ልብህ ያሰበውን ጥሩ ነገር ከመፈጸም አትቦዝን። ሃሳቡ በውስጥህ አርጅቶ እስኪሞት አትጠብቅ ።
ሰዎች ምን ይሉኝ ብለህ አትፍራ ። ሰዎች ብትሠራም ባትሠራም የሆነ ነገር ማለታቸው አይቀርም። መጠንቀቅ ያለብህ ነገር ድርጊትህ በጎ ተግባር መሆኑን ማረጋገጥህን ነው።
ድርጊትህ ጥሩ መሆኑን ካመንክበት ለመተግበር ሞክር ፣ ተጣጣር ።
ድርጊትህ ሙሉ በሙሉ ባይሳካ እንኳ በመሞከርህ ብቻ የህሊና እረፍት ታገኛለህ ።
በተከታታይ ከሠራህ ደግሞ እየሠራህ ማሻሻልህ አይቀርም። ጥሩ ነገር ለማድረግ ምቹ ጊዜ አትጠብቅ። ምቹው ጊዜ ሃሳቡ ወደ ጭንቅላትህ የመጣበት ጊዜ ነው ።
መማር ባለብህ ጊዜ ተማር፣
መሥራት ባለብህ ጊዜ ሥራ፣
ዱአ ማድረግ ባለብህ ሰአት ዱአ አድርግ
መጻፍ ባለብህ ጊዜ ጻፍ፣
ማረፍ ባለብህ ጊዜ እረፍ ።
ሁሉን በጊዜ አድርገው ፣ ጊዜው ካለፈ ጠዓሙም ውጤታማነቱም እንደዛው ማለፉ አይቀርምና ።
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-
=t.me/FKR_ESKE_JENET