የቅድመ ክፍያ ስማርት ቆጣሪዎች ትግበራ መጀመሩ ተገልጿል።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች በዩኒፋይድ ፕሪፔይመንት ፕሮጀክት የኤስ ቲ ኤስ ስማርት ነጠላ ፈዝ ቆጣሪዎችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።
አሁን ላይ ለፕሮጀክቱ ትግበራ የሚያበቁ ሁሉም አስፈላጊ ዕቅዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውንና 2 ሺህ 55 አዲስ ስማርት ነጣላ ፌዝ ቆጣሪዎች የመግጠም ስራ መከናወኑን አገልግሎቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።
በዚህም ደንበኞች ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ካሉበት ቦታ ሆነው የቶከን ቁጥር በቴሌ ብር እና በሌሎች የክፍያ አማራጮች በመግዛት ኤሌክትሪክ መጠቀም እንዲችሉ ያስችላቸዋል ነው የተባለው።
በአዲስ አበባ ቆጣሪ የተገጠመባቸው አካባቢዎች፦
ባልደራስ ኮንዶሚኒየም፣ ፈረስ ቤት እና የካ ሳይት 100 ቆጣሪዎች፣
ባቱ እና መካኒሳ ኮንዶሚኒየም 1 ሺህ 432 ቆጣሪዎች፤
ሲ ኤም ሲ ልዩ ቤቶች ጀርባ የመከላከያ ቤቶች 523 ቆጣሪዎች ናቸው፡፡
አገልግሎቱ እንዳስታወቀው በአጠቃላይ በዩኒፋይድ ፕሪፔይመንት ፕሮጀክት 500 ሺህ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን በዘመናዊ ቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎች ለመቀየር ታቅዷል።
አሁን ላይ ከ500 ሺህ ቆጣሪዎች ውስጥ 125 ሺህ በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ለሶስት ፌዝ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች ሙሉ በሙሉ ለመቀየር ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፤ 25 ሺህ ነጠላ ፌዝ ስማርት ቆጣሪዎች ደግሞ አዲስ አበባ ለሚገኙ ደንበኞች እየተቀየረ ይገኛልም ብሏል፡፡
Source: tikvahethmagazine@Ethiopianbusinessdaily