Postlar filtri


ቀሲስ በላይ መኮንን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እና በ10 ሺህ ብር ተቀጡ

ሐሰተኛ ሰነድ ተጠቅመው ከአፍሪካ ሕብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ገንዘብ ለማውጣት ሞክረዋል በሚል የወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው ቀሲስ በላይ በአምስት ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር እንዲቀጡ ተወስኗል።




ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀር ግፊት እያደረጉ መሆናቸው ተሰማ


ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ “በመወለድ የሚገኝ ዜግነት” በመባል የሚታወቀው የዜግነት መብት’ እንዲቀር ወይም እንዲቋረጥ የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ ፈርመዋል፡፡

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1868 የጸደቀው 14ኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ አንድ ሰው የወላጆቹ የዜግነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ እስከተወለደ ድረስ የዜግነት መብቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን የሲቪል መብቶች ዋና አካል ተደርጎ ይታያል፡፡

የፕሬዝደንት ትረምፕ ትዕዛዝ ታዲያ በአስፈጻሚው አካል ሥልጣን እና በሕገ መንግሥት ማሻሻያው ዙሪያ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ ክርክሮች ቀስቅሷል።


የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተጨማሪ ብድር አጸደቀ

የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)፣ ኹለተኛውን የኢትዮጵያ የተራዘመ ብድር ግምገማ በማጠናቀቅ ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ትናንት ተጨማሪ 248 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል።

ድርጅቱ ለኢትዮጵያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ባለፈው ሐምሌ ካጸደቀ ወዲህ፣ እስከ ትናንት የለቀቀው ብድር 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።

መንግሥት ለማኅበራዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብሮች የሚሠጠው ድጎማ ከተጠበቀው በታች መኾኑን በግምገማ ሪፖርቱ የገለጠው ድርጅቱ፣ ለጉዳት ተጋላጭ ለኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሴፍቲ ኔት ድጋፎችን ማጎልበት ያስፈልጋል በማለት መክሯል።

ድርጅቱ፣ የነዳጅ ዋጋ የመንግሥትን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሊመልስ በሚችል ደረጃ መስተካከል እንዳለበትም ምክረ ሃሳቡን ለግሷል።


በደቡብ ሱዳን በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ። አውሮፕላኑ ከግዛቷ ተነስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በማቅናት ላይ እያለ መከስከሱን የግዛቱ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ጋትዌች ባይፓል መግለጻቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።


አምነስቲ ''በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ ያስፈልጋል›› አለ

በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ፡፡

በክልሉ መንግስት መር የዘፈቀደ የጅምላ እስር መፈጸም ከተጀመረ ድፍን አራት ወራት ተቆጥረዋል ያሉት የድርጅቱ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታ በክልሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ ባለበት ሁኔታ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታ ከማሳፈርም በላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የመብት ተሟጋቾች ጭምር በጅምላ ታፍሰው በግፍ የታሰሩት ሁሉ እንዲለቀቁ ተጽዕኗቸውን ተጠቅመው ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡




የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር በኋይት ሀውስ ሊገናኙ ነው

ኔታንያሁ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዓለ ሲመት ከፈጸሙ በኃይት ሀውስ የሚያገኟቸው የመጀመሪያው የውጭ ሀገር መሪ ይሆናሉ ተብሏል።


የጎፋ ተፈናቃዮች ሰብአዊ ድጋፍ አለማግኘታቸውን የተናገሩ ሰዎች መታሰራቸው ተሰማ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ 627 አባወራዎች በቂ ሰብአዊ ድጋፍ አለመድረሱን ለብዙኅን መገናኛ የገለጹ ስምነት ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ቤተሰቦቻቸው እና የወረዳው ነዋሪዎችን ዋቢ ባደረገበት አሜሪካ ድምፅ በዘገባው አመልክቷል።


አሜሪካ ኤም 23 ቡድን የወሰደውን እርምጃ አወገዘች

በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 የተባለው ታጣቂ ቡድን ቁልፍ የሆነችውን የምሥራቅ ኮንጎ ዋና ከተማ ተቆጣጥሬአለሁ ማለቱን ተከትሎ አሜሪካ ድርጊቱን አውግዛለች።

በተያያዘ ዜና የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቲሺኬሴዲ እና ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ቀውሱን በሚመለከት ነገ ረቡዕ ለመወያየት ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳስታወቀው ትላንት ሰኞ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ቲሺሴኬዲን በስልክ ያነጋገሯቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ " በሩዋንዳ የሚታገዘው ኤም 23 ጎማ ላይ አድርሶታል የተባለውን ጥቃት አውግዘዋል። አሜሪካ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክን ሉዓላዊነት እንደምታከብር አረጋግጠውላቸዋል" ብሏል።

ግጭቱ ወታደራዊ መፍትሄ የማይገኝለት እንደሆነ የጠቆሙት የኬኒያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ፕሬዝደንት ሺሴኬዲ እና ፕሬዝደንት ካጋሜ ነገ ረቡዕ ለመወያየት እንደተስማሙ አመልክተዋል።


ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በበቃ እርሻ ላይ የታፈሱ ወጣቶች በግዳጅ ይሰማሩበታል በሚል የቀረበበትን ክስ "ሐሰት" ነው አለ



ድርጅቱ በቅርቡ ወደ በበቃ ቡና እርሻ ታዳጊዎች እየተወሰዱ ነው በሚል የቀረበው ዘገባ "እጅግ ከእውነት የራቀና የተቋሙን መልካም ገፅታ የሚያጠለሽ" ብሎታል።

"በእርሻ ቦታው ስራ ለማሰራት ነው እንኳን እንዳይባል ይህ ወቅት የቡና ለቀማ ጊዜ እንዳልሆነ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆኑ ማንኛውም ለዘርፉ ትንሽ ቀረብ የሚል ሰው በሚገባ ይገነዘበዋል"

ያለው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዜጎችን ክብር፥ ደህንነትና እድገት በማንኛውም ሁኔታ ከፍ ለማድረግ በሁሉም ድርጅቶቹ ብቻ ሳይሆን በሃገር አቀፍ ደረጃም ጭምር በሚያደርጋቸው አበርክቶዎቹና ሰው ተኮር ስራዎቹ ማረጋገጥ የቻለ ተቋም ነው ብሏል።




ቀይ መስቀል በኢትዮጵያ የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት መሠረተ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የመሰረተው ትምህርት ቤቱ ዋና ዓላማው ትውልድን በሰብዓዊነት ማነጽ ነው ተብሏል፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የተስፋፉ ግጭቶችን ተከትለው የታዩ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ለሰብዓዊ ትምህርት ቤት መቋቋም አቢይ ምክንያት ነው ተብሏልም፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ትናንት ሰኞ ጥር19/2017 በይፋ ያቋቋመውና ስራ ያስጀመረው የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት የሰላም፣ የግጭት-አልባ እና ሰብዓዊነት መርህዎች ላይ አተኩሮ ትምርት የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡




ዓለማቀፍ የቁርአንና አዛን ውድድር በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ

ዓለማቀፍ የቁርአንና አዛን ውድድር በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ። የፊታችን ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስቴዲየም በሚካሄደው ታላቅ ዓለም አቀፍ የቁርአን ውድድር ላይ ከ60 አገራት የሚመጡ 100 የሚደርሱ ተወዳዳሪዎች፣ የልኡካን ቡድን ተሳታፊዎች እንዲሁም ኢንቨስተሮችና ታዋቂ ግለሰቦች እንደሚገኙ ተጠቁሟል።


የውድድር መድረኩ ቱሪስቶችን ወደ አገራችን ለመሳብ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የተገለፀ ሲሆን፤ የአገር ገጽታ ግንባታ አበርክቶውም የጎላ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡


በአማራ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ያስፈልጋል ተባለ

በአማራ ክልል “ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ አሁን በክልሉ ባለው ግጭት” ምክንያት ጉዳት የደረሠባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት 112 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በጦርነቱ እና በአሁኑ ግጭት በርካታ ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸውን የገለጹት የቢሮው ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተር ዘመነ አበጀ ለአብነትም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልጸዋል።


ሲአይኤ ኮሮና ቫይረስ ከቤተሙከራ ያመለጠ ነው አለ

አዲሱ የአሜሪካ ማዕከላዊ ስለላ ድርጅት ወይም ሲአይኤ ሀላፊ ጆን ራትክሊፍ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ በተፈጥራዊ መንገድ የተከሰተ ሳይሆን ከቤተ ሙከራ ያመለጠ የመሆን እድሉ ሰፊ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን መሞት ምክንያት የሆነው ቫይረስ እንደ ሀገር እስካሁን ወጥ አቋም አለመያዙ ትክክል አለመሆኑንም ጠቅሰዋል።

ቻይና በበኩሏ ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ አምልጧል የሚለው አስተያየት አሜሪካ ቻይናን ለማጥቃት በሚል የምታሰራጨው መረጃ ነው በሚል ውድቅ አድርጋለች።


ኮንጎ ከሩዋንዳ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች❗️

በሩዋንዳ በሚደገፉት አማፂያን እና በዴሞክራቲክ ኮንጎ መንግስት ኃይሎች መካከል፤ ቁልፍ በሆነችው ጎማ ከተማ ምሥራቃዊ ክፍል ጦርነት የተቀሰቀሰ ሲሆን፣ በትንሹ 13 የሰላም አስከባሪ ሃይሎች እና የውጭ ሃገር ወታደሮች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ተፈናቅለዋል። ዴሞክራቲክ ሪፐሊክ ኮንጎም ከሩዋንዳ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች።

የኤም 23 አማፂ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መኖሪያ እና የሰብዓዊና የጸጥታ ማዕከል ወደ ሆነችው ወደ ጎማ ግዛት በመገስገስ ብዙ ስፍራዎችን ተቆጣጥሯል።


ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛውን ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው

ሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

“ከቃል እስከ ባህል “ የሚል መሪ ቃል የተሰጠው ይህ ጉባኤ ከ 1 ሺ 7 መቶ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙበት ተገልፆል።

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ የውጭ ሀገራት ወዳጅ ፓርቲዎች ተወካዮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙም ተነግሯል።



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.