🌼Ꭼᴛʜɪᴏ 𝐒ᴛᴜᴅᴇɴᴛ 𝐆ᴜɪᴅᴇ ™🌻


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Ta’lim


🎀 𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄 𝐓𝐎 '' Ꭼᴛʜɪᴏ 𝐒ᴛᴜᴅᴇɴᴛ 𝐆ᴜɪᴅᴇ ™
Buy Ads : https://telega.io/c/Ethiostudentguide

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


DARKIFY dan repost
💥 WAVE TIME 🔍

🌟 NEW SPECIAL FOLDER 🌟



🔊 ቻናላችሁን ማሳደግ የምትፈልጉ ከ 1K በላይ ያላችሁ በሙሉ wave folder ውስጥ መግባት የምትፈልጉ  ካላችሁ ቻናላችሁን በፍጥነት እና በታማኝነት እናሳድጋለን።


@papa_graphy




Hello, Musabih Man! Thank you for visiting our Channel


Hi 😭◦ , Thank you for joining us!




ሴት ልጅ አንተን እንዳፈቀረችክ የምታቅበት 10 ምልክቶች ከታች #JOIN ብለክ ተተቀምበት እና ህዝቤ ሆይ ምን ትተብቂያለሽ ገብተህ አንበዋ😋😋😋😋
👇👇👇👇👇👇👇


🥰

➡️ Channel jaalatamoo ergaalee ajaaibsiisoo fi barsiisoo ta'an qabu kana irratti gadi tuquudhaan JOIN taasisaa! ➡️ JOIN 📌

1️⃣ 💡💡💡💡💡💡💡

     🚘 'https://t.me/addlist/4e8EfR1mqNFlY2E8' rel='nofollow'>JOIN
    JOIN

2️⃣ 💡💡💡💡💡💡💡

    🚩 MORE JOIN  🚩
   🚩 MORE JOIN 🚩


3️⃣💡💡💡💡💡💡💡
    🍰MORE JOIN  🕯
   🍰 MORE JOIN 🕯


𝙰𝚍𝚍 𝚢𝚘𝚞𝚛 𝙲𝚑𝚊𝚗𝚗𝚎𝚕
ᥲძძ ᥡ᥆ᥙr ᥴһᥲᥒᥒᥱᥣ

📌 Channel keessan tolaan nu waliin beeksifadhaa


እርግጠኛ ነኝ ፎቶ ለመነሳት ፈልገው የአነሳስ style ጠፍቶብዎት  ተቸግረው ያውቃሉ።የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇

https://t.me/addlist/Hi8NJ3zE-GA2N2Nk


💥 ለ 2016  የ Ʀᴇᴍᴇᴅɪᴀʟ ተማሪዎች ɴᴇᴛᴡᴏʀᴋ ላልሰራላቹ  ምደባ በማየት እንድንተባበራቹ  የምትፈልጉ Ʀᴇɢɪsᴛʀᴀᴛɪᴏɴ ɴᴜᴍʙᴇʀ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ ላይ ላኩልን

12.4k 2 37 185 32

☑️ የ  Ʀᴇᴍᴇᴅɪᴀʟ ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ ❗️

☑️ በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Ʀᴇᴍᴇᴅɪᴀʟ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል ።

☑️ ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የƦᴇᴍᴇᴅɪᴀʟ ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል ። ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል ።

☑️ ምደባ ለመመልከት

☑️ Website: https://placement.ethernet.edu.et 

☑️ Telegram: https://t.me/moestudentbot

☑️ ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል ።

Ꭼᴛʜɪᴏ 𝐒ᴛᴜᴅᴇɴᴛ 𝐆ᴜɪᴅᴇ ™ ☑️


🎮🎮🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️  🅰🅰🅰
1️⃣5️⃣🔠 🤍🤍🎆  Times! 🙌

We're overjoyed to announce that our Telegram Channel family has grown to an incredible 1️⃣5️⃣ 🅰️ Subscribers ⭐Your support, engagement, and enthusiasm mean the world to us. 🌐🌐


Whether you've been with us from the beginning or just joined the journey THANK YOU for being a part of our community.⭐️⭐️⭐️⭐️


🤍🫰 Your ˡⁱᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ inspire us to create more content for you  ⭐️⭐️⭐️⭐️


                 💥 Eᴛʜɪᴏ Sᴛᴜᴅᴇɴᴛ Gᴜɪᴅᴇ ™


BAHIRDAR UNIVERSITY

መገኛ፦ ባህር ዳር
አየር ሁኔታ፦ ሞቃታማ ነው የሌለ ቀን ቀን ፀሀያማ ነው በጣም፤ በተለይ engineering, Low,Arc,Land ያሉበት የባብ campus ይባላል ጥላ ያስፈልጋል ወንድም ሴትም ነው እዛ ጣጣ የለውም። እና ያው የሚሞቅ ነገር አያስፈልግም ቀለል ያለ ብርድ ልብስ  ለመያዝ ሞክሩ።

