድኖች በሕግ ይጠየቃሉ
በጥምቀት በዓል በታቦተ ሕጉ ላይ የተሳለቁ፣ የትንኮሳ ስብከቶችና አለባበሶችን በማኅበራዊ ሚዲያ ያሠራጩ ኃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች በሕግ እንደሚጠየቁ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰሞኑን ግለሰቦችና ቡድኖች ሃይማኖታዊ ቅራኔ እና ጥላቻ ሊፈጥሩ የሚችሉ በቪዲዮ የለቀቁትን አሉታዊ መልእክቶችን እና ተግባራትን በፍጥነት ለማረም በጽሕፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ማብራሪያ ለሚዲያ አካላት ሰጥቷል፡፡
በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳብራራው ከእምነቱ ሥርዐት ባፈነገጠ መንገድ አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸው ግለሰቦችና ቡድኖች የሌላውን እምነትና ሥርዐት በማንቋሸሽ፣ ክብረ ነክ ተግባራትን በመፈጸም፤ በተለይም በጥምቀት በዓል ታቦተ ሕጉ ላይ በመሳለቅ፤ የኢስላማዊ አለባበስ መገለጫ የሆነውን ጀለቢያ በመልበስ ሙስሊሞች በመምሰል የትንኮሳ ስብከቶችና ዝማሬዎች በማቅረብ፣ የትንኮሳ አለባበሶች ጭምር በመጠቀም በማኅበራዊ ድረገጽ የለቀቁት አጫጭር ቪዲዮችዎች የእምነቱ ተከታዮችን ማስቆጣቱን ያብራራል፡፡
ይህ ዓይነቱ ተግባር በሀገራችን ለዘመናት የዘለቀውን የመከባበር፣ በሰላም አብሮ የመኖር እሴትን የሚሸረሽር ድርጊት መሆኑን የገለጸው መግለጫው፤ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ የድፍረት ድርጊት በመሆኑ ይህን የፈጸሙ ግለሰቦችና ቡድኖች በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባ፣መጠየቅም መጀመሩን መግለጫው ያስረዳል፡፡ ማንኛውም ግለሰብም ይሁን ቡድን ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሌሎችን መብትና ጥቅም በሚጻረር አግባብነት የሌለውና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት የሚፈጽም ማንኛውም ሕገ ወጥ ተግባር በዝምታና ሊታለፍ እንደማይገባው ይገልጻል፡፡
በመጨረሻም ማኅበራዊ ድረገጾችን እና ሚዲያዎችን በመጠቀም የጥላቻ ንግግሮች፣ ትንኮሳዎችና ክብረ ነክ ድርጊቶች የሚፈጽሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፡- ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ ከፍትሕ የጸጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሠሩ እንደሆነ የወጣው መግለጫ ያስረዳል፡፡ አያይዞም ይህ ዓይነቱን ተግባር ለመከላከል የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሥርዐት ላይ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ የሃይማኖት
ተቋማት ጉባኤ መግለጫ ያስረዳል፡፡
Via ኢኦተቤክ ቴቪ
@Nigatu5