Gettechinfo ®️


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Telegram


info about technology ስለቴክኖሎጂ መረጃ
Facebook ቻናላችንን ይከተሉን
https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


የመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያው ሰው አልባ አውሮፕላኖች አቅርቦት ስርዓት ተጀመር (Drone Delivery System)
------------------------------------------------------------------------
ታህሳስ 10፣ 2017፣ ዱባይ የመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያውን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የቤት ለቤት አገልግሎት ስርዓት በይፋ ጀምሯል፣ ይህም በሀገሪቱ የቴክኖሎጂ እድገቶች ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። ይህ ተነሳሽነት በዱባይ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን (DCAA) የሚመራ ሲሆን የመጀመሪያውን የስራ ፍቃድ ለቻይና የቴክኖሎጂ ግዙፉ Meituan ቅርንጫፍ የሆነው ኬታ ድሮን ሰጠ። የስርአቱ የሙከራ ምዕራፍ በዱባይ ሲሊኮን ኦሳይስ (ዲኤስኦ) የጀመረው ስድስት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም አራት የመላኪያ መንገዶችን ለመፍጠር ነበር። የሚቀርቡት ቁልፍ ቦታዎች የሮቸስተር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (RIT-Dubai) እና ዱባይ ዲጂታል ፓርክን ያካትታሉ፣ ምግብ፣ መድሃኒት እና አስፈላጊ ነገሮች በፍጥነት ማድረስ ላይ ያተኮሩ።
የዱባይ አልጋ ወራሽ ሼክ ሃምዳን ቢን መሐመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም የመክፈቻ ሥርዓቱን የመንግስት የቴክኖሎጂ እድገትን ለመምራት ያለውን ቁርጠኝነት በማሳየት የዚህ ጅምር አስፈላጊነት ጎልቶ ታይቷል። ይህ ተነሳሽነት ምሳሌን ብቻ ሳይሆን ከተማዋን ከሦስቱ ዋና ዋና የከተማ ኢኮኖሚዎች ተርታ ለማሰለፍ ካለው ከዱባይ የኢኮኖሚ አጀንዳ ጋር ይጣጣማል ብለዋል። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ለገና በቴሌ ብር እስከ 15 ሚሊዮን ያሸንፉ
ቴሌ ለገና እስከ 15 ሚሊዮን ብር የሚያሸንፉበትን ጨዋታ አዘጋጅቷል።ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም አፑን አውርደው ይጫወቱ
I am inviting you to download telebirr SuperApp, register and make a transaction to get reward. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index1230.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1722184804351104&inviterId=980093187200004&language=en&campaignType=christmas&time=Jan-01-2025-Jan-07-2025




ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን በ67 ከተሞች አስጀመረ
**

ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ፍጥነት እና አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችለውን ዘመናዊ የ4ጂ LTE የሞባይል አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 67 ከተሞች አስጀምሯል፡፡

የ4ጂ LTE ኔትዎርክ ማስፋፊያው በከተሞቹ በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ ላይ የሚገኘውን የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ በቀጣይም የቴሌኮም ኔትዎርክ እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከኢትዮ ቴሌኮም የማኀበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡


#NGAT
ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከታህሳስ 21 እስከ 25/2017 ዓ.ም ይከናወናል፡፡
ለመመዝገብ 👇
HTTPS://NGAT.ETHERNET.EDU.ET
ከምዝገባ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል።
የመፈተኛ USER NAME እና PASSWORD በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (
https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ቻይና ከመቶ ሺህ በላይ በራሪ ተሽከርካሪዎችን ልታመርት ነው
+++++

ቻይና እአአ በ2030 በአየር እየበረሩ ከተሞቸን የሚያገናኙ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ገበያውን ለመቆጣጠር እየሰራች ነው፡፡

ይህ ሌላኛው የኢኮኖሚ ከፍታዋ መነሻ እንደሆነ የገለጸችው ቻይና፣ የዚህ ስራ ግብ የከተሞች ትራንስፖርት አገልግሎትን በአየር ታክሲዎች ፣ በጭነት ድሮኖች እና በኤሌክትሪክ በሚሰሩ የአየር ላይ ተሽከርካሪዎች መሰረታዊ እመርታ ማምጣት እንደሆነ አስታውቃለች፡፡

