#ቀዕቃዕ_ኢብኑ_ዓምር
✍አሚር ሰይድ
ታላቁ የኢስላም የጦር መሪ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ የፋርስ ሙሽሪኮችን ለመዋጋት 10ሺህ ሙጃሂዶችን አዘጋጅቶ ወደ ጦር ሜዳ ዘመተ። የጦር ሜዳው ላይ የተሰለፉትን የፋርስ ወታደሮች ሲመለከት ከሙስሊሞች ሠራዊት በቁጥርና በትጥቅ የበለጡ እጅግ ግዙፍ ሆነው አገኛቸው። ሙጃሂዶቹን ማማከር የዘ።
“ወደ መዲና እንመሰስ? ወይንስ ሸሂድ እስከምንሆን ድረስ እንዋጋ?" በማለት ጠየቀ። ሁሉም በአንድ ድምፅ ተክቢራ አሰሙና አንዲህ በማለት መለሱ
.....“ከሀገራችን የወጣነው ሸሂድ ሆነን ለመሞትና በስሮቿ ጅረቶች በሚፈሱባት ጀነት ለመግባት አይደልን?!” አሉ።
ኻለድ የወታደሮቹ መልስ አስደሰተው። ግዙፉን የኪስራን ጦር ለመፋለም በቂ ሠራዊት አልነበረውምና ከመዲና ተጨማሪ ኃይል እንዲላክበት ለኸሊፋው አቡበከር ደብዳቤ ላከ።
የኻሊድ ሠራዊት ከሰፈረበት ርቀት የበረሀውን አሸዋ እያቆራረጠ የሚመጣን ፈረሰኛ ተመለከቱ። የሚያነሳው አቧራ የሚመጣውን ሰው በቅጡ እንዳያዩ ጋርዷቸዋል። የኸሊፋው አቡበከር አጋዥ ጦር እንደሆነ ግን ገምተዋል። በትኩረት ሲመለከቱት አጓድ ፊቱን የሸፈነ ፈረሰኛ ነበር። ለማረጋገጥ ወደ ኋላው ተመለከቱ። ምንም ነገር የለም። ኸሊፋው ምን ነክቷቸው ነው የኪስራን ግዙፍ ሠራዊት ለመግጠም አንድ ፈረሰኛ የሚልኩት! አንድ ሰው? አዎ! እስላም በብዛት አያምንም። ወደሠራዊቱ ተጠጋና ኸሊፋው አቡበከር የሰጠውን ደብዳቤ ይዞ ወደ ፊት አመራ። ፊቱን ገለጠና ስሙን አስተዋወቀ “እኔ አሚሩል ሙእሚኒን የላኩኝ ትጥቅና ሠራዊት ነኝ" አለ። አቡበክር የላኩለትን ደብዳቤ ለኻሊድ ሰጠ። ደብዳቤውን ማንበብ ጀመረ።
"የአላህ ባሪያ ከሆነው አቡበከር ለኻለድ የተላከ:-
ወንድሜ! የላኩልክ አንድ ሰው ብቻ እንዳይመስልህ የቃዕቃዕ ድምፅ ከአንድ ሺህ ፈረሰኞች ይበልጣል ቃዕቃዕ ያለበት ሠራዊት ፈፅሞ አይሸነፍም" ይላል። የኻሊድ ፊት በፈገግታ ደመቀ "የአላህ ሠራዊቶች ሆይ! ፋርሶችን ለመግጠም ተዘጋጁ! ተጨማሪ ኃይል ደርሶናል” አለ።
ጦርነቱ ተጀመረ። የጠላት ጦር መሪ ሁርሙዝ ወታደሮቹን አዘዘ “ከኻለድ ጋር ብቻ ለብቻ
በምንገጥምበት ሰዐት ከጀርባ መጥታችሁ ግደሉት" አለ።
የመሪዎቹ ግጥሚያ ተጀመረ። ኻለድ ሁርሙዝንን በመግጠም ተዘናግቶ ሳለ የጠላት ወታደሮች በጀርባው በኩል መጡ። ጀግናው ቃዕቃዕ እንደ አንበሳ የጦር ሜዳውን ተቀላቀለ። አንድ በአጓድ ሁሉንም አንገታቸውን በጠሰ። ጦርነቱንም ሙስሊሞች አሸነፉ።
አቡበክር ሲዲቅ ይህን ሲሰሙ ለኻሊድ አንዲህ በማለት ደብዳቤ ላኩ “ቀዕቃዕ ያለበት ሠራዊት አንደማይሸነፍ አሁን ያወቅክ ይመስለኛ"
ያ የቀድሞው የድልና የክብር ታሪካችን የተገነባው አንደ ቃዕቃዕ አብኑ ዓምር ባሉ ጀግና ወጣቶች ነበር
ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group