የወባ በሽታን አስመልክቶ በአገር አቀፍ ደረጃ ሳምንታዊው የውይይት ስብሰባ ተካሄደ
በአገር አቀፍ ደረጃ የወባ በሽታ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ዛሬ ጥር 19/2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከል በበይነ መረብ ሳምንታዊ የውይይት ስብሰባ ተካሄደ፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝ በተመለከተ የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል፣ የክልል ጤና ቢሮዎች፣ ክላስተሮች የወባ ወረርሽኝን አስመልክቶ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን፣ የታዩ ለውጦችን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የወባ ወረርሽኝ ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ በአገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎችና ክላስተር ወረዳዎች ወረርሽኙ እየቀነሰ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች የመከላከል ስራው ላይ የመቀነስ ሁኔታዎች እንደሚታዩ ተገልጿል።
ለተማሪዎች የጤና ትምህርት የተሰጠ መሆኑን፣ በተለያዩ በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ ለማሕበረሰቡ የወባ የመከላከያ መንገዶች እና የጤና ትምህርቶችን አስመልክቶ የግንዛቤ ስራዎች መሰራታቸውን፣ እስከ አሁን የተሰሩ ስራዎች ውጤታማነትን በተመለከተ ግምገማ መደረጉን እና በቀጣይም የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት በተሻለ መንገድ ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን፣ ስለሆነም አካባቢን ከማጽዳት አንጻር ሕብረተሰቡን በማስተባበር በዘመቻ መልክ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት መታቀዱን ክልሎች በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር የውይይቱን ማጠቃለያ ሃሳብ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት የወባን ወረርሽኝየመከላከሉና የመቆጣጠሩ ስራ ውጤታማ መሻሻል ማሳየቱን፣ በሁሉም አካባቢ የተጠናከረ የመከላከል ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ ከክልል እስከ ወረዳ በተዋረድ የሚገኙ አመራር አካላት ሁሉ ከዚህ በፊት ሲደረግ የነበረውን የመከላከልና የመቆጣጠር ድጋፍ በማጠናከር መከናወን የሚገባቸው ተግባራት መስራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያሳሰቡ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