አውቶ ፍላይት እና ኢ ሀንግ የመሳሰሉ ኩባንያዎቸ በጃፓን የሙከራ በረራ በማድረግ የተሳካላቸው ሲሆን ይህንን ሙከራ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና በመካከለኛው ምስራቅ ለማስፋፋትም ትልቅ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
የቻይና ደቡባዊ የቴክኖሎጂ ማዕከል ሼንዘን ከተማ በበረራ ታክሲዎች እና በአውሮፕላን ማጓጓዣ ዘርፍ ግንባር ቀደም ለመሆን በማለም በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘርፉን ለማስፋፋት 12 ቢሊዮን ዩዋን (1.7 ቢሊዮን ዶላር) ለመሠረተ ልማት ግንባታ ለማፍሰስ ቃል ገብታለች ።
ሼንዘን በ2026 ከ1,200 በላይ የማኮብኮቢያና የማረፊያ ስፍራዎችን ለመገንባት ዕቅድ የያዘች ሲሆን ለዚህም በበረራ ወቅት የሚኖረውን የአየር ትራፊክ የኔት ወርክ፣ የሎጂስቲክስ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ስራ ለማቀላጠፍ እየሰራች ትገኛለች፡፡
የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ እንዳስታወቀው በ 2025 ሌሎች 658 መገልገያዎችን ለማጠናቀቅ አቅዳ እየሰራች ነው፡፡
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


Gemini ምንድን ነው?
Gemini በጎግል የተገነባ ትልቅ የቋንቋ ሞዴል ነው። ይህ ማለት በሰው ቋንቋ የተጻፉ ጽሁፎችን በመመልከት እና በማጥናት የተለያዩ ቋንቋዎችን መረዳትና መጠቀም የሚችል ኮምፒውተር ፕሮግራም ነው።
ምን ያደርጋል?
* ይተረጉማል: አንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ ይለውጣል።
* ይፈጥራል: ግጥሞችን፣ ኮድ፣ ኢሜይሎችን፣ ደብዳቤዎችን እና ሌሎችንም ይጽፋል።
* ይመልሳል: ጥያቄዎችህን በዝርዝር ይመልሳል።
* ይማራል: አዲስ መረጃዎችን በየጊዜው ይማራል እና ይሻሻላል።
እንዴት ይሰራል?
Gemini በሰው ልጆች እንደሚያደርጉት በተመሳሳይ መንገድ ቋንቋን አይረዳም። በምትኩ፣ በጣም ትልቅ የሆነ የመረጃ ቋት ውስጥ ያሉ ቃላትን እና ሀረጎችን በማነፃፀር እና በማጣመር መልስ ይሰጣል።
ለምን አስፈላጊ ነው?
Gemini እንደ ትርጉም፣ የመረጃ ፈልግ፣ እና የፈጠራ ስራዎች ባሉ በርካታ አካባቢዎች ሊረዳን ይችላል። ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ሌላ ቋንቋ የማይናገር ሰው ጋር እንዲግባባ ሊረዳው ይችላል ወይም አንድ ሰው አዲስ ነገር እንዲማር ሊረዳው ይችላል።
ምን አይነት ጥያቄዎች ልንጠይቅ እችላለን?
* የእውነታ ጥያቄዎች: ለምሳሌ፣ "የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ?"
* የትርጉም ጥያቄዎች: ለምሳሌ፣ "Hello" በአማርኛ ምን ይባላል?"
* የፈጠራ ጥያቄዎች: ለምሳሌ፣ "ስለ አንድ ሮቦት የሚናገር አጭር ታሪክ ጻፍልኝ።"
አፑን(App) ከPlay Store በማውረድ በስልካቹ መጫን ትችላላቹ
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


የመውጫ ፈተና ( Exit Exam)

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት ላይ  የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ( Exit Exam)ጊዜን ትምህርት ሚኒስቴር  አሳውቋል።

በዚህ መሰረት በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት ላይ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።