📌በውስጡ ያሉ ግቢዎች፧ አምስት ሲሆኑ እነርሱም


  🔅ፔዳ ግቢ
ዋናው ግቢ  ሲሆን በውስጡም 2 ግቢ አሉት faculty of Business(Fb) ena mainይባላሉ  የተለያዮ የትምህርት መስኮች ይሰጣሉ የሚገኘው ከከተማ 2ብር ባጃጅ ነው ያው ከተማ በሉት
በውስጡ ያሉ የትምህርት መስኮች
   🔸all social dep'ts exept law and Governance
   🔸Comptional science
   🔸medcine
   🔸Maritaym

🔅ሰላም ግቢ
ይሄም ከተማ ነው የሚገኘው ከዋናው ግቢ ብዙም አይርቅም
🔸Textile ጋር የተያያዙ ሁሉም departmenቶች እዚህ ግቢ ላይ ይገኛሉ

  🔅ይባብ ግቢ
ይሄ ግቢ ሞቃታማ እና ፀሀያማ ነው የሚገኘው ባህርዳር መግቢያ ላይ ነው ከከተማ የወጣ ነው
በውስጡ ያሉ የትምህርት መስኮች
   🔸 fresh Engineering
   🔸computer science
   🔸Law
   🔸Arc
   🔸Land organisation ናቸው
Architecture በፈተና ነው ሚገባው ፥ በየአመቱ ሰላሳ ተማሪ ተቀብሎ ያስተምራል ከአንደኛ አመት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ በዚሁ ግቢ ይማራሉ።
  
🔅 ዘንዘልማ ግቢ
ይህ ግቢ ደሞ መውጫ ላይ ነው ያለው በውስጡ ያሉ የትምህርት መስኮች
  🔸 agriculture
  🔸 ke compitional Geology dep't
  🔸vertenary medicine et..
  🔸ፖሊ ግቢ ይሄ ወፍ fresh yelem  ያው 2nd year en 3rd year engineering ነው ያሉት

Generally

Bahir Dar University is organized into
💻Faculty
💻Colleges
💻Institutes
💻 Schools &
💻Academy

🎬Institutes
Bahir Dar Institute of Technology
Ethiopian Institutes of Textile and Fashion Technology &
Institute of Land Administration

🎬Colleges
📃College of Agriculture and Environment
📃 College of Medicine and Health Sciences
📃 College of Business and Economics and
📃 College of Natural sciences

🎬Schools
📖School of Law
📖 School of Computing and Electrical Engineering
📖School of Civil and Water Resources Engineering
📖School of Mechanical and Industrial Engineering and
📖School of Chemical and Food Engineering

🎬Faculties
📮Educational and Behavioural Sciences (the oldest),
📮Faculty of Humanities, and
📮Faculty of Social Sciences

🎬Academy
📌 Maritime Academy
📌 Sports Academy

ምግብ ቤቶች እንዲሁም ዋጋቸው
about Food አረ peace new yelele በተለይ የካፌ ዳቦ ሁሉም ነው ሚወደው (እኔ ራሱ በሃሳብ 🍣)

  የሚገራርም ላውንቾች አሉን ዋጋ አያሳስብም
  አረ ሱቅ የፈለጋችሁት ነው ያለው በቃ በእኔ ይሁንባችሁ ምንም አታጡም ውጭ በር ላይ ደግሞ ያበደ ነው ቡና ፣ሻይ ፣ወተት፣  ምግብ ቤቶች ጨቅ ናቸው

ውሃ ትንሽ አዛ ነው ያው ስትቆዩ የሚለመድ ነው 😌

ባህር ዳር ስትገቡ  የሚዘጋጁ ሰርቪሶች⛰🚈 አሉ senior ተማሪዎች አብረው ይቀበሏቹኃል ፨ እና ምንም አያስቸግርም ዋናው confidence new


📎2017 Remedial  Discussion  groups.

👨‍🏫 Remedial Universty የደረሳችሁ ተማሪዎች በየግሩፖቻችሁ ገብታችሁ መተዋወቅ ይኖርባቹሃል። ትውውቃችሁን ግቢ ሳትገቡ በቴሌግራም ከጨረሳችሁ  ትምህርቱን በአንድነት ትወጣላችሁ❗️

🔸ስለጉዞ መረጃ :ግቢም ከገባችሁ በኋላ ፋይል ለመለዋወጥ እንዲሁም የRemedial  የሚድና ፋይናል ሁሉንም በአንድ  ለመለዋወጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው🔸

አስታዉሱ :መረጃ  የዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ  ስኬታማነት  ከሚወስንባቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛዉ ነው ❗️

✍️ለሁሉም ጓደኞቻችሁ ሼር
አድርጉላቸው🔻
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔆  1. Adigrat University

