🟡ሲያነቃቁን ለምን አንነቃም? ሙተን ይሆን እንዴ?
(አሌክስ አብርሃም)
💡ለመጀመሪያ ጊዜ self-help book የሚሏቸውን ሳነብ በጣም ነቅቸ ነበር! አስታውሳለሁ የ Rhonda Byrne ን The secret ሳነብ በጣም ከመንቃቴ የተነሳ ለስራ እጀን ከመጠቀም ይልቅ አዕምሮየን ለመጠቀም ወስኘ ነበር። ለምሳሌ መብራት አጥፍቸ ከመተኛት ተኝቸ መብራቱ ልክ እንቅልፍ ሲወስደኝ ይጠፋል ብየ ለራሴ እነግረዋለሁ፤ጧት ስነሳ እንደበራ ባገኘው አልደነቅም፣ ከእንቅልፌ ከመንቃቴ አንድ ደይቃ በፊት በራሱ ጊዜ እንደበራ አምናለሁ። የወሩ የመብራት ሂሳብ ግን የነገረኝ ሌላ ሆነ፤ ተው ወንድሜ በጣም አትንቃ አለኝ። እናም እያጠፋሁ መተኛት ጀመርኩ። ከ1890 ዓ/ም ጀምሮ መብራት ሀይል መብራት ያላጠፋበት ብቸኛ ወር ነበር። ስንነቃ አይወዱ😀
🕯ኦሾን ያነበቡ የኔ ዘመን ወጣቶች ደግሞ "ሐይማኖት ባህል ገለመሌ ከጫነብን ፍዘት ወጣን" አሉና በየመንገዱ ፀጉራቸውን በመፍተል መቆዘም ጀመሩ፤ ይህንንም "ውስጣዊ ንቃት" አሉት። ከአመታት በኋላ ሁሉም ጠበል ገብተው እየጮሁ ከንቃታቸው በጣም ነቁ። በቀን አምስቴ ኡዱ የሚያደርጉ፣ ለጁመዓ የሽቷቸው መዓዛ ከሞያሌ የሚጣራ ፣ እንዴት ያሉ ንፁህ ሙስሊም ወዳጆቸ ሳይቀሩ ጀዝበው ገላቸውን መታጠብ አቁመው ነበርኮ! ስንት ተቀርቶባቸው ተመለሱ። የዛን ሰሞን ወጣቱ ሁሉ ውስጣችን በራልን እያለ ስንት ጨለማ ተከናነበ። ራሳቸውን ያጠፉም ነበሩ። ኦሾና አለቃ ገብርሃና ተረታቸው እንጅ ኑሯቸው አያምርም።
🔦ይሄው በዚህኛው ዘመን ደግሞ አነቃቂወች እንደአሸን ፈሉና "ያሰብከውን ትሆናለህ፣ ነኝ በል፣ አለኝ በል፣ ደርሻለሁ በል፣ እችላለሁ በል፣ በሀሳብህ መኪና አስነሳ፣ አሉ፤ ወጣቱ የሀሳብ መኪና አስነሳ፤ በሀሳብ ሲጋልብ ራሱ ጋር ተጋጨ፣ ቤተሰቡ ጋር ተጋጨ፣ አገሩ ጋር ተጋጨ፣ፈጣሪው ጋር ተጋጨ ። ከሆነስ ሆነና ለምንድነው በዚህ ዘመን ይሄ ሀሁሉ አነቃቂ ንግግር ያላነቃን? የእውነት የሆነ ጊዜ ያነቃን ነበርኮ፣ እየቆየ ግን እንኳን ሊያነቃን ያስተኛን ጀመረ፤ እኮ ለምን?
