ቻይና ብላክ ፓንተር 2.0 የተባለ አዲስ ፈጣን ሯጭ ሮቦት ሰራች፡፡
በቻይና ዢጂያንግ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ የጥናት ቡድን በሴኮንድ 10 ሜትር መሮጥ የሚችል ሮቦት መስራቱን ገልጿል። ይህም የዓለማችን ፈጣን ባለ አራት እግር ሮቦት ያደርገዋል። ሮቦቱ ብላክ ፓንተር 2.0 የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል፡፡
ብላክ ፓንተር 2.0 38 ኪሎግራም የሚመዝን ሲሆን 0.63 ሴንቲ ሜትር ቁመት አለው። በ2018 (እ.ኤ.አ) የተጀመረው ሮቦቱን የማበልፀግ ስራ ፍጥነቱን በሰከንድ ከ6 ሜትር እንዲበልጥ ለማድረግ የተለያዩ ማሻሻያዎች ሲደረግ ቆይቷል።
በውሻ አምሳያ የተሰራዉ ሮቦቱ ለወታደራዊ ተልዕኮዎች፣ ለነፍስ አድን ስራ እና ለአሰሳ እንደሚያገለግል ተጠቁሟል፡፡
በ100 ሜትር ሩጫ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ዉድድሩን ለማጠናቀቅ በሰኮንድ 10 ሜትር ይሮጣሉ፡፡ ተመራማሪዎቹ በቀጣይ የሮቦቱን ፍጥነት በሴኮንድ 15 ለማድረስ እየሰሩ መሆኑንን ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል፡፡
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን : Gettechinfofb
የቴሌግራም አድራሻችንን: https://t.me/Gettechinfonow