የጥምቀትን በዓል ያለምንም አደጋ ለማክበር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ
የጥምቀት በዓልን ከአደጋ በፀዳ ሁኔታ ለማክበር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡
ለበዓሉ አከባበር የተለያዩ ዝግጅቶችን የሚያደርጉ ወጣቶች ማስጌጫዎችን ከመስቀላቸው በፊት የኤሌክትሪክ መስመሮችን በጥንቃቄ እንዲመለከቱ እና አስቀድመው ቅኝት እንዲያደርጉ ያሳሰቡት፤ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ናቸው።
ከዚህ ቀደም በነበረው የበዓሉ አከባበር የኤሌክትሪክ መስመሮችን ለበዓሉ ተብለው በሚተከሉ ድንኳኖች ውስጥ የሚያስገቡ ሰዎች እንዳጋጠሙ ያስታወሱት አቶ ንጋቱ፤ ከዚህ በፊት ለታቦታት መሸፈኛ የሚውሉ የብረት ሰረገላዎች ከኤሌትሪክ መስመር ጋር በመገናኘታቸው 4 ወጣቶች ሕይወታቸው ማለፉን አስታውሰው የጥንቃቄ መረጃዎች እንዲወሰዱ አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪም ፀበል ለመረጨት ወደ ባህረ ጥምቀቱ የሚያመሩ አካላት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው፣ ነፍሰ-ጡሮች እና የታወቀ ሕመም ያለባቸው፣ አቅመ ደካሞችና ሕጻናት መገፋፋት ያለባቸው ቦታዎች እንዳይገቡ እንዲሁም ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች የጥንቃቄ መመሪያዎችን እንዲያከብሩም መጠየቃቸውን አሃዱ በዘገባው አመልክቷል።
ለማንኛውም የአደጋ ጥቆማ 939 አጭር መስመር ላይ መደወል እንደሚቻል የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡
#እውን_መረጃ