Bahiru Teka dan repost
🔷 ረመዳንን ለመቀበል የሚረዱ 10 ነጥቦች
ካለፈው የቀጠለ
ያለፈውን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/4636
ረመዳንን ለመቀበል ከሚረዱ ነጥቦች አምስተኛውን ( ተውበት አደርጎ መቀበል ) የሚለውን አይተን ነበር ።
– ስድስተኛው – ከመሀበራዊ መገናኛ ዘዴዎች
በተለይ እንደ ፌስቡክ ፣ ቲክ – ቶክና ፣ ዩ – ቲዩብ የመሳሰሉት መራቅ ።
እንደነዚህ አይነት ሚዲያዎች ምእራባዊያን የሰውን ልጅ ባጠቃላይ ሙስሊሞችን በተለይ ከስነምግባር ውጪና የስሜት አምላኪዎች ለማድረግ የዘረጉዋቸው መረቦች ናቸው ። በእነዚህ ድህረገፆች አማካይነት የሚለቋችው ፀያፍ ፊልምና ምስሎች ሰዎችን በቀላሉ ከስነምግባር ውጪ አድርገው የስሜት አምላኪ ያደርጉታል ።
የሚያሳዝነው በእነዚህ ሚዲያዎች ዋናው ተጠቃሚ ሙስሊሙ መሆኑ ነው ። ከረመዳን ፆም ቱሩፋት ተጠቃሚ ለመሆንና ያለችውን የኢማን ጭላንጭል ለመጠበቅ የፈለገ ሰው ከእነዚህ ሚዲያዎች ይራቅ ። የረመዳንን ወር ለመቀበል ከዚህ ወደ አዘቅት ይዞ ከሚጓዝ የስሜት ፈረስ ወርዶ በተውበት ፈረስ ወደ አላህ መገስገስ ይነርበታል ።
– ሰባተኛ – ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ማድረስ
አላህ ባሪያው አንድ ፀጋ ሲውልለት ካመሰገነ ሌላ ፀጋ ይጨምርለታል ። ከፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ በላኢላሀ ኢልለላህ ኑሮ ለረመዳን ወር መድረስ ነው ። ለዚህ ፀጋው አላህን ማመስገን በጣም አስፈላጊ ነው ። ባሪያው ለረመዳን ወር ስላደረሰው ካመሰገነው በቱሩፋቱ ተጠቃሚ ያደርገዋል ። ወንጀሉንም ሊምርለት ሰበብ ይሆነዋልና አላህን ማመስገን ባህሪያችን እንዲያደርግልን እንለምነዋለን ።
– ስምንተኛ – ይቅር ማለት
ረመዳንን ለመቀበል ልብን ንፁህ አድርጎ የአእምሯችንን ገፆች ነጭ አድርገን ከዘመድ ከጓደኛ ከማንኛውም ሰው ያለን ዲናዊ ያልሆኑ ቅያሜዎችን አስወግደን ለበደለን ይቅር ብለን መቀበል ይኖርብናል ። በዱንያዊ ጉዳይ ቂም ይዞ ፆም ትርፉ ረሀብና ጥም ነው ። የሁለት የተጣሉ ሰዎች ስራ እስኪታረቁ ድረስ ወደ አላህ ዘንድ አይወጣምና ።
– ዘጠነኛ – ፆመኞችን ለማስፈጠር መዘጋጀት
ረመዳን ሲመጣ አብዛኛው ሰው በአቅሙ ልክ የተለያዩ ማፍጠሪያዎችን ያዘጋጃል ። ይህ ውስጣዊ ዝግጅት ከቀደመውና ማባከን ከሌለበት ጥሩ ነው ። ከዚሁ ጎን ለጎን ረመዳን የመተዛዘን የመረዳዳት ወር እንደመሆኑ ምስኪኖችን ፣ አቅመደካሞችን ሰው ፊት ቆመው የማይለምኑ ችግራቸው አላህና ራሳቸው እንጂ ማንም የማያውቅላቸው ወንድምና እህቶችን በማስታወስ የምንችለውን በማድረግ በረመዳን እንዲደሰቱ ለማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል ።
– አስረኛ – ቁርኣን ለመቅራት መነየት
ረመዳን ቁርኣን የወረደበትና የቁርኣን ወር ስለሆነ ይህ አላህ ለአማኞች የሰጠው የህይወት መመሪያ የሆነውን ገፀበረከት በውስጡ የሁለት ሀገር ስኬት የያዘው ከጌታችን ለየአንዳንዳችን የተላከው ደብዳቤ አንብበን በውስጡ ያለውን ማእድን ሳንጠቀምበት አላህ ፊት እንዳንቀርብ ቁርጥ ባለ ንያ ቁርኣን መቅራት እጀምራለሁ ብለን ልንዘጋጅ ይገባል ። ቀጥሎ ባወጣነው ፕሮግራም መሰረት በቀኑ ወይም በማታው ክ/ጊዜ ጀምረን ለማክተም እንዲወፍቀን አላህን መለመን አለብን ።
አላህ ካገራላቸው ባሮቹ ያድርገን ።
ጠቃሚ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ ።
https://t.me/bahruteka