የጉምሩክ ኮሚሽን በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የተሳለጠ የጉምሩክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ::
#######################
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም )
የጉምሩክ ኮሚሽን በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የተሟላ የጉምሩክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡
ኮሚሽኑ ከጅቡቲ የጉምሩክ ማስተባበሪያ ጀምሮ የትራንዚት እና ሌሎች የጉምሩክ ስነስርዓቶችን ማስፈጸም የሚያስችል የተለየ፣ ፈጣን እና ቀላል አሰራር በመዘርጋት አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡
በተጨማሪም በነጻ ንግድ ቀጠናው አስፈላጊ የጉምሩክ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል የተሟላ የሰው ኃይል እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን በመመደብ ወደስራ ገብቷል፡፡
ነፃ የንግድ ቀጠና ልዩ ኢኮኖሚ ቀጠና አካል ሲሆን በውስጡ እሴትን የሚጨምሩ፣ የሎጅስቲክስ አገልግሎቶችን፣ የማምረት ስራዎች እንዲሁም ንግድ የሚከናወንበት ሲሆን፤ የሎጅስቲክስ ስርዓቱን ለማፋጠን እና ለዓለም አቀፍ ንግድ ቅልጥፍና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት :-
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/ecczenaበድረ ገጽ፦
www.ecc.gov.etበቴሌግራም፦
https://t.me/EthiopianCustomsommission