🔆  2. Ambo University

🔆  3. Arba Minch University

🔆  4. Arsi University

🔆 5. ASOSSA UNIVERSITY

🔆  6. Axum University

🔆  7. Bahir Dar University

🔆  8.  BONGA UNIVERSITY

🔆 9.  BULE HORRA UNIVERSITY

🔆 10. DEBARK UNIVERSITY

🔆 11. Debrebirhan University

🔆 12. Debremarkos University

🔆 13.  DEBRETABOR UNIVERSITY

🔆 14.  DEMBI DOLO UNIVERSITY

🔆  15.  Dilla University

🔆 16  Dire Dawa University

🔆 17. Gambella University

🔆  18. Gondar University

🔆  19. Haramaya University

🔆 20. Hawassa University

🔆  21. INJIBARA UNIVERSITY

🔆  22. Jigjiga University

🔆  23. Jimma University

🔆  24.  JINKA UNIVERSITY

🔆  25.  KEBRI DEHAR UNIVERSITY

🔆  26. Kotebe Metropolitan University

🔆  27. Meda Welabu University

🔆  28. Mekelle University 👇🏾

🔆  29. MEKIDELA AMBA UNIVERSITY

🔆  30. METU UNIVERSITY

🔆  31. Mizan-Tepi University

🔆  32. Oda BultumOBU

🔆  33. RAYA UNIVERSITY

🔆  34. Selale University

🔆  35. Semera University

🔆 36. WACHAMO UNIVERSITY

🔆  37. Welketie UNIVERSITY

🔆 38. WERABE UNIVERSITY

🔆  39. Wolayita Sodo University

🔆 40. Woldiya University

🔆 41,  Wollega University


JIMMA UNIVERSITY

መገኛ፡ ጅማ (ኦሮሚያ)
የአየር ሁኔታ፡ ሞቃታማ ፥ ከአዳማ እና ከመሰል ሞቃት ሃገሮች ለሚመጡ ተማሪዎች ሙቀቱ ምንም ዓይነት ተጽእኖ የለውም እንዲያውም ሊበርዳቸው ይችላል፤ በግልባጩ ደግሞ ከብርዳማ አከባቢ ለሚመጡ ተማሪዎች የሙቀቱ መጠን ከፍ ያለ ይሆንባቸዋል ።
ለማንኛውም ቀለል ያሉ ልብሶችን ይዛቹህ ብትሄዱ መልካም ነው።

በውስጡ ያሉ ግቢዎች 5 ናቸው
1 Main campus
2 Agriculture
3 Koto furdissa
4  BECO SOCIAL
5  AGARO BRANCH NEW

🏢 Main campus
◉ All social science
◉ Medicine
◉ Other health
◉ Computer science, etc

🏢 Agriculture campus
◉ Veterinary
◉ Computational

🏢 Koto furdissa campus
◉ All Engineering departments and
◉ Software students ይገኛሉ።

🌈 በእያንዳንዱ ግቢ አንደኛ አመት ተማሪዎች ይመደባሉ ‼️ የጂማ ዩኒቨርሲቲ ብሎኮች በጣም የሚያማምሩ ናቸው ።ትምሮ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ትንሽ ከበድ ሊልባቹህ ስለሚችል በግቢው ምቾት እንዳትታለሉ ።

☀️ የምግቢ ነገር ከሌሎች ግቢዎች በሚመጡ ተማሪዎች የተመሰከረለት ነው።የግቢ ካፌ በጣም ተስማሚ ከመሆኑ የተነሳ የነን ካፌዎች ቁጥር እንዲያንስ ተጽእኖ ፈጥሮበታል (😱)
ምግቡ Normal ነው አንዳንድ ምግቦች ሊደብሩ ይችላሉ በተለይ ለፍሬሽ ቢሆንም ግን ጨጓራ ምናምን አይነካም።

✨ ከካፌው በተጨማሪ ግቢ ውስጥ እና ከግቢ ውጭ ያሉ ብዙ አማራጮች አሉ።ከግቢ ውጭ ያሉ ብዙ ምግብ ቤቶች አሉ ፥ በአይነትም በጥራትም አሪፍ የሚባሉ።በጣም የሚገርማቹህ ውድ የሚባልው ምግብ 85ብር ነው ።(መምጣቴ ነው በቃ😁) ፓስታ ፣ አይነት ፣ ሽሮ ምናምን ከግቢ ውጭ 95ብር ሲሆኑ ግቢ ውስጥ ደግሞ 60-65ብር ናቸው።

💥 ሻይ 3 ብር ሲሆን ቡና ደግሞ 5ብር ነው ። ( እረ ጉድ ነው!) ለነገሩ ብዙም አይገርምም ሀገሩ ጅማ እኮ ነው በቡናማ አይታሙም።ከግቢ ውጭ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ማግኘት ይቻላል፤