የተፈጥሮ ቋንቋ ማቀነባበሪያ ምንድነው( What is Natural Language Processing (NLP))
የተፈጥሮ ቋንቋ ማቀነባበሪያ (NLP) በተፈጥሮ ቋንቋ በኮምፒውተሮች እና በሰዎች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ የሚያተኩር የሰው ሰራሽ ኢንተለጀንስ (AI) ቅርንጫፍ ነው። የNLP ግብ ኮምፒውተሮች የሰውን ቋንቋ ትርጉም ባለው እና ጠቃሚ በሆነ መንገድ እንዲረዱ፣ እንዲተረጉሙ እና ምላሽ እንዲሰጡ ማስቻል ነው።
የNLP ቁልፍ ጉዳዮች (Key Areas of NLP)
1. የጽሁፍ ትንተና (Text Analysis)፡- ትርጉም ያለው መረጃ ለማውጣት ጽሑፍን መተንተን፣ እንደ ስሜት ትንተና፣ አርእስት ሞዴሊንግ እና የተሰየመ አካል እውቅና።
2. የቋንቋ መፍጠር (Language Generation): ወጥነት ያለው እና ከዐውደ-ጽሑፉ ጋር ተዛማጅነት ያለው ጽሑፍ መፍጠር። ይህ እንደ ቻትቦቶች፣ ይዘት መፍጠር እና ማጠቃለያ ያሉ መተግበሪያዎችን ያካትታል።
3. የንግግር ማወቂያ (Speech Recognition)፡ የሚነገር ቋንቋን ወደ ጽሁፍ መለወጥ፣ በድምጽ የሚንቀሳቀሱ ስርዓቶችን እና ምናባዊ ረዳቶችን ማንቃት።
4. የማሽን ትርጉም (Machine Translation)፡ እንደ ጎግል ተርጓሚ ባሉ አገልግሎቶች ላይ እንደሚታየው ጽሑፍን ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ በራስ-ሰር መተርጎም።
5. ሴንቲሜን አናላይሲስ (Sentiment Analysis)፡ ከጽሁፍ አካል በስተጀርባ ያለውን ስሜታዊ ድምጽ መወሰን፣
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ 100 ሺህ ዶላር መመንዘር ጀመረ
*****

ቢትኮይን የተሰኘው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ (ክሪፕቶ ከረንሲ) በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

በዚህም የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ100 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ይህም በዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ ታሪክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

የቢትኮይን ዋጋ እንዲህ ሊጨምር የቻለው ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክሪፕቶ ከረንሲን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን እንደሚቀበሉ በማሳወቃቸው መሆኑ ተገልጿል።

ትራምፕ የቀድሞን የአሜሪካ የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽነር ፖል አትኪንስ የሃገሪቱ የስቶክ ገበያ የሆነውን ዎል ስትሪት እንዲመሩ ማጨታቸው ከተሰማ ከሰዓታት በኋላ የቢትኮይን ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ሚስተር አትኪንስ አሁን ካሉት የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽን ኃላፊ ጋሪ ጌንስለር የበለጠ የክሪፕቶ ከረንሲ ደጋፊ ስለመሆናቸውም ነው የተገለፀው።

ዶናልድ ትራምፕ ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ክሪፕቶከረንሲን የተቹ ቢሆንም አሁን ግን አሜሪካን የምድራችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ ሲሉ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ እየናረ መምጣቱ ተጠቁሟል።

በተለይም ባለፈው ወር ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ የቢትኮይን ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ሲያሳይ መቆየቱ ነው የተገለፀው።

አንዳንድ ትልልቅ ኩባንያዎችና ተቋማት ቢትኮይንን እንደ ገንዘብ መቀበል መጀመራቸውም ለተፈላጊነቱ ማደግ ሌላ ምክንያት ነው ተብሏል።

የዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ 100 ሺህ ዶላር መግባቱን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ያሉ የቢትኮይን ተጠቃሚዎች እና ደንበኞች ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ ነው።


ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እገዛ በሚሰሩ ሮቦቶች የመንገድ ጥገና አካሄደች፡፡

ሮቦቶች እና ሾፌር አልባ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የተከናወነው የመንገድ ጥገና 158 ኪ.ሜ ርዝማኔ እንዳለው ተገልጿል፡፡

መንገዱ የሀገሪቱን መዲና ቤጂንግን ከደቡባዊ የቻይና ግዛቶች ጋር የሚያገናኝ የፍጥነት መንገድ ነዉ፡፡ በስራዉ ላይ ድሮኖች የመንገዱን አጠቃላይ ገጽታ በመከታተል ምስላዊ መረጃዎችን ያቀርባሉ፡፡ ምስሉ ላይ ያለዉን መረጃ መሰረት በማድረግ ሮቦቶቹ ጥገና በሚያስፈልገዉ የመንገድ ክፍል ላይ በመሰማራት አስፈላጊውን ጥገና ያደርጋሉ፡፡

በስራዉ ላይ የተሳተፉት ማሽኖች በስራ ወቅት ለሚገጥማቸዉ ችግር ምላሽ መስጠት እንዲችሉ ሆነዉ የበለጸጉ ናቸዉ፡፡ በመሆኑም ደህንነቱ የተጠበቀና ወጪ ቆጣቢ የጥገና ስራ መስራት ስለመቻሉ ሀይዌይስ ኢንዱስትሪ የተባለው ድረ-ገጽ ዘግቧል፡፡

ይህ ጅማሮ ጥራታቸውን የጠበቁ መንገዶችን ለመገንባት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ፣ ሮቦቶች እና ሾፌር አልባ ተሽከርካሪዎች ትልቅ አቅም እናዳላቸው ያሳየ ስለመሆኑ ተጠቁሟል። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ ያደርጋል
*************
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን በቅርቡ አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል።

"Ethiopia Land of Origin" የሚል ስያሜ የተሰጠው አውሮፕላኑ 400 መቀመጫዎች ያሉት ነው። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ቻይና ወሳኝ በተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዓለምን መምራት ጀምራለች ቻይና ወሳኝ በተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዓለምን መምራት መጀመሯን የአውስትራሊያው የስትራቴጂክ ፖሊሲ ጥናቶች ኢንስቲትዩት ባወጣው ሪፖርት ጠቆመ።
ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት ቻይና ከ44 ቁልፍ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ውስጥ በ37ቱ ከምዕራባዊያኑ ቀዳሚ ደረጃን መያዟን አረጋግጧል።
ሰው ሠራሽ አስተውሎ፣ የኤሌክትሪክ ባትሪ፣ ሰው አልባ አውሮፕላን፣ የኑክሌር ኃይል፣ የሮቦት ሳይንስ እና የሕዋ ምርምር ቻይና ከፍተኛ ዕድገት ያሳየችባቸው የቴክኖሎጂ ዘርፎች ናቸው ተብሏል።
በሳይንሳዊ ምርምር ስመ-ጥር የሆኑ 10 ተቋማት ሁሉም ቻይና ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውም ተገልጿል።
አሜሪካ እና አውሮፓ በወሳኝ የቴክኖሎጂ ዘርፎች በቻይና እየተቀደሙ መሆናቸውን ይኸው የአውስትራሊያ የፖሊሲ ምርምር ተቋም አሳውቋል።
ቻይና አሁን ላይ በሚታወቁ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በሚፈጠሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችም የበላይነት ለመያዝ ሩቅ አሳቢ ዕቅድ እንዳላትም ተገልጿል።
የቻይና ግስጋሴም ሀገሪቱን በቅርቡ የቴክኖሎጂ ልዕለ-ኃያል ሊያደርጋት እንደሚችልም ተጠቁሟል።
አልጀዚራ እንደዘገበው አሜሪካ እና ቻይና በበረታ የቴክኖሎጂ ፉክክር ውስጥ ገብተዋለ። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


የገምቱ ይሸለሙ
ውጤቱን ቀድሞ በትክክል ለመለሰ የሞባይል ጥቅል እንሸልማለን። ኮሜንት ላይ ይፃፉልን


ማን ያሸንፋል (ይገምቱ ይሸለሙ)
So‘rovnoma
  •   ማንቸስተር ዩናይትድ
  •   ቼልሲ
8 ta ovoz


5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት በወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭና ሆሳዕና ከተሞች በይፋ ጀመረ
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የአካዳሚክ ማኅበረሰብ አባላት በ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ዙሪያ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 21/2017 ዓ/ም፡ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ለሳይበር ደህንነት የሚጫወተው ሚና በሚል ርዕስ በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ ተማሪዎች እና የአካዳሚክ ማኅበረሰቡ ጋር የቪዲዮ ኮንፍረስን (Video Conference) የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን፤ በዚህም ከ43 ዩኒቨርሲቲዎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ 30 ከሚሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የተውጣጡ ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በቪዲዮ ኮንፈረንሱ ላይ 5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በግለሰብ፣ በተቋም እና  ሀገር ደረጃ ስለሚያስገኘው ፋይዳ፣ የባለድርሻ አካላት እና የዜጎች ሚና እንዲሁም ኢኒሼቲቩ ለሳይበር ደህንነት ስለሚኖረው አበርክቶ ገለጻ ቀርቧል፡፡ ገለጻውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር ልህቀት ማእከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ ያቀረቡ ሲሆን፤ ኢኒሼቲቩ በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ እና የእድሜ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎች ሊወስዱት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ ባለንበት የዲጂታል ዘመን ቴክኖሎጂው ይዞልን የመጣቸው መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ ሁሉ ከፍተኛ የስጋት ተጋላጭነትም ይኖረዋል፤ ለዚህም የዲጂታል ምህዳሩ ላይ መሰረታዊ እውቀት እና ንቃተ  ያለው ዜጋ ለመፍጠር ኢኒሼቲቩ ላይ ያሉ ስልጠናዎች ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ አቶ ቢሻው ተናግረዋል፡፡

የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የተማሪዎችንም ሆነ በአጠቃላይ የታዳጊ ወጣት ኢትዮጵያውያንን መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ክህሎት የሚያጎለብት ስልጠና በመሆኑ ሁሉም ሰው መውሰድ እንደሚገባው  በኮንፈረንሱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ተማሪዎችና የአካዳሚክ ማኅበረሰብ አባላት ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በዛሬው እለት የተካሄደው ኮንፍረንስ ተማሪዎችም ሆነ የአካዳሚክ ማኅበረሰቡ በስልጠናው ላይ በስፋት እንዲሳተፉ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፤ በኢኒሼቲቩ አጠቃላይ  አተገባበር፣ ኢኒሼቲቩን ተግባራዊ ለማድረግ  ሊኖሩ በሚገቡ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ዙሪያ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኢኒሼቲቩ ላይ ከቀረቡት ስልጠናዎች በተጨማሪ መሰረታዊ የሳይበር ደህንነት ስልጠና በሚካተትበትና በሚሰጥበት አግባብ ዙሪያ  ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል ፡፡

በቪዲዮ ኮንፈረንሱ ማብቂያ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደርጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነተ አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ  አርአያሥላሴ እንዳሉት 5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢንሼቲቭ የኢትዮጵያ ወጣቶችን ከመጻኢው ዘመን ጋር የሚያስተሳስር መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ወርቃማ እድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
#5_Million_Ethiopian_Coders #Digital_Ethiopia #INSA  
http://www.ethiocoders.et
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የቴክኖሎጂ ዕውቀት ለማላቅና በዘርፉ ተፈላጊነታቸውን ለማሳደግ የሚሰራውን ተቋም ተዋወቁት፤

ድርጅቱ አመኒም ሶሉሽንስ ይባላል።

የድርጅቱ መስራቾችም እዛው አሜሪካ ነዋሪና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የሆኑት ጀሚላ ተሰማና ጸጋዬ ሽንብር ናቸው።

ድርጅቱ ወደ ስራ በገባባቸው ባለፉት አራት አመታት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስኬታማ መሆን የሚያስችላቸውን ክህሎት ተኮር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በ19 ዙሮች የተቋሙን ስልጠና የወሰዱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በቴክኖሎጂ ዘርፍ በመንግስታዊና የግል ተቋማት ተፈላጊ ባለሙያዎች መሆን የቻሉ ሲሆን፣ ገቢያቸውንና ኑሯቸውን በማሻሻል ላይ ይገኛሉ።

ተቋሙ ከሚሰጠው ስልጠና ባሻገር በወሰዱት ስልጠና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ልምዳቸውን የሚያጋሩበትና ወጣቶችም ትስስር የሚፈጥሩበትን መድረክ ያመቻቻል።

በቅርቡ በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ባዘጋጀው ተመሳሳይ መድረክ ላይም የተቋሙ የቀድሞ ሰልጣኞች ስኬት የተከበረ ሲሆን፣ በሥራ ገበያ ውስጥ አስፈላጊ ስለሆኑ ክህሎቶች የባለሙያዎች ምክርና የልምድ ልውውጥም ተካሂዷል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በቴክኖሎጂው መስክ ከተሻሉ የሥራ አማራጮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያግዙ መሰል የስልጠና ተቋማት በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ እየተበራከቱ በመምጣት ላይ እንዳሉ ከቪኦኤ አማርኛ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። #MoE ════❁✿❁════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ቴስላ ሮቦቫን የተሰኘ አዲስ ሾፌር አልባ ተሽከርካሪ አስተዋወቀ፡፡

ሮቦቫን የሚል መጠሪያ የተሰጠዉ ሾፌር አልባ መኪና በትናንትናዉ ዕለት ቴስላ ባዘጋጀዉ የትዉዉቅ መድረክ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ 20 ሰዎችን የመጫን አቅም ያለዉ መኪናዉ 30ሺህ ዶላር መሸጫ ዋጋ ተተምኖለታል፡፡ 

መኪኖቹ በዋናነት የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጡ ታስበዉ እንደተሰሩ ቴስላራቲ በድረ ገጹ አስታዉቋል፡፡ የቴስላ ባለቤት ኤለን መስክ በትውውቅ መርሓ ግብሩ ወቅት እንደተናገሩት ከአውሮፓውያኑ 2027 በፊት ተሽከርካሪዎቹን ለገበያ ለማቅረብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡

ሮቦቫን ወደ ስራ ሲገባ የትራንስፖርት ዋጋ በመቀነስ ብሎም የመንገድ ላይ ቆይታን በማሳጠር ምቹ የሆነ የትራንስፖርት ሥነ ምህዳርን ለመፍጠር እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

በፈረንጆቹ 2003 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን ለመስራት የተቋቋመዉ ቴስላ አሁን ላይ ትኩረቱን ሾፌር አልባ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ማምረት ላይ አድርጓል ፡፡

════❁✿❁ ═══════
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፦
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.