የማለዳ ዜናዎች
1፤ መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በወጪ መጋራት ፖሊሲ የሚከፍሉትን ክፍያ እስከ አምስት ዕጥፍ ገደማ እንደጨመረው ዋዜማ ሰምታለች። የወጪ መጋራት ክፍያ የተጨመረው፣ የአንድ ተማሪ የቀን የምግብ በጀት ከ22 ብር ወደ 100 ብር መጨመሩን ተከትሎ ነው። በአዲሱ ማስተካከያ መሠረት፣ ለአራት ዓመት የዩንቨርሲቲ ቆይታ አንድ ተማሪ ይከፍለው የነበረው ከ25 ሺሕ ብር የማይበልጥ ክፍያ ወደ 120 ሺሕ አሻቅቧል። 35 ሺሕ ብር ገደማ ይከፍሉ የነበሩት አምስት ዓመት የሚማሩ የምህንድስና ተማሪዎች ደሞ ወደ 150 ሺሕ ብር አካባቢ እንዲከፍሉ ይደረጋል። ትምህርት ሚንስቴር አዲሱን የወጪ መጋራት ተመን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገና ባይልክም፣ በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋዜማ ተረድታለች።
2፤ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል በክላስተር ከተዘራው የስንዴ ምርት 70 በመቶውን ከአርሶ አደሮች በወቅታዊ የገበያ ዋጋ ገዝቶ እየወሰደ መኾኑን ዋዜማ ሰምታለች። ባኹኑ ወቅት አንድ ኩንታል ነጭ ስንዴ በገበያ ላይ 5 ሺሕ 500 ብር እየተሸጠ ሲኾን፣ አርሶ አደሮች ግን በማዳበሪያ ዋጋ ውድነት የተነሳ ዋጋው አትራፊ እንዳልኾነ ተናግረዋል። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው አርሶ አደሮች፣ የምርታቸውን 70 በመቶ ለመንግሥት ለመሸጥ የገቡት ስምምነት ባይኖርም፣ የበላይ አካል ትዕዛዝ ነው በሚል እንዲሸጡ እየተገደዱ መኾኑን ገልጸዋል። ኾኖም ይህ አሠራር በክልሉ ወጥ በኾነ ኹኔታ እየተተገበረ አይደለም ተብሏል። የስንዴ ግዥውን ትዕዛዝ የሚያስፈጽሙት፣ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ መዋቅሮች እንደኾኑ ዋዜማ ተረድታለች።
3፤ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል። ረቂቅ ማሻሻያው፣ ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አዋጅ የሚጥሱ ፓርቲዎችን ሕጋዊነት ከመሰረዙ በፊት በጥፋቱ ክብደት ልክ እስከ 5 ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ማገድ የሚያስችለውን ሥልጣን የሚሠጥ ነው። ቦርዱ የጣለበትን እገዳ የተቃወመ ፓርቲ፣ ውሳኔው በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል የተሻሻለው አዋጅ ይፈቅዳል። ቦርዱ አገራዊ ምርጫ ማካሄድ የማይችልባቸው "ኹኔታዎች" የሚለው አንቀጽም፣ የጸጥታ ችግር፣ ወረርሺኝ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ተብሎ ተዘርዝሯል። ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤቶች ምርጫ የተመዘገቡ ዕጩዎች ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር፣ የምርጫው ውጤት እስኪገለጽ በወንጀል ተጠርጥረው እንዳይያዙ የሚከለክል አንቀጽም በማሻሻያው ተካቷል።
4፤ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ተከላካይ ቡድን (ሲፒጄ) ትናንት ባወጣው ልዩ ሪፖርት፣ ኢትዮጵያን "የተድበሰበሰ ክስ" ከሚመሠርቱ ወይም "በሽብር" ወይም "በአክራሪነት" ውንጀላ ቅጣት ከሚጥሉና ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት ከሚያስሩ አገራት ተርታ መድቧታል።
በዙህም ኢትዮጵያ ከግብጽ፣ ሩሲያ፣ ማይነማርና ቤላሩስ ተርታ ተመድባለች። ኢትዮጵያ ካሠረቻቸው ስድስት ጋዜጠኞች አምስቱ በአማራ ክልል የሚካሄደውን ግጭት ከዘገቡ በኋላ የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሠረተባቸው ሪፖርቱ ጠቅሷል። ስድስተኛው ጋዜጠኛ የሺሃሳብ አበራ በመስከረም 2017 ዓ፣ም መታሠሩንና ባለሥልጣናቱ ጋዜጠኛው የታሠረበትን ምክንያት እስካኹን እንዳልገለጡ ወይም ክስ እንዳልመሠረቱበት ሪፖርቱ ገልጧል። ኤርትራ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት 16 ጋዜጠኞችን በማሠር ቀዳሚዋ ኾና የቀጠለች ሲኾን፣ በዓለም ላይ ደሞ ከኢራንና ቬትናም ጋር ሰባተኛዋ ቀዳሚ ጋዜጠኛ አሳሪ ተብላለች።
5፤ አሜሪካ፣ በሱዳን ወታደራዊ መሪና በጦር ሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን ላይ ትናንት ማዕቀብ ጥላለች። አሜሪካ በጀኔራል ቡርሃን ላይ ማዕቀብ የጣለችው፣ ከድርድር ይልቅ የጦርነት አማራጭን መርጠዋል በማለት ነው። ጄነራል ቡርሃን የሚመሩት ሠራዊት፣ በሲቪል መሠረተ ልማቶች ማለትም በትምህርት ቤቶች፣ በሆስፒታሎችና በገበያ ቦታዎች ላይ ጥቃቶችን እና ከፍርድ ውጭ የኾኑ ግድያዎችን ይፈጽማል በማለት አሜሪካ ከሳለች። ለሱዳን ጦር ሠራዊት ጦር መሳሪያ ያቀብላሉ የተባሉ አንድ የሆንግኮንግ ኩባንያና አንድ የሱዳንና ዩክሬን ተወላጅ ግለሰብም የማዕቀቡ ሰለባ ኾነዋል። ማዕቀቡ የንብረትና ገንዘብ የማንቀሳቀስና ማንኛውም አሜሪካዊ ዜጋና ኩባንያ ጋር የንግድ ልውውጥ እንዳያደርጉ የሚያግድ ነው። አሜሪካ፣ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ዋና አዛዥ ጀኔራል ደጋሎ ላይ ከቀናት በፊት ተመሳሳይ ማዕቀብ እንደጣለች ይታወሳል።
via:ዋዜማ
#እውን_መረጃ