አንድ የ 8 ዓመት ህፃን ልጅ ለአዕምሮ በሚከብድ ሁኔታ ተደፍራ ተገድላ በመቀጠልም ተሰቅላ ተገኘች‼️
በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ አንዲት ህጻን ከቤት ተወስዳ ከተደፈረች በኋላ ተገድላ መገኘቷ ቁጣ ቀስቅሷል።
" በኛ የደረሰ በማንም አይድረስ " የሚሉት የተጎጂ ቤተሰብ በልጃቸው ላይ ለደረሰው ቀሰቃቂ ወንጀል " ፍትህ እንሻለለን " ብለዋል።
ሲምቦ ብርሃኑ ትባላለች፡፡ የ8 ዓመት ልጅ ስትሆን ገና የአንደኛ ክፍል ተማሪ ነበረች።
ባሳለፍነው ሳምንት ባለፈ ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ተመልሳ ምሳ እንደበላች ከመኖሪያ ቤቷ የደረሰችበት ሳይታወቅ ቀርቷል።
በዕለቱ ፍለጋ የወጣው ቤተሰብ ታዳጊዋን ከነሙሉ ጤንነትና በህይወት ለማግኘት ግን አልታደሉም፡፡
ሮጣ ያልጠገበች ፤ ክፉ ከደጉን እንኳን የማትለይ ህፃን ለአዕምሮ በሚከብድ ሁኔታ ከተደፈረች በኋላ " እንዳትናገር በሚል " ከመኖሪያ ቤታቸው ጀርባ በቅርብ ርቀት ላይ ህይወቷ አልፎ መገኘቱን አንድ የቤተሰቧ አባል ለዶቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል።
ህፃኗ ከተገደለች በኋላ ተሰቅላ መገኘቷን የገለጹት የቤተሰብ አባሉ " ጫማዋን ያወለቁባትና የሰቀሏት ቦታ አንድ አይደለም የ50 ሜትር ገደማ ርቀት አለው " ብለዋል።
በወረዳው ኤላ ከተማ በ8 ዓመቷ ልጅ ሲምቦ ላይ የተፈጸመው ጥቃት አባት የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸው እና በስራ ቦታ መሆናቸው እንዲሁም እናት የ2 ወር እመጫት በመሆናቸው አጋጣሚውን በመጠቀም እንደነበር የቤተሰቡ አባል ተናግረዋል።
የተጎጂ ቤተሰብ አባል የሆኑት አስተያየት ሰጪ " የህፃኗ ቤተሰብ ቤት በፊት ለፊት በኩል ሆቴል በመሆኑ የሚገባውና የሚወጣው ብዙ ነው፡፡ በጓሮ በኩል ፑል መጫወቻም አለ፡፡ ደፋሪዎችም በዚያው በጀርባ በር እንደወሰዷት ነው የቤተሰብ ስጋት " ብለዋል።
2009 ዓ.ም. የተወለደችው ትንሿ ሲምቦ ገና በ8 ዓመቷ ለዚህ እጅግ ለአሰቃቂ ድርጊት ሰለባ መሆኗ ቤተሰቦቿን ቁጭት ውስጥ ከቷል።
" ባለሙያዎች በሰውነቷ ላይ የታየውን ፈሳሽ በመውሰድ ምርመራ እያደረጉ ነው " ያሉት የቤተሰብ አባል እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ ተጠርጣሪ አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት ተኩል የተገኘው የህፃኗ ሲምቦ አስክሬን በትናንትናው እለት ስርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል
።
©ዶቼ ቨለ ሬድዮ@Esat_tv1@Esat_tv1