🍇 ሙዝ ፣ ብርቱካን፣ አቩካዶ ምናምን ዘጭ ነውሌላም የተለያዩ ጁስ ቤቶች ይገኝሉ ፥ ጁስ 35ብር ነው

💧 ሌላው ደግሞ የብዙ ግቢዎች ችግር የሆነው የውሃ ጉዳይ ነው፤ ውሃ ጅማ ውስጥ ለአንድ ቀን ጠፋ ማለት ኒዎርክ መብራት ጠፋ ማለት ነው። የውሃ ችግር ጅማ ውስጥ የለም ማለት ይቻላል እንዳያሳስባቹህ ።

💦 ውሃ ግን ሙሉ ለሙሉ አይጠፋም አይባልም ግን በዛ ቢባል ለአንድ ቀን ነው ።
በተረፈ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን ቀዳሚ ከሚባሉት ዩንቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም በመሆኑ ብዙ አስቸጋሪ ነገር አያጋጥማችሁም ።

SOURCE : Jimma University Info Centre


Debrebirhan University

መገኛ ደብረ ብርሃን
ርቀት : ከአ.አ 130km
የጉዞ ሰአት : 1:30-2:30 (mostly)
የአየር ሁኔታ ፡ በጣም ቀዝቃዛ ነገር ግን ግንቦት አከባቢ ለቲሸርት አመቺ ነው ጠዋት እና ማታ ግን በየቀኑ ብርድ አይቀሬ ነው፡፤ ደብዬ ውስጥ በተለይ ጥቅምት አብዝቶ ደሞ ሕዳር ላይ ያለው ብርድ እንኳን ለሰው ልጅ ለእቃም አይመከርም በጣም ከፍተኛ ብርድ አለ  ስለዚህ ተማሪዎች እዚህ ከመጡ በጣም ወፍራም ብርድልብስ ወፍራም ልብሶች ግድ እና ግድ ነው ፡፡

ግቢ ብዛት :- 1 ከከተማም የ 3ብር ታክሲ ነው ለከተማው  ቅርብ  ሲሆን ነገር ግን ጤናዎች መማሪያ ከግቢ ውጪ ነው ማደሪያቸው ግን ከሁሉም ጋር ተመሳሳይ ነው፥ ለት/ት ጊዜ ግን ወደ  class መግቢያና መውጫ ሰአቶች  ላይ የግቢ Bus የሰርቪስ አገልግሎት ይሰጣቸዋል

የEnginering ሳይንስ department ብዛት: 7
1, Electrical and computer   
      engineering
2, Mechanical engineering
3, Civil engineering
4, COTM (construction  
     technology management)
5, Industrial engineering
6, Chemical engineering
7, Food engineering


የምግብ ነገር ብዙም አያሳስብም
ግቢ ውስጥ ሁለት አዳራሽ ያለው የጊቢ ካፌ እና ሶስት ላውንቾች ይገኛሉ

ግቢው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች አገልግሎቶች
1. ላውደሪ
2. ፀጉር ቤት
3. አነስተኛ ሱቆች (not mini market, not super market) ነገር ግን ብዛት ነገር አላቸው መገኛቸው ለወንዶች ቅርብ Block 34 ለሴቶች ቅርብ ዶርሚተራቸው መውጫ ላይ

ሌላው ደግሞ  ግቢው እንደ አምናው ትራንስፖርት ላምበረት መናኀሪያ( አዲስ አበባ) ያዘጋጃል ማለትም ከአ.አ እስከ ግቢ ድረስ በ ግቢ Bus  በነፃ ሲገቡ ተማሪ ሕብረቶች እና ክበባት አቀባበል ያደርጉላቸዋል ።

                 ══ •⊰✿【📚👨‍🎓👩‍🎓📚】✿⊱• ══
                         Eᴛʜɪᴏ Sᴛᴜᴅᴇɴᴛ Gᴜɪᴅᴇ ™
   


Adama Science & Technology University ( ASTU )

መገኛ ፡ አዳማ , አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስአበባ በ 100km እርቀት የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ ካሏት ሁለት የ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ አንዱ ነው ።
በውስጡ ያሉ ግቢዎች ፡ አንድ ለናቱ ነው
የአየር ሁኔታ ፡ ሞቃታማ በተለይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ትንሽ ይሞቃል ፤ ይህን እንጂ ማታ ማታ ደግሞ ያልተጋነነ ብርድ ስለሚኖር ሹራብ ነገርም ያስፈልጋቹሃል ።

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የ ASTU አዲስ ገቢ ተማሪዎች። በስተመጨረሻም እንደተመደባችሁ ስንሰማ እጅግ ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አላችሁ። ( የ Senior ደስታ ጦጣዎችን እያዩ መዝናናትም አይደል😂...ስቀልድ ነው) እውነቱን ለመናገር የ ASTU Seniorኦች ከ አንዱ ላይብረሪ ስር ቁጭ ብሎ Tiktok ከማየት ወጪ ፍሬሽ ላይ ሙድ የሚይዝበት time የለውም (አያሳስባችሁ☺️🙏) ከዛ በተጨማሪ ደግሞ እናንተን በተለያዪ ነገሮች ለማገዝ ተዘጋጅተው የሚጠብቋችሁ የተማሪ ፖሊሶችና በጎ ፍቃደኞች አሉ። (ምንድነው ገና ሳንጠራ እንደዚህ ማሸርገድ🤨)
ያው እንግዲህ መምጣታችሁ ስለማይቀር ስለ ASTU በጎች ልንገራችሁ (ማወቅ ስላለባችሁ🤓)

የASTU ጅብ

ጅብ ሲፈጠር የተፈጠረው ጅብ ሆኖ ሲሆን የ ASTU የሚል ቅድመ ግንድ ሲጨመርበት በግ ይሆናል☹️። ታዲያ በግ ነው ብላችሁ እንደ በግ እንዳትንቁት(በግ ይናቃል እንዴ🤔) ያኔ በጉ እሱ ሳይሆን እናንተ ናችሁ...(በጎች🤓)

ታዲያ ፍሬሽ ሁልጊዜ ሲመጣ አንድ የተለመደች ነገር አለች ... ምን ?😳

ሰብ ሰብ ብሎ በጀማ ጅብ ማራወጥ (ማሯሯጥ😅)። ከጅብ ነክ ነገሮች ስንወጣ ደሞ ማታ ላይ ዶርም አካባቢ ቁጭ ብሎ Mini militia🔫🔫 መጫወትም የተለመደ ነው።

Science & Technology  ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ እሚሰጣቸው Departmentoch ውስን ናቸው ማለትም Engineering እና Applied Science ፊልዶች ብቻ ናቸው ።

Under   Engineering there are 3 schools
1. Electrical
2.Mechanical
3.Civil

Under electrical engineering or CSE there are 3 streams
A) Electrical and computer engineering
B) Electronics and communication engineering
C) Power and control engineering

Under Mechanical engineering
A. Chemical
B. Mechanical
C. Material

Under civil and arc school.
A.Architecture
B. Civil
C. Water resource management and hydrolic Engineering
D. Geomatics
E. software engineering

Departments of Applied Natural Sciences are
*.Applied Biology
*.Applied Chemistry
*.Applied Geology
*.Applied Mathematics
*.Applied Physics
*.pharmacy
*.industrial.....

ወደ ዩኒቨርስቲው ለመቀላቀል ፈተና ያለው ሲሆን እሚቀበላቸው ተማሪወች ውስን ናቸው ተማሪ እምንቀበለው በ Laboratory ኣችን ልክ ነው ብለው ስለሚያምኑ ! በጠቅላላ ግቢው ውስጥ ከ Fresh እስከ Masters 7000 ተማሪወች 2000 ሰራተኞች ይገኛሉ ።

🎯 ተማሪወች ትንሽ ከመሆናቸው አንፃር ምግብ ከየትኛውም ግቢ የተሻለ ነው ። 

📕 library 📖

1-Central Library
2-Applied Library
3-Liberal arts library
4-Post graduate library
5-Females library

🎯 እንዲሁም በየ department ቶች  የየራሳቸው library ያላቸው ሲሆን የሴቶቹ ለብቻቸው እሚጠቀሙበትም አላቸው ። ሌላው ነገር libraryወቹ በውስጣቸው በጣም ፈጣን WiFi & Computer አላቸው ። ግቢው ለሚጠቀምበት በጣም ብዙ laboratory ወች አሉ ።

🏖 DSTV  ግቢው ውስጥ Anfi እሚባል ቦታ አለ እዛ ላይ በ cinema standard led screen አለ እንዲሁም ሶስት ቦታወች ላይ አነስተኛ screenoch አሉ ። ለሴቶች ትንሽ ሻል ያለ አገልግሎት ይሰጣል በዶርመተሪ በlibraryም በብዙ ነገር ይጠቀማሉ !

💦 የራሱ ውሀ ማጣሪያ ያለው ሲሆን ፤ ብዙም የውሀ ችግር የለም መብራት አይጠፋም ከጠፋም በ 5 ደቂቃ ውስጥ እሚነሳ automatic generator አለ ። Dormitory አሪፍ  የሚባል ነው ።  የግቢ መግቢያ ሰዓት 3:00 ከሌሎች የተሻለ ነው ። ሌላው በፍፁም ሰው እማይተናኮሉ ለማዳ ለመባል እሚቀርቡ ጅቦች አሉ ።

🥇 በጣም ጠቃሚ ነገር 🥇

🎯 ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በተለየ ነው ት/ት እሚሰጠው ለምሳሌ Common course እሚባል ነገር የለም engineering እሚገባ ቀጥታ pre engineering ይማራል  Applied ም እንደዛው ነው ።

🎯 GPA ከ 3.5 በላይ ካለ እና ሌላ ፊልድ ደርቦ መመረቅ ለሚፈልግም dual degree ይሰጣል 2 degree ማለት ነው ።  International degree መስጠትም እጀምራለሁ ብሎ ለ2013 ባች ቃል ገብቷል ::

   Launch 🍔
ke 35-45 new hulum megeboch,.....
▫ Beyayenet.......35birr
▫ shero...............35birr
▫ pasta................40birr
▫ Ruz.......................35birr
Ena be egna bach maletem 2013 entry yeneberenew begna adadis field tejemeruwal
eg. Ke engineering field 👉 (software 👩‍💻 engineering),
ke applied science👉(pharmacy ,industrial...)
Ena gibiw international 🌎 degree esetalew bemil curriculumun revise argotal lemesale final ke chapter-1 eske mechereshaw yemetal(yehe addis yetejemere new begna😂)
ena continuous assessment biseru enkuan final ke 40% belay mametat must new(be addisu curriculum)

                 ══ •⊰✿【📚👨‍🎓👩‍🎓📚】✿⊱• ══
                         Eᴛʜɪᴏ Sᴛᴜᴅᴇɴᴛ Gᴜɪᴅᴇ ™
   


ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

መገኛ: አማራ ክልል ም/ጎጃም
ከ አ.አ 313km ትገኛለች በጣም ውብና ያማረች ውብ ከተማ

የአየር ጸባይ:  ቀን ላይ ሞቃታማ ስትሆን ምሽት ላይ ና ጠዋት ላይ  ትንሽ ቅዝቃዜ አለ.

🚩የታላቁ ደራሲ የ ሀዲስ አለማየሁ (ፍቅር እስከ መቃብር) እንዲሁም የበላይ ዘለቀ: የ ዮፍታሄ ንጉሴ እናት ሀገር ስትሆን ህዝቦቿ ከቤተሰባችን በላይ አቅፈውና ደግፈው ፍቅር ሰጥተው ያኖሩናል ወደዚች ሀገር ሲመጡ ዘረኝነት የሚባል ነገር አይኑ ጠፍቶ ተቀብሮ ፍቅር የሚባለው ነገር ዘረኝነት መቃብር ላይ በቅሎ ታገኙታላችሁ ሌላ በማርና በጠላ አንታወቃለን
  ዮንቨርሲቲው ከ ከተማው  በ1km እርቀት ላይ ይገኛል የ 3 ብር ትራንሰፖርት ማለት ነው


  ሁለት ግቢ አለን ዋናው ግቢና ቡሬ Campus   በነገራችን ላይ ቡሬ ከ ማርቆስ 115km ርቀት ላይ ትገኛለች  ይህም የ50ብር ትራንሰፖርት ማለት ነው
 
የሚሰጣቸው ት/ቶች ሰንመለከት የማይሰጠው የት ክፍል የለም ግን  በ social በኩል እንደ markrting, banking & finance   አይሰጥም መቼም ከዚህ ውጭ ምርጫ እንደማይኖሮ ተስፋ አደርጋለሁ::

ስለ ትምህርት ነክ እና ስለ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ሙሉ መረጃ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
            ⚜️ Eᴛʜɪᴏ Sᴛᴜᴅᴇɴᴛ Gᴜɪᴅᴇ ™ ⚜️


Wollo University

መገኛ ፡ ደሴ( አማራ)
የግቢ ብዛትና የአየር ሁኔታ ፡ ዩንቨርሲቲው ሁለት ግቢዎች ያሉት ሲሆን እነሱም ደሴ ከተማ እና ኮምበልቻ ከተማ ላይ ይገኛሉ፤ ሁለቱ ከተሞች በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች ቢሆኑም የአየራቸው ፀባይ ግን ለየቅል ነው።

ደሴ ከተማውም በመጠኑ ብርዳማ ሲሆን ግቢው ደግሞ ትንሽ ከከተማው ወጣ ብሎ ስለሚገኝና ሰፈሩም ዛፍ ነገር ስላካበበው የብርዱ መጠን ጠንከር ይላል በተለይ ምሽት ላይ ወዝወዝ ያስደርጋል ።

ኮምበልቻ ከተማ ደግሞ የኢንዱስትሪ ከተማ ስለሆነች መሰለኝ ሞቅ ትላለች ምናልባት የፋብሪካው ጢስ ይሆን?
ለማንኛውም ኮምቦልቻ ግቢ ለምትመደቡ ተማሪዎች ቀን ቀን ሞቃታማ ማታ ማታ ደግሞ ከዶርም ወጣ ሲሉ ብርዳማ ግቢ ነው ።

ኮቻ ግቢ ልክ በልክ ነገር ናት ማለት ግቢው በጣም ሰፊ ሚባል ነገር አይደለም geographical አቀማመጡ ለተማሪዎች ሳይሆን ለወታደሮች ተብሎ design የተደረገ ሊመስላቹህ ይችላል ቢሆንም ግን ፍቅር ፍቅር ከሚሸቱት የግቢው ማህበረሰብ (ተማሪዎች) ተመጣጣኝ ካሳ ይጠብቃቹሃል።

1, ደሴ campus (main campus)
ሁሉም የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች የሚገኙበት ሲሆን በተጨማሪም ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ውስጥ የጤናውን(medicine, nursing,HO..) እና የቲቺንግን(biology, physics, chemistry..)  እና የቋንቋ ትምህርት (አረብኛ፣አማርኛ..)ክፍሎች የያዘ ግቢ ነው።

kombolcha institute of technology
ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው ግቢው የቴክኖሎጂ ግቢ ነው
በውስጡም
Engineering, computer science, fashion design and architecture የመሳሰሉትን መስኮች አቅፎ የያዘ ግቢ ነው
Engineering
- Electrical and computer engineering
- Mechatronics Engineering (robotics)
- Software engineering
- Mechanical Engineering
- Civil engineering
- Textile engineering
- water resources and irrigation Engineering
- Hydrolics Engineering
- Industrial Engineering
- Cotem
- Garment Engineering
- Leather Engineering
- Chemical engineering...
በቀጣይ ምናልባትም Biomedical engineering ሊጀምር ይችላል።
Computer science
- CS
- IS
- IT

Fashion design and architecture
የትምህርት ሂደቱ አሪፍ የሚባል ነገር ነው ቢሆንም ግን ትንሽ ያጨናንቃል ።
በግ ተራ፣ኦቨር፣ጨብሲ ምናምን ለሚያበዛ ተማሪ የግቢው የክብር መሸኛ ደብዳቤ ይበረከትለታል ( ትምሮ ፊት ይነሳዋል)
በተረፈ ግቢያችን ከዘረኝነት የፀዳ ነው እንዳልል ከኢትዮ ውጭ ያለ ዩንቨርሲቲ ስለሚያስመስልብኝ በአንፃራዊነት ከሌሎች ግቢዎች በተሻለ መልኩ ሰላማዊ ግቢ ነው ለማለት ይቻላል።(ኮሽ ብሎ አያቅም )

ኮምቦልቻ ግቢ ለምትመደቡ ተማሪዎች ግቢው የሚገኘው አስፓልት ዳር በመሆኑ  ግቢ በር ላይ በመውረድ ከመናሀሪያ ትርምስ ትድናላቹህ

ደሴ ግቢ ለምትመደቡም ሰርቪሶች ስለሚመደቡ ብዙ አታስቡ  ፤ለማንኛውም ግን ንብረታችሁን ጠንቀቅ በሉ ምክንያቱም መናሀሪያ መግባታቹህ ስለማይቀር ብዬ ነው።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ስትደርሱ የተማሪዎች ህብረት ፣ የተማሪ ፖሊስ፣ቻሪቲ ክበብ፣ የሰላም ክበብ .. ወዘተ አባላት በር ላይ ባጅ አጥልቀው ስለሚቀበሏቹህ ምንም ዓይነት ሀሳብ አይግባቹህ ።

                 ══ •⊰✿【📚👨‍🎓👩‍🎓📚】✿⊱• ══
                         Eᴛʜɪᴏ Sᴛᴜᴅᴇɴᴛ Gᴜɪᴅᴇ ™
   


ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

መገኛ ፡ ሃዋሳ : ከአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ ውብ ከተማ
Location :- Southern nation nationalities and peoples representative in sidama zone   hawasa city

የአየር ሁኔታ ፡ Mostly በቀኑ ክፍለ ጊዜ ሞቃታማ ሁና አመሻሽ ላይ ደስ የሚል አየር አላት ፤ ከተማዋ በራሱ የሆነ ደስ የሚል ነገር አላት 💐
Weather condition : hot Rainy almost the entire year the weather is more of similar to addis ababa

በውስጡ ያሉ ግቢዎ ፡ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በውስጡ ብዙ ግቢዎች ያሉ ሲሆን ከነሱም ውስጥ

1, Main campus
📍Location: Hawassa town ( found on the enterance of the city)
        Departments
- governance
- engineering
- social others
- art
- architect
- tourism
- hotel management
-  Sport
- law
- Computational science ..
               
2, Techno campus
📍Location: beside the main campus connected with the main campus though bridge
  Departments
           -->  Engineering
             --> information system
            --> programming
            --> Enla,discrit,

➦ for engineering and computer science students until 3rd year after that the student will be transfered to main campus..

3, Agri campus 
📍Location:  located on the middle o fthe city around piyasa

           Departments
              --> animal

4, Yirgalem campus
📍Location : Yirgalem  town (near hawassa city..)

          Departments
-->FB faculty of business
- marketing management
- logistic
-Accounting
-Cooperative
- management
-economics 

5, Referral campus
📍Location: located around the lake hawassa amazing view from the dorm nice sunset ...

        Departments
             --> Medicine
               --> HO
               --> nursing
               --> environmental health
               --> radiology
               --> ophtometry
               --> psychiatry

6, wendo genet agriculture
📍 Location : wendo genet
  Department   --> plant...

መብራት አይጠፋም for the white house & for african dorms አንዳንዴ  yitefal

ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሀገራችን ላይ አሉ ከሚባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ጥራቱም ሆነ በግቢ ውበቱ አንደኛ ደረጃ ከሚባሉት ተርታ የሚመደብ ግቢ ነው ።
ትምሮ በተወሰነ መልኩ ሊያጨናንቅ ይችላል ግን በግቢው ውበትና በከተማው ማብለጭለጭ ካልተሸነፋቹህ የትምህርቱ ነገር ሙድ አለው።
ጨብሲ ዘጭ ነው ሶ እንዳትበላሹ።
ከጨበሱ አይቸክሉ ፣🍺🚫
ከቸከሉ አይጨብሱ 🍻🚫
👆👆👆 እንዳትሰሙ 🙈🙉🙊

የምግብ ቤቶች ዋጋ
የምግብ ዋጋ በaverage ከ15-40 ብር ይደርሳል፥ የሁሉም ግቢዎች ዋጋ ይለያያል ።
ቡና ምናምን 5 ብር
None ካፌ ለሚፈልጉ ተማሪዎች ደግሞ fair በሆነ ዋጋ ....

                 ══ •⊰✿【📚👨‍🎓👩‍🎓📚】✿⊱• ══
                         Eᴛʜɪᴏ Sᴛᴜᴅᴇɴᴛ Gᴜɪᴅᴇ ™
   


.      የ2017 ሪሜዲያል መቁረጫ ነጥብ መግለጫ ❗️

🔅 በ 2016 ትምህርት ዘመን የ 12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች የአቅም ማሻሻያ ( Remedial Program ) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ውሳኔን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ መስከረም /2017

🔹 ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን አነስተኛ የተማሪዎች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ውጤት መቀነስ በትምህርት ዘርፉ እና በአጠቃላይ በሀገር ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊ ፣ ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዲሁም ተዛማጅ ችግሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የገጠመውን የውጤት መቀነስ ለማስተካከል የማካካሻ ትምህርት ( Remedial Program ) በተመረጡ የትምህርት አይነቶችና ይዘቶቻቸው ላይ በማስተማር እና የመመዘኛ ፈተና በመሰጠት ምዘናውን የሚያልፉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመደበኛ ፕሮግራም እንዲቀጥሉ መወሰኑ ይታወቃል ።

🔸 በመሆኑም የ 2017 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ያላቸዉን የቅበላ አቅምን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ( Remedial Program ) የመግቢያ ነጥብ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ፈተናዉን የወሰዱና ከ50 ከመቶ በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ::

1. በሁሉም አማራጮች ( በግል እና በመንግስት ተቋማት ) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት ( ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ ።

1, የተፈጥሮ እና የማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 204/600
2, የተፈጥሮ እና የማሀበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 192/600
3, ታዳጊ ክልል ና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ና ማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 192/600
4, ታዳጊ ክልል ና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ና ማሀበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 186/600
5, ማሀበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ወንድ ተማሪዎች 160/500
6, ማሀበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ሴት ተማሪዎች 155/500
7, በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 238/700
8, በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 224/700

💥 የRemedial መቁረጫ ነጥብ ላይ ግርታ ለተፈጠረባቹህ ተማሪዎች

💰በክፍያ የመንግስት ወይም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ለመማር👇

⚡️ ከ 600 ለተፈተናቹህ 600×0.31=186

600 ተፈትናቹህ 186 እና ከዚያ በላይ ያመጣቹህ ተማሪዎች በግል(በክፍያ) የመንግስት ወይም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማካካሻ ትምህርት መማር ትችላላችሁ።

⚡️ ከ 500 ለተፈተናቹህ 500×0.31=155

500 ተፈትናቹህ 155 እና ከዚያ በላይ ያመጣቹህ ተማሪዎች በግል (በክፍያ) የመንግስት ወይም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማካካሻ ትምህርት መማር ትችላላችሁ።

⚡️ ከ 700 ለተፈተናቹህ 700×0.31=217

700 ተፈትናቹህ 217 እና ከዚያ በላይ ያመጣቹህ ተማሪዎች በግል (በክፍያ) የመንግስት ወይም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማካካሻ ትምህርት መማር ትችላላችሁ።

⚡️ ከዚህ ውጭ በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች ተመድባቹህ በመንግስት ወጪያቹህ ተሸፍኖ የ Remedial ፕሮግራም ለመማር ከላይ በተቀመጠው ዝርዝር መስፈርት መሰረት ይሆናል ።

                   ══ •⊰✿【📚👨‍🎓👩‍🎓📚】✿⊱• ══
                           Eᴛʜɪᴏ Sᴛᴜᴅᴇɴᴛ Gᴜɪᴅᴇ ™

   

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.