ቄስ አለሙ ሼጣ አረፉ። ህብረቱ በጉዳዩ ላይ ይህን ብሏል..
"የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን ከመጋቢት 1999 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2008 ዓ.ም በዋና ጸሐፊነት የመሩት ቄስ ዓለሙ ሼጣ በዛሬው ዕለት ወደ ሚወዱትና ወዳገለገሉት አምላካቸው ዕቅፍ ተሰብስበዋል።
ኅብረቱን በታማኝነትና በጥበብ በመምራት በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የነበሩት ወንድማችንና አባታችን ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም በማረፍ ሞቶ ወደ ተቤዣቸው ጌታ ክብር ገብተዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ በወንድማችን፣ በሥራ ባልደረባችንና በአባታችን እረፍት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለመላው ወንጌላውያን አማኞች መጽናናትን ይመኛል።"
@meleket_tube