📍የህክምና ባለሙያወች ከተሳሳትኩ አፉ ብለው ያርሙኝና በእነሱ ሙያ Drug tolerance የሚሉት ነገር አለ አሉ፤ በትክክል ከተረዳሁት ለሆነ ህመም የተሰጣችሁ መድሀኒት ከሆነ ጊዜ በኋላ በሽታችሁ ጋር ይግባቡና ፍሬንድ ይሆናሉ። በሽታው መድሃኒቱን ይላመደዋል።ጉቦ እንደበላ ደንብ አስከባሪ በሽታችሁ መንገድ ዳር ሲያሰጣችሁ መድሀኒቱ እንዳላየ ያልፈዋል። ለምሳሌ የእንቅልፍ ችግር ገጠማችሁና በሐኪማችሁ የእንቅልፍ ኪኒን ታዘዘላችሁ እንበል ፤ የመጀመሪያ ሰሞን ድብን ያለ እንቅልፍ ያስወስዳችኋል፤ እየቆየ ሰውነታችሁ ሲላመደው መድሀኒቱን ውጣችሁም ቁልጭ ቁልጭ ስትሉ ታነጋላችሁ። ወይ አይነቱን ወይ መጠኑን ባለሙያ ካልቀየረው በቃ ለውጥ የለም። አይ መጠኑን ራሴ እቀይረዋለሁ ብላችሁ ጨመር አድርጋችሁ ከወሰዳችሁ ደግሞ ትተኙ ይሆናል ግን እንደገና ላትነሱ ትችላላችሁ።
🔑ወደህይወት ስናመጣው እኛ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ሰዓት ማንኛውንም ማነቃቂያ ከመላመድ አልፈን እንደዘፈን ሸምድደነው አብረን እየደገምነው ነው። ገና ፊቱን ስታዮት አብራችሁ "ብሮሮሮሮሮ" አትሉም?! ለዛ ነው ከነዋሪ መካሪና ዘማሪ የበዛው። የፈለገ ብንመከር ብንዘከር ብንሰበክ ብንወገዝ ወይ ፍንክች። አሁን ሞራል፣ ሐይማኖት፣ የአገርም ይሁን የሰው ፍቅር፣ ይሉኝታ ፣መማር ፣ የራስ ክብር ወዘተ አእምሯችን ተላምዷቸው ተራ ነገር ሁነውብናል።
✨የሞራል ተቋሞቻችን በሞራል ድሽቀት ከተራው ህዝብ ቀድመው ባፍጢማቸው ተተክለዋል፤ የትዳር ሰባኪወቹ ማግባትና መፍታት መድረክ ላይ እንደመውጣትና መውረድ ቀሏቸዋል፤እንደውም የጓዳቸውን ውድቀት እንደባንዲራ በአደባባይ እየሰቀሉ እዮልን ባይ ሆኑ። አሁን እንደህዝብ ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው የሚያነቁን ወይ (((ብር ማጣት))) አልያም (((ብር ማግኘት))) ይሄ የመጨረሻው ዶዝ(መጠን) ነው!
💎ሰው ክብሬ፣ ገመናየ ፣ማንነቴ የሚለውን ነገር ሁሉ ይዞ ገበያ ከወረደ ምን ይመልሰዋል?! ከዚህ በኋላስ? ምን ያነቃን ይሆን? ምክንያቱም በብር የሚመጣ ንቃት በአንዴ አይረካም፤ እንደአደንዛዢ ዕፅ በየቀኑ መጠኑን እየጨመሩ ካልወሰዱት መጨረሻ የለውም። መመለስም መቀጠልም የማንችልበት አውላላ ሜዳ ላይ የሚያስቀር መርገምት ነው!! ምን ላድርግ ቸገረኝ፣ የማደርገው አጣሁ ልሙት እንዴ ታዲያ በሚል ሰበብ ከሰውነት ድንበር ከምንርቅ በየግላችን "ይሄንኛው ነገሬ ለገበያ ከሚቀርብ ሞቴን እመርጣለሁ" የምንልለት የሆነ መስመር ልናሰምር ግድ ነው። ሰው ራሱ ወስኖ ያሰመረውን መስመር ከሞት በስተቀር ምን ያሻግረዋል?!
✍አሌክስ አብርሃም
ሸጋ ቅዳሚትን ተመኘን!❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot