. የ2017 ሪሜዲያል መቁረጫ ነጥብ መግለጫ ❗️
🔅 በ 2016 ትምህርት ዘመን የ 12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች የአቅም ማሻሻያ ( Remedial Program ) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ውሳኔን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ መስከረም /2017
🔹 ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን አነስተኛ የተማሪዎች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ውጤት መቀነስ በትምህርት ዘርፉ እና በአጠቃላይ በሀገር ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊ ፣ ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዲሁም ተዛማጅ ችግሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የገጠመውን የውጤት መቀነስ ለማስተካከል የማካካሻ ትምህርት ( Remedial Program ) በተመረጡ የትምህርት አይነቶችና ይዘቶቻቸው ላይ በማስተማር እና የመመዘኛ ፈተና በመሰጠት ምዘናውን የሚያልፉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመደበኛ ፕሮግራም እንዲቀጥሉ መወሰኑ ይታወቃል ።
🔸 በመሆኑም የ 2017 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ያላቸዉን የቅበላ አቅምን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ( Remedial Program ) የመግቢያ ነጥብ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ፈተናዉን የወሰዱና ከ50 ከመቶ በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ::
1. በሁሉም አማራጮች ( በግል እና በመንግስት ተቋማት ) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።
2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት ( ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ ።
1, የተፈጥሮ እና የማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 204/600
2, የተፈጥሮ እና የማሀበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 192/600
3, ታዳጊ ክልል ና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ና ማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 192/600
4, ታዳጊ ክልል ና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ና ማሀበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 186/600
5, ማሀበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ወንድ ተማሪዎች 160/500
6, ማሀበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ሴት ተማሪዎች 155/500
7, በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 238/700
8, በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 224/700
💥 የRemedial መቁረጫ ነጥብ ላይ ግርታ ለተፈጠረባቹህ ተማሪዎች
💰በክፍያ የመንግስት ወይም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ለመማር👇
⚡️ ከ 600 ለተፈተናቹህ 600×0.31=186
ከ 600 ተፈትናቹህ 186 እና ከዚያ በላይ ያመጣቹህ ተማሪዎች በግል(በክፍያ) የመንግስት ወይም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማካካሻ ትምህርት መማር ትችላላችሁ።
⚡️ ከ 500 ለተፈተናቹህ 500×0.31=155
ከ 500 ተፈትናቹህ 155 እና ከዚያ በላይ ያመጣቹህ ተማሪዎች በግል (በክፍያ) የመንግስት ወይም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማካካሻ ትምህርት መማር ትችላላችሁ።
⚡️ ከ 700 ለተፈተናቹህ 700×0.31=217
ከ 700 ተፈትናቹህ 217 እና ከዚያ በላይ ያመጣቹህ ተማሪዎች በግል (በክፍያ) የመንግስት ወይም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማካካሻ ትምህርት መማር ትችላላችሁ።
⚡️ ከዚህ ውጭ በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች ተመድባቹህ በመንግስት ወጪያቹህ ተሸፍኖ የ Remedial ፕሮግራም ለመማር ከላይ በተቀመጠው ዝርዝር መስፈርት መሰረት ይሆናል ።
══ •⊰✿【📚👨🎓👩🎓📚】✿⊱• ══
Eᴛʜɪᴏ Sᴛᴜᴅᴇɴᴛ Gᴜɪᴅᴇ ™