Postlar filtri
















Rev. Tezera Yared (GloriousLifeChurch) dan repost
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)
... ዓለሞች...
“እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤”
— ቆላስይስ 1፥15-16

✍️ የሚታይ ውጤት የሚያመጡት የማይታየውን የሚያዩ ሰዎች ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ሰብአዊ እምነት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት እንዳለ በግልጽ ያስተምረናል።

የሰብአዊ እምነት ምሳሌ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም ቶማስ ግን በአለማመን ብዙ ትምህርትን የወሰድንበት ነው። ሰብአዊ እምነት የሚመሰረተው በአምስቱ የስሜት ህዋሳቶች ላይና በአእምሮ ላይ ባለው መረጃ ልክ ነው።
እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱሳዊ የእምነት ምሳሌ የሚሆኑ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም አብርሃም ግን የእምነት አባት ነው። በእምነት ሕይወቱም ብዙ ለእምነት ሕይወት የሚሆን መልህቆችን ያስተምረናል።

የሚታየው ነገር ከሚታየው ነው ብሎ ማመን ሰብአዊ እምነት ሲሆን፤ የማይታየውን ነገር ለሚታየው ምክንያት ነው ብሎ ማመን ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ነው።

በመጨረሻም መጽሐፍ ቅዱስ ተፈጥሮአዊ፣ስጋዊ እና ግዑዛዊ አለም ማለትም የሚታየውና የሚዳሰሰው አለም፤ እንዲሁም መንፈሳዊ አለም ማለትም የማናየውና የማንዳስሰው አለም እንዳለ ይነግረናል።
ስለዚህ የማናየው አለም የሚታየውን አለም ስለሚገዛ ከማይታየው አለም ጋር የጠበቀ ግንኙነት በቃሉ እና በመንፈሱ በማድረግ በዚህ በሚታየው አለም ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር እንበርታ!

ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 06/04/2017
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም ምሽት!








…ለሰው የከበረ ሀብት!!!
መጽሐፈ ምሳሌ 12
27፤ ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፤
ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።
መትጋት እና አለመትጋት በሰው ልጆች መሀከል ከፍተኛ ልዩነትን የሚያመጣ አስደናቂ ነገር ነው፤ ዛሬ ከሰነፍን ዛሬ በሰነፍንበት ነገር ነገ ወደን ሳይሆን በግዳችን እንተጋለን፤ ትጋት ከፍተኛ ውጤትን የሚያመጣው በትክክለኛ ጊዜና ሰአት ሲደረግ ብቻ ነው!!!
መልካም የትጋት ቀን!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ






ቡራኬ 🙌 Blessing

💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

“ከእግዚአብሔር ቤት ባረክናችሁ።”
  — መዝሙር 118፥26

“We have blessed you from the house of the Lord.”
  — Psalms 118:26

አድራሻችን: ከለም ሆቴል ወደ 24 ቀበሌ የሚወስደውን ሃይ ዌይ መንገድ እንደጨረሱ በስተ ግራ በኩል ያገኙናል፡፡

☆ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል ሕይወትዎ ለዘላለም ይለወጣል።

Share 👉🏼 @AgapeGLC


ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ!

💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

አድራሻችን: ከለም ሆቴል ወደ 24 ቀበሌ የሚወስደውን ሃይ ዌይ መንገድ እንደጨረሱ በስተ ግራ በኩል ያገኙናል፡፡

☆ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል ሕይወትዎ ለዘላለም ይለወጣል።

📢 የፍቅር እና የእምነት ድምጽ👂

Share 👉🏼 @AgapeGLC




.... አባታችሁማ....!!!
“እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ በሰማይ የሚኖር አባታችሁማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም!””
የሉቃስ ወንጌል 11:13 አማ05





